ኪዳን ግዕዝ ፤ አማርኛና እንግሊዝኛ
መልክዐ ውዳሴ ዘሰንበት
ኃ.ደ / ጌ.ተ - H.D / G.T Columbus OHIO 2020
ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ
ማርያም እምነ ናስተበቍዓኪ።
እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን
እንሰግድልሻለን ፤ እንማልድሻለን።
ኃደ / ጌተ-HaDe / GeTe Columbus, OH,
እምዓርዌ ነአዊ ተማኅፀነ ብኪ
በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ
ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።
ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል። ስለ
እናትሽ ፣ ስለሐና ብለሽ ፤ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄ
ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።
ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምአኑስ
አንቲ ውእቱ ቀመረ መድኃኒት ሐዳስ።
በሰዎች ሁሉ የተወደድሽ ፤ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
አዲስ አማናዊቱ (እውነተኛይቱ) ቀመር አንቺ ነሽ።
ማርያም ድንግል ወለተ ዳዊት ንጉሥ
ሰላም ሰላም ለመልክዕኪ ውዱስ
ለለ፩ዱ እስከ እግር ወርእስ።
የንጉሥ ዳዊት ልጅ ድንግል ማርያም ከእግር እስከ
ራስ ለእያንዳንዱ ፤ ለተመሰገነው መልክሽ ሰላም ሰላም
እላለሁ።
ታቦት አንቲ ዘረሰየኪ ታዕካሁ
ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ ሥጋኪ ሥጋሁ።
ማደሪያው አድርጎ የመረጠሽ አማናይቱ
(እውነተኛይቱ) ታቦት አንቺ ነሽ።
ማርያም ድንግል ለእጓለ እመሕያው ተስፋሁ
ዕቀብኒ እግዝእትየ ለለመዋዕሉ ወርኁ
እስመ ኢየአምር ሰብእ ዘይመጽእ ላዕሌሁ።
ከሥጋሽ ሥጋ ፤ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ ኢየሱስ ክርስቶስ
ካንቺ ተወልዷልና። እመቤቴ በየጊዜውና በየሰዓቱ
ጠብቂኝ። ሰው በራሱ ላይ የሚመጣውን ነገር
አያውቅምና።
መቅደስ አንቲ ዘይኬልሉኪ ኪሩቤል
እለ ሥዑላን በሥዕሉ ለእግዚአብሔር ቃል።
በእግዚአብሔር ቃል ሥዕል የተሣሉ ፤ ኪሩቤል
የሚጋርዷት አማናይቱ (እውነተኛይቱ) መቅደስ
አንቺ ነሽ።
ማርያም ድንግል መክሐ ደናግል
ሰላም ሰላም በምልዓ ሕሊናየ እብል
ለልደትኪ ፍሥሓ ወሣህል።
የደናግል መመኪያ ፣ ድንግል ማርያም ፣ ይቅርታና
ደስታ ላለበት ልደትሽ በፍፁም ልቦናዬ ሰላም ሰላም
እላለሁ።
አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ቀይሕ
እንተ ውስቴታ መና ብሩህ።
በውስጧ ብሩህ መና ያለባት የወርቅ መሶብ አንቺ
ነሽ።
ማርያም ታቦት ዘተከለልኪ በንጽሕ
አድኅንኒ እግዝእትየ እማየ ሙስና መፍርህ
ከመ አድኃንኪዮ ቀዳሚ ለኖኅ።
በንጽሕና ፣ በቅድስና ያጌጥሽ ድንግል ማርያም ድሮ
ኖኅን ከጥፋት ውኃ እንዳዳንሽው እመቤቴ ማርያም
እኔንም አድኝኝ።
አንቲ ውእቱ ተቅዋመ ወርቅ ዘትነብሪ
ብርሃኖ ለዓለም ዘትፀውሪ።
እውነተኛውን የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን
የተሸከምሽ ፤ ለዘላለም የሆንሽ እውነተኛይቱ
(አማናዊቱ) የወርቅ ተቋም ድንግል ማርያም ነሽ።
ኦ ድንግል መሐሪት እመ መሐሪ
ኃጥአነ እለ ከማየ አመ ይኴንን ፈጣሪ
ለአድኅኖትየ ማርያም ሥመሪ።
ፈጣሪ እንደ እኔ የመሰሉት ኃጢአተኞችን በሚፈርድበት
ጊዜ የምሕረት አምላክ እናት ፤ መሐሪ የሆንሽ ድንግል
ማርያም እኔን ለማዳን ውደጂ።
አንቲ ውእቱ ማዕጠንተ ወርቅ እግዝእትየ
ፍሕመ መለኮት ብቍጽ እንተ ዲቤኪ ተወድየ።
ልዩ ንፁሕ የመለኮት ፍሕም የተጨመረብሽ ፣
የወርቅ ማዕጠንት እመቤቴ አንቺ ነሽ።
ማርያም ድንግል ደመና ብዕልየ
በዝናመ ሣህልኪ ሐረገ ወይን ፀገየ
ወሮማንሂ ሐዋዘ ፈረየ።
ድንግል ማርያም የብዕሌ (ብልጽግናዬ ) ደመና አንቺ
ነሽ። በንጽሕናሽ ዝናም ሐረገወይን አበበ። ሮማንም
መልካም ፍሬን አፈራ።
ተፈሥሒ ማርያም ርግበ ገነት ጽባሐይ
እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ።
የአዶናይ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ፤
የምሥራቃዊው ገነት እርግብ ማርያም ደስ ይበልሽ።
አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ
ዘሠረፅኪ እምሥርወ ዕሤይ
ወእምጕንደ ዳዊት ኅሩይ
ፍሬ ማኅፀንኪ ይሴፎ ነዳይ።
ከእሴይ ሥር ፣ ከተመረጠው ዳዊት ግንድ የበቀልሽ
መዓዛሽ ያማረ ፣ የወደደ ፣ ማርያም አበባ ፣ የማሕፀንሽ
ፍሬ ወልድን ድሀው ሁሉ ተስፋ ያደርገዋል።
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ዘእንበለ ተክል ቀዳሚ
ምሳሌኪ ኮነ በሥምረተ አምላክ ቀዋሚ።
ሳይተክሏት ተተክላ ፣ ውኃ ሳይጠጧት አብባ
ለምልማ እንደተገኘችው የዓሮን በትር ፣ በሕያው
አምላክ ፈቃድ ምሳሌሽ እንዲሁ ሆነ።
ስእለተ ነዳያን ማርያም ዘኢትጸመሚ
አስተበቍዓኪ በዕለተ ምንዳቤ ማሕመሚ
ውስተ የማንየ ለነዳይ ትቁሚ።
የነዳያንን ልመና ችላ የማትዪ ማርያም በአስጨናቂው
የችግር ቀን በእኔው በድሀው ቀኝ ትቆሚ ዘንድ
እማልድሻለሁ።
ለኪ ይደሉ ውዳሴ ወስባሔ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ዘይትረከብ ውስተ ኲለሄ።
የኤሎሄ እናት ድንግል ማርያም ፣ በሁሉም ቦታ
በሚገኙት መላእክትና የሰው ልጆች አንደበት
ፍፁም ምሥጋና ይገባሻል።
ማርያም ድንግል ማርያም እመ ኤሎሄ
ከመ ለብሐዊ ፍቁርኪ አቅረብኩ እማኄ
ለዝክረ ስምኪ ዘምዕዝ እምርኄ።
እንደወዳጅሽ ለብሐዊው (አንጥረኛው) ቅዱስ ኤፍሬም
መዓዛው ከሽቶ ለሚበልጠው ለስምሽ አጠራር እጅ
መንሻን አቀርባለሁ።
ሰአሊ ለነ ፤ ሰአሊ ለነ ፤ ሰአሊ በእንቲአነ
ማርያም እምነ ፤ ወእሙ ለእግዚእነ
ወልድኪ ይምሐረነ ፤ ወመዋርስቲሁ ይረስየነ
በየማኑ ያቁመነ።
ልጅሽ ውዳጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲምረን ፤ በቀኙ
እንዲያቆመንና የርስቱ ወራሾች እንዲያደርገን ፤
የጌታችን እናትና እናታችን ድንግል ማርያም ስለእኛ
ብለሽ ለምኝልን ፤ ለምኝልን ፤ ለምኝልን።
ስብሐት ለኪ ማርያም በኈልቈ አድባር ወአውግር።
ስብሐት ለኪ ማርያም በኈልቈ ቀላያት ወባሕር።
ስብሐት ለኪ ማርያም በኈልቈ ዕፀው ወሣዕር።
ማርያም በተራሮችና በኰረብታዎች ቁጥር ልክ ምሥጋና
ይገባሻል። ማርያም በጥልቆችና በባሕሮች ቁጥር ምሥጋና
ይገባሻል። ማርያም በዛፎችና ሣሮች ቁጥር ልክ ምሥጋና
ይገባሻል።
ስብሐት ለኪ ንግሥተ ፍቅር በልሳነ ኲሉ ፍጡር።
እስመ ምሉዕ ስብሐትኪ በሰማይ ወምድር።
ንግሥቴ ሆይ በፍጡራን አንደበት ሁሉ ምሥጋና
ይገባሻል። በሰማይና በምድር ምሥጋናሽ የመላ (ምሉዕ)
ነውና።
ጸሎተ ቡራኬ
መቅድመ ኪዳን
ተሠሃልከ እግዚኦ ምድረከ።
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሉያ
ሕዝብ በአንድነት (People)
ተሠሃልከ እግዚኦ ምድረከ።
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሉያ
ይእቲ ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ ሰአሊ በእንቲአነ
ከመ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ያስተርኢ ኂሩቶ በላዕሌነ።
ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ፍሥሓ ወሰላም ለእለ
አመነ።
ወሚጥ መዓተከ እምኔነ
ሕዝብ በአንድነት (People)
አርእየነ እግዚኦ ሣህለከ።
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሉያ ፣
ሃሌ ሉያ
ይእቲ ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ ሰአሊ በእንቲአነ
ከመ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ያስተርኢ ኂሩቶ በላዕሌነ።
ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ፍሥሓ ወሰላም ለእለ
አመነ።
ሰላመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወፍቅራ ለእግዝእትነ
ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ሞገሰ መስቀሉ ወኀብተ
ረድኤቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ወትረ ኢይርኃቅ እምኔነ ወእምነ ኵልክሙ እስከ ለዓለም።
በመቀባበል
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ።
ጸሎተ ኪዳን
ኪዳን ዘነግህ መሥዋዕት ዘሥርክ ዘነገሮሙ እግዚእነ
ለአርዳኢሁ ንጹሐን እምቅድመ ዕርገቱ ውስተ ሰማይ ድኅረ
ትንሣኤሁ እሙታን ሣህሉ ወምሕረቱ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ
ዓለም አሜን።
ካህን (Prist)
ቅዱስ
Holy
እግዚአብሔር ፤ ቅዱስ ኃያል ፤ ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ፤
ዘተወልደ እም ማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ
እግዚኦ።
እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት ከቅድስት
ድንግል ማርያም የተወለደ ፤ አቤቱ ይቅር በለን።
God, holy mighty, holy Living, Immortal, who was born
from the holy Virgin Mary; have mercy upon us, Lord.
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ፤ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ
ተሣሃለነ እግዚኦ።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት
በዮርዳኖስ የተጠመቀ ፤ በመስቀል ላይ የተሰቀለ ፤ አቤቱ
ይቅር በለን።
Holy God, holy Mighty, holy living, Immortal, who was
baptized in Jordan and crucified on the tree of the
cross; have mercy upon us, Lord.
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት
በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ።
Holy God, holy Mighty, holy Living, Immortal, who did
rise from the dead on the third day,
ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ
ይመጽእ በስብሐት ይኮንን ሕያዋነ ወሙታነ ፤ ተሣሃለነ
እግዚኦ።
በምስጋና ወደ ሰማይ ወጣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።
ዳግመኛም በጌትነት ፤ ይመጣል በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ
ዘንድ አቤቱ ይቅር በለን።
ascend into heaven in glory, sit at the right hand
of the Father and wilt come again in glory to judge the
quick and the dead; have mercy upon us, Lord.
ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን
ለይኩን።
ለአብ ምስጋና ይሁን ፤ ለወልድም ምስጋና ይሁን ፤ ለመንፈስ
ቅዱስ ምስጋና ይሁን ፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን ፤
አሜን ይሁን ይሁን።
Glory be to the Father, glory be to the Son, glory be
to the Holy Spirit, both now and ever and world
without end. Amen and amen, so be it, so be it.
ቅዱስ ሥሉስ እግዚአብሔር ሕያው ተሣሃለነ።
ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን።
O holy Trinity, living God, have mercy upon us.
ስብሐት ለእግዚአብሔር።
ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን።
Glory be to God.
ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባል።
It is right, it is just.
አቤቱ ሁሉን ለፈጠርህ ለማትመረመር አምላክ ለአንተ
ሰውነታችንን እናስገዛለን። አቤቱ የነግህ ምስጋናንም
እናቀርብልሃለን። የሁሉ ዕውቀት ኃያል የምትሆን ፣ ይቅርታህ
የበዛ አምላክ ፤ ነፍስን የፈጠርሃት ፤ ከዓለም አስቀድሞ ከአብ
የተወለድህ አንተን እናመሰግንሃለን።
O Lord, maker of all, in visible God, we stretch out our
soul to thee and we offer morning prayer unto thee. O
Lord, the powerful wisdom of all, God plenteous in mercy,
the maker of the soul, we glorify thee, begotten
from the Father be fore the creation of the world;
የብቻው ቃል የምትሆን በቅዱሳን አድሮባቸው የሚኖር አርምሞ
በሌለበት ምስጋና አለቆች ካሏቸው ሠራዊተ መላእክትም
የምትመሰገን ፤ በእጅ ያልተፈጠርህ ፤ የተሠወሩትን የፈጠርህ ፤
የማትታይ ንጹሕ ቅዱስ የምስጋናህን ኅቡእ ጥበብን ያስረዳንን
የተናገርህ ፤
Thou, who art the only Word and does rest in Thy
saints, art praised by the archangels with ceaseless
glories. Thou was not created with hands but art creator
of the hidden things, Thou art the invisible, pure, and
holy, and the announcer who told us the wisdom of Thy
hidden glory.
የማይጠፋ ብርሃንን ለኛ ተስፋ ያስደረግከን። አቤቱ ፍጹም
ምስጋናን ንጹሕ ምስጋናንም ለአንተ እናቀርባለን።
እኛ የአንተ አገልጋዮች እናመሰግንሃለን። ሕዝቡም አንተን
ያመሰግናሉ።
Thou hast made us hope for the unquenchable light;
and we, Thy servants, offer unto thee glory, thanksgiving
and holiness; and the people glorify thee.
ኪያከ ንሴብሕ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግናለን።
O Lord, we glorify thee.
የብርሃን አምላክ ሆይ ፣ የሕይወት መገኛ ፤ የዕውቀት
መጀመሪያ ፣ ጸጋን በፍጹም ጸጋ የሚሰጥ። ነፍስን የፈጠረ
መንፈስ ቅዱስን በመስጠት የሚጠቅም ፤
O God of light, Thou art the source of life, the head of
know ledge, the giver of grace from the perfect grace,
the maker of the soul, giver of good, giver of the Holy
Spirit,
የጥበብ መገኛ የቅዱሳን መምህርና የዓለም መሠረት ፤
የንጹሓንን ጸሎት የሚቀበል። ወልድ ዋሕድ አንተን
እናመሰግናለን።
the treasure of wisdom, the helper, the teacher of
saints, the foundation of the world, who acceptest the
prayer of the holy ones. We glorify thee, O only-
begotten Son,
ቀዳሜ በኵር የምትሆን የአብ ቃል ፣ ለምንጠራህ ለእኛ ለሁሉ
የሚሆን የአንተን ጸጋ የሰጠኸን። ነውር የሌለብህ ንጹሕ
አባት። ብል ነቀዝ የማያበላሸው ገንዘብ ያለህ ፤ በፍጹም
ልቡናቸው ለሚያምኑብህ የምትሰጥ።
the first-born Word of the Father; Thou hast granted
Thy universal grace to us who call upon thee. O pure
and blameless Father, Thou hast the treasures which
moth and rust do not corrupt, and of which Thou givest
to those who trust upon thee in all their thoughts.
ዓለም ሳይፈጠር የነበረውን ብርሃን ያዩት ዘንድ መላእክትን ደስ
የሚያሰኛቸው ፤ የማይለወጥ ጠባቂያችን። በእኛ የነበረውን
ጨለማ በአባትህ ፈቃድ አራቅህልን።
Through Thy Father's pleasure Thou hast enlightened
us, we who had treasured up darkness, we whom Thou
hast brought from darkness to light,
ከጨለማ ወደ ብርሃን አወጣኸን ፤ ከሞት አድነህ ሕይወትን
ሰጠኸን። ከመገዛት ነጻ አወጣኸን። በመስቀልህ በሰማይ
ወዳለው ወደ አባትህ ያቀረብከን።
and granted us life after death, and granted us
freedom from slavery. With Thy cross Thou hast
brought us nearer to Thy Father in heaven.
አቤቱ በወንጌል መራኸን። በነቢያት አረጋጋኸን። ያቀረብከን
አምላክ አንተ ነህ። ዳግመኛ አቤቱ ዕውቀትን ግለጽልን።
ለአንተ ለአምላካችን ምስጋናን እናቀርባለን።
With the gospel Thou hast led us and with the
prophets Thou hast comforted us, we whom Thou hast
brought nigh, O God. Give us, O God, light. We praise
thee,
አርምሞ በሌለበት ምስጋና እኛ የአንተ አገልጋዮች
እናመሰግንሃለን። ሕዝቡም አንተን ያመሰግናሉ።
O our God, that with ceaseless thanksgiving we may
say that we are Thy servants; and the people praise
thee.
ኪያከ ንዌድስ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግናለን።
O Lord, we praise thee.
ከሁሉ በላይ የምትሆን የእግዚአብሔር ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ
ሆይ ጌትነትህ ለዘላለም ከሚሆን መንግሥትህ ጋራ በቃላችን
ይህንን ምስጋና ሦስተኛ ጊዜ ለአንተ እናቀርባለን። ፍጥረት
ሁሉ በመራድ በመፍራት ያመሰግንሃል።
O Jesus, the Son of God, who art above all, thrice over
do we offer thanksgiving unto thee with Thy Father in
Thy eternal kingdom, and all the creatures glorify thee
in trembling and fear of soul.
ነፍስ ሁሉ የሚፈራው ፣ የሚያመልከው የጻድቃን ነፍሳት
በአንተ ጸንተው ይኖራሉ። መናፍስት ያመጡትን የጐርፉን
ፈሳሽነት ከእኛ ጸጥ ያደረግህልን ፤ ከጥፋት አድነህ የሕይወት
ወደብ የሆንከን ፤
And all the souls of the righteous trust in thee, Thou
who didst quiet the stormy floods of the evil spirits for
our sake, and who became to us life from destruction,
and a refuge wherein there is the hope of eternal
salvation.
የዘላለም ድኅነት አለኝታ ያለበት መሸሻ የሆንከን ፤ በባሕር
የተጨነቁትን የምታድን ፤ በምድረ በዳ ያሉትንም የምታድን
Thou savest those who are troubled on the sea,
through Thy grace Thou healest those who are in the
wilderness,
በጽኑ እስራት ካሉትም ጋራ አብረሃቸው የምትኖር ከሞት
ማሰሪያ የፈታኸን ፤ ችጋረኞችንና የሚያለቅሱትን
የሚያረጋጋቸው። የደከሙትን በመስቀሉ የሚያድን ፤
Thou accompaniest those whose imprisonment is very
hard; so loosen us from the bond of death. Thou
comfortest the miserable and the weeping, Thou savest
the weak with Thy cross,
ከአመንበት ከእኛ መዓቱን ሁሉ የሚያርቅ ፤ ነቢያትና
ሐዋርያት በኅቡእ ያመሰገኑህን አንተን አቤቱ እናመሰግናለን።
Thou takest away and removest all the wrath from us
who have trusted in thee. O Lord, whom the prophets
and the apostles thanked secretly, we thank thee.
ለአንተ ምስጋና እናቀርባለን። አንተን አምነን በመንግሥተ
ሰማያት እናርፍ ዘንድ ፤ ፈቃድህንም እየሠራን በትእዛዝህ
እንድንሄድ አድርገን። ሁሉንም በቸርነትህ ጐብኝ ትንንሾችንም
ትልልቆችንም። ገዢውንና ሕዝቡን ፣ ጠባቂውንና መንጋውን።
O Lord, whom the prophets and the apostles thanked
secretly, we thank thee. We glorify thee, so that we,
believing in thee and fulfilling Thy will, may rest in the
abode of life. Grant us to walk according to Thy order.
O Lord, through Thy mercy visit all, small and great,
rulers and people, shepherd and flock
አቤቱ አምላካችን ሆይ ክቡር መንግሥት የአንተ ነውና
ከዓለም አስቀድሞ ምስጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለልጅ ልጅ ለዘላለሙ የማይፈጸም።
…….ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እምቅድመ
ዓለም ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለትውልደ ትውልድ
ዘኢየኀልቅ ለዓለመ ዓለም።
for Thine is the kingdom, O blessed Lord our God.
Glory be to the Father, the Son and the Holy Spirit,
before the creation of the world, both now and ever,
and from generation to endless generations, and world
without end.
አሜን።
Amen.
ጸጋ ዘእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።
The grace of God be with you.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Thy spirit.
ንሰብሖ ለአምላክነ።
ፈጣሪያችንን እናመስግን።
Let us glorify our God.
ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባል።
It is right, it is just.
አጽንዑ ሕሊና ልብክሙ።
የልባችሁን አሳብ አጽኑ።
Strengthen the thought of your heart.
.
ብነ ኀበ እግዚአብሔር አቡነ ዘበሰማያት አቡነ ዘበሰማያት ፤
አቡነ ዘበሰማያት ፤ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
ከእግዚአብሔር ዘንድ አለን። አባታችን ሆይ አባታችን ሆይ ፤
አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
We lift them unto the Lord, our Father who art in
heaven, our Father who art in heaven, our Father who
art in heaven, lead us not into temptation.
ብርሃንን የሚሰጥ እግዚአብሔር አብ ፤ ለሁሉ ኃይል
የሚሆን ፤ ነፍስን ሁሉ የሚጐበኝ ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ
ብርሃን ፤ ዓለምን የፈጠረ ፤ ወደ ሕይወት የሚመራ ፤
የማያልፈውን ተድላ የሚሰጥ ነው።
O God the Father, giver of light, the power of all,
visitor of all souls, light which was before, creator of
the world, the leader of life and giver of immortal
happiness:
ከጨለማ መሰናክል አውጥተህ የማይገኝ ብርሃንን የሰጠኸን ፤
ያመንብህን እኛን ከማዕሠረ ክሕደት አውጥተህ በሃይማኖት
ያከበርከን።
ከአገልጋዮቹ የማይርቅ ፣ የማይለይ ዘወትር ከእነርሱ ጋራ
የሚኖር ፤ በፍርሃት በረዓድ የምትለምነውን ነፍስ ቸል የማይል
Thou hast taken us out of the snares of darkness, and
granted us the unsearchable light. Thou hast loosed us,
we who believe in thee, and covered us with faith.
Thou art not far from Thy servants but art always with
them. Thou dost not neglect the soul which supplicates
thee with fear and trembling.
ከሕሊና አስቅድሞ ሁሉን የሚያውቅ ፤ ከአሳብ አስቀድሞ
የሚመረምር ፤ ሳንለምነው የምንሻውን አውቆ የሚሰጠን ፤
ሳንጠራጠር የምንለምነውን የሚሰማን ፤
Thou knowest all before the thought, and examinest all
before the thought. Through Thy will Thou suppliest our
needs before we ask; Thou hearest us who call upon
thee without doubting.
የማይመረመር ብርሃን። በሰማያት ያሉ የመላእክት ንጉሥ
አድሮባቸው የሚኖር ሊቃነ መላእክት ያቀረቡትን ምስጋና
የሚቀበል።
Thou art the unsearchable light and the King of the
heavenly hosts, bearer of the glorious song of the
archangels upon whom Thou restest.
አቤቱ የምንለምንህን ስማን ፤ አርምሞ የሌለበትን ቃል
በሃይማኖት ስጠን። አንተን ፈጽሞ እናመሰግን ዘንድ ፤ አንተን
እናከብር ዘንድ ፤ በአንተም ጸንተን እንኖር ዘንድ አቤቱ እኛ
አገልጋዮችህ እናመሰግናለን።
O Lord, we pray thee to hear us. Grant us the
unceasing word in trust. We glorify thee, we thank thee,
and we bless thee; O Lord, we, Thy servants, glorify
thee because we depend upon thee.
ኪያከ ንሴብሕ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግናለን።
O Lord, we glorify thee.
አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቊርጥ ልመናችንን ስማን።
ድዳ ለነበሩት ቃል ፤ለተሰበሩት ምርጒዝ ፤ ለዕዉራን ብርሃን ፤
ለሐንካሶች መሄጃ ፤ ለምጻሙን የሚያንጻ ሆንሃናቸው። በደዌ
የተያዙትን አቤቱ አዳንህ ፤ ደንቆሮችን ፈወስህ።
O Lord, Jesus Christ, holy, Thou hast heard us. Thou
didst become a word to the dumb, a staff to the broken
ones, light to the blind, a way to the lame, and the
purifier of the lepers. O Lord, Thou didst heal the sick
and cure the deaf.
ሞትን ዘለፈው። ጨለማንም ሣቀየው ፤ ብርሃንን የፈጠረ
ኅልፈት የሌለበት። ፀሐይ የማይጠፋ ፋኖስ ፤ በቅዱሳን ላይ
ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ ፤ በተወሰነ በቍርጥ ፈቃድ ለዓለም
ጌጥ ሁሉን የፈጠረ።
Thou didst rebuke death and destroy the darkness.
Thou didst create the light of the sun which does not
set, the unquenchable light, the Sun which always
shineth over the holy ones, Thou didst establish all
through Thy fixed will for the decoration of the world.
ሰውን ለማዳን ለሁሉ ተገለጽህ ፤ ነፍስን የመለስሃት አንተ
ነህ። ሁሉን እንደሚገባ ማሰብን አስቀደምህ። መላእክትን
የፈጠርህ ፤ የሁሉ አባት ፤ የሁሉ ጌታ ፤ የዓለም ጌጥ ፤
ምድርን የፈጠርሃት። ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ፤ ጥበብና
ዕውቀት ከአብ ወደዚህ ዓለም ተላከ።
Thou didst appear clearly to all to save man, Thou art
the restorer of the soul, and Thou wert beforehand in
determining all things rightly. O Thou, Creator of
angels, Father of all, the adornment of the world and
the maker of earth, Wisdom and Knowledge were sent
to the world by the Father who was before.
ይህ አኗዋር የማይለወጥ ፣ የማይፈርስ ፤ የማይመረመር ነው ፤
የማይታይ መንፈስ ነው። ይህን የተናገርህ አንተ ምስጉን ነህ።
ምስክርነትህም የተደነቀ ነው። ስለዚህ እኛ አገልጋዮችህ
እናመሰግንሃለን።
This existence is unchangeable and unsearchable and
invisible Spirit. Thou art the glorious announcer and Thy
name is wonderful. For this reason we, Thy servants,
praise thee, O Lord.
ኪያከ ንዌድስ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግናለን።
O Lord, we praise thee.
የማይለወጥ ባንተ ማመንን የሰጠኸን አቤቱ ይህን ክቡር
ምስጋና ሦስተኛ ጊዜ እናቀርብልሃለን። የሞትን ማሠርያ
ክሕደትን በሃይማኖት ድል እንድንነሳው ያደረክልን ፤
ለሚያምኑብህ ቅን ልቡናን የፈጠርህ ፤ ከሰው ወገን አማልክት
ይባሉ ዘንድ ፤
Thrice over do we offer this holy glory to thee, who
hast given us Thy unchangeable faith with which Thou
hast made us break the bonds of death. Thou didst
create the up right minds of those who believe in thee
that they may be called gods among men.
በመንፈስ የጠላትን ኃይል እንረግጥ ዘንድ የሰጠኸን ፤
የማይፈታውን እንፈታ ዘንድ ከአባትህ ዘንድ ፍቅርን
አደረግህልን። በመካከላችንም ሆነህ አስታረቅኸን። አቤቱ
የሚለምኑህን ስማቸው። አቤቱ የምንለምንህ እኛ አንከሰስ ፤
በመከሰስ ጊዜ በጠላታችን ላይ እንኑርበት እንጂ።
Thou hast granted us to tread down all the powers of the
.enemy through the Spirit, so that we may loosen that
which cannot be loosened. Thou hast made effectual for
us love towards Thy Father and made reconciliation
between us and him. O Lord, hear those who supplicate
thee.
ዘወትር እንድንጸልይ አንድርገን። ከጠላታችን ማታለል
እንጠበቅ ዘንድ የዘላለም ንጉሥ ሆይ ስማ። ባልቴቱን
አርጋጋት። አባት እናት የሞቱበትን ልጅ ተቀበል። የታለሉትን
በቸርነትህ አንጻ። ሰነፎችን አስብ ፤ አዋቂ አድርጋቸው።
O Lord, let not us, who sup plicate thee, fall into sin,
but vindicate us against our enemies, our accusers.
Grant us continuous prayer that we may be kept from
being swallowed up by the enemy. O eternal King, hear;
comfort the widows, accept the orphans, purify the
unclean through Thy mercy, grant wisdom to the foolish,
የጠፉትን መልስ። በግዞት ያሉትን አድናቸው። ለሁላችንም
መጸግያ ሁነን። አቤቱ አምላካችን ክቡር መንግሥት ያንተ
ነውና።
እለ ውስተ ሞቅሕ አድኅን ወለኵልነ ኩን ፀወነ እስመ ለከ
እግዚኦ አምላክነ መንግሥት ቡሩክ።
Restore the lost, save the prisoners, and be a refuge to
all of us, for Thine is the blessed kingdom, O Lord our
God.
አሜን።
Amen
ጸጋሁ ለእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከናንተ ጋር ይሁን።
The grace of God be with you.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Thy spirit.
አእኵትዎ ለአምላክነ።
ፈጣሪያችንን አመስግኑት።
Give ye thanks unto Our God.
ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባል።
It is right, it is just.
የማትለወጥ አንተን አብን የነፍሳችን መድኃኒት የምትሆን
የጥበባት መሠረት የልቡናችን ጠባቂ። ውሳጣዊ ዓይናችንን
ብሩኅ ያደረግህልን። የሕሊናችንን ጨለማ አርቀህ ከአንተ
በሚገኝ ዕውቀት አከበርከን። ለጥፋት የተሰጠ የቀደመ ሰው
አዳምን በልጅህ መስቀል አዳንህ ፤
O immortal Father, Saviour of our soul, the foundation
of wisdom, keeper of our hearts, Thou hast granted light
to our inward eyes and covered us with Thy knowledge
against the darkness of our mind Thou didst save the
first man, who was given to destruction,
በማይለወጥ አደስከው። ስሕተቶች በትዕዛዝህ ጠፉ። በልጅህ
ሞት አዳንህ። የጠፋውን ፈለግህ።
ስለዚህ እኛ አገልጋዮችህ እናመሰግናለን።
by the cross of Thy Only-begotten, and didst renew
him by the immortal things. Iniquities vanished through
Thy commandment, and Thou didst make redemption
through the death of Thy Son and didst search for the
lost one.
For this reason we, Thy servants, glorify thee, O
Lord.
ንሴብሐከ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግናለን።
We glorify thee, O Lord.
ሳናቋርጥ አርምሞ ጽርዓት በሌለበት ቃል ሊቃነ መላእክት
ለሚያመሰግኑህ ለአንተ ከምስጋና የሚበልጥ ምስጋናን
እናቀርብልሃለን። ያውም መላእክት የሚያመሰግኑት ምስጋና
ነው። አቤቱ አንተን በማኅሌት ያመሰግኑሃል።
We praise thee, O Lord, with glorious song, Thou whom
the archangels always glorify, unceasingly and without
rest, and whom the lords praise singing with the praise
of glory and thanksgiving. O Lord, Thou hast sent Thy
counsel,
ያንተ ምክር ፣ ያንተ ቃል ፣ ያንተ ጥበብ ፣ ያንተ መጐብኘት
የላክኸው ወልድ ከቀድሞ ጀምሮ ከአንተ ጋራ የነበረ ፤ ዓለም
ሳይፈጠር ያልተፈጠረ ፤
Thy Word, Thy Wisdom and Thy visitation, which was
with thee before the world began, without being
created; that is the Word who was not created,
ባሕርየ ሰብእን ለማዳን በሥጋ የተገለጸ ቃል ልጅህ ወዳጅህ
ጌታችን ኢየሱስ ከኃጢአት ቀንበር ነጻ አደረገን። አቤቱ
ስለዚህ እኛ አገልጋዮችህ እናመሰግንሃለን።
who appeared in flesh for the salvation of mankind.
Thy beloved Son, our Lord Jesus, hath set us free
from the yoke of sin. For this reason we, Thy
servants, praise thee, O Lord.
ንዌድሰከ እግዚኦ።
አቤቱ እናመሰግንሃለን።
We praise thee, O Lord.
ምስጋናን ሦስተኛ ጊዜ ከልባችን ለአንተ እናቀርባለን።
ሕይወትን የምትሰጥ አቤቱ። የትሑታንን ሰውነት የሚጐበኝ ፤
የተቸገረውን ሰውነት ቸል የማይል ፤ ከሀገራቸው የተሰደዱትን
የሚቀበላቸው ፤ የሚረዳቸው። በመከራ ያሉትን የሚያድን ፤
From our heart we offer to thee thrice over praise, O
Lord, giver of life. Thou didst visit the soul of the
humble and didst not despise the troubled soul. Thou
didst accept the persecuted and help them, Thou didst
save those in difficulty.
ለተራቡት የሚያስብላቸው ፤ ለተበደሉ የሚበቀልላቸው።
የምእመናን ወዳጅ ለጻድቃን የሚመሰክርላቸው። የንጹሓን
ማደሪያቸው ፤ በእውነት የሚለምኑትን የሚሰማ ፤ ባልቴቷን
የሚሠውር ፤ አባት እናት የሞቱበትን የሚያድን ፤
Thou thinkest of the hungry and avengest those against
whom sin was committed. Thou art the friend of the
faithful, speaker to the righteous, dwelling-place for the
pure; Thou hearest those who call upon thee in
righteousness, protectest the widow, savest the orphan,
የሃይማኖት ክብር ምስጋና ማረፊያ ላደረጋት ለቤተ ክርስቲያን
ቅን መሪ የሚሰጥ። ሀብት ጸጋ ኃይልም የመንፈስ ቅዱስ ጉባኤ
የምትሆን።
Grantest right leadership to the church which Thou
hast made a dwelling-place of the glorious faith, the
council of the Spirit, the gift of grace and power.
አንተን ስናመሰግን ዘወትርም ሳናርፍ የመንግሥትህን ነገር
በልቡናችን እናውቃለን። አንተ ስለገለጽህልን ፤ ልጅህ ወዳጅህ
ጌታችን ኢየሱስም ስለገለጸልን ምስጋና ጽንዕ ያለው ለዘላለሙ።
በእንቲአከ ወበእንተ ፍቁር ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ ዘቦቱ ለከ
ስብሐት ወእኂዝ ለዓለመ ዓለም።
While we praise thee without rest we know in our
hearts Thy kingdom which was declared unto us by
thee and Thy beloved Son, our Lord Jesus, through
whom be glory and dominion to thee, world without end.
አሜን።
Amen
ጸሎት
Prayer
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ……..
አባታችን ሆይ ፤ በሰማያት የምትኖር ፤ ስምህ ይቀደስ……..
Our Father who art in heaven, hallowed be Thy
name…...
ጸሎተ ቡራኬ
Prayer Of Blessing
አነሣሥቶ ለአስጀመረን ፤ አስጀምሮም ለአስፈጸመን
ክብርና ምስጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለአንድ አምላክ ይገባል ፤
ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ኃይሉ ደስታ በቀለ Hailu Desta Bekele
March 15,
ምንጭ / Source: mytewahdo.org
← ጸሎተ ነግህ