በ 07/11/2013 ዓ.ም ረቡዕ ቀን አስራአንድ ሰዓት በቅጡ ሳይሞላ ራት ለመብላት ተቻኩዬ ነበር።
ራት ለመብላት በእጅጉ ቸኩዬ ነበር ሆኖም በላሁኝ። በእውነቱ ጣፋጭ ነበር ። ነገር ግን የበላሁ ስለመሆኔ ለማወቅ ከአፌ የቀረውን ጣዕም በማጣጣም ካልሆነ በሆዴ የለም። ልደታ ማሪያም ቤተክርስቲያንን ተሳልሜ ስመለስ ፤ በበዶ ሆዴ የማድር መስሎ ተሰማኝ ።

ጓደኛዬ አብሮኝ ከቤተክርስቲያን እዬተመለሰ ነበርና እሱም መራቡን ነገረኝ። በወቅቱም ሲኒዬር የሆነ ተማሪ የሚያጠግብ ድቡልቡል የተጠበሰ ዳቦ ቢበላ እንደመከረው ነገረኝ። ገዝተን ለሁለት ተካፍለን እንድንበላ ሃሳብ አቀረብሁለት። ተቀባይነት በማግኘቱ ከለሁለታችንም አስር አስር የኢትዮጵያብር አዋጥተን ገዛን ። የተመለስልልንን ዝርዝር የአምስት ብር ሳንቲም መልሰን ተካፍለን ማስቲካ ገዛንበት። ሙሉሙሉ 15 ብር መሆኑ ነው!
በወቅቱ ብዙም አይነደረቅ የሚባል አይነት ሰዎች አይደለንም ነበር። ሁለታችንም ጭል ወዳለው ቦታ ለመሄድ አሰብን። ዳሩ አዲስአበባ ጭል የሚል መንደር ለማግኘት ይከብዳል ስለዚህ በግራና በቀኝ አስፋልት በመሐል የባቡር መስመር እና እልፍ ህዝብ በሞላበት አካባቢ ለመመገብ ተገደድን። ሙልሙሉ ለሁለት ተከፈለ ፤ የተጠቀለለበት ቅጠልም ተገፎ ተጣለ።

ነገር ግን መብላት እንደጀመርን በመንገዱ ከሚጎርፉት እልፍ ሰዎች መከካከል አንድ ሴት ከጓደዋ ጋር እየመጣች ሳለ ወደኛ አፈጠጠች። እኛም መንገድ ዳር መብላት ነውር መስሎን ስለነበር ተሳቀቅን። ነገር ግን ልጅቷ አልፋን ትንሽ ራቅ ካለች በኋላ ወደኛ ዞራ በመቆም፤ ወደኛ እያየች ልበል/ ልተው የሚል ስሜት ይነበብባት ጀመር። ጤንነቷን ተጠራጥረን ከጓደኛዬ ሀውልቱ ጋር በመገረም ተያየን።
ልጅቷ ወዲያው ከጓደኛዋ ተነጥላ ወደኛ በመቅረብ ትንሽ ቁራሽ እንድሰጣት “ትንሽ ዳቦ ስጠኝ እስኪ” በሚል አሳዛኝ ተማፅኖ ጠየቀችኝ። እኔም ድንግጥ አልኩና የፍራቻዬን ያክል “ስጣት” አልኩት ጓደኛዬ ሀውልቱን።
አላመነታም፤ ቆርሶ ሰጣት።
ያኔ ያልተረሳኝ ነገር ቢኖር ልጁ እየቆረሰ ባለበት ጊዜ “ትንሽ፣ ትንሽ” ማለቷ ነበር ። ብዙም አልፈለግችም ማለት ነው። ያንን ማለቷ ጥያቄዋ የመድሃኒት መሆኑን እንድንጠራጠር አደረገን።
አመስግና ከሄደች በኋላ “ምናልባት የስኳር በሽታ ታማሚ ትሆናለች።” አለኝ ሀውልቱ።
በትንሽ ነገር ሰው ማዳን ይቻላል ። ምናልባት ያች ቁራሽ ባትፈውስ ታስታግሳለች።