ቅዳሴ ቄርሎስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም።
አሜን።
In the Name of the Father, the Son, and the Holy
Spirit One GOD. Amen.
ሚመጠን ግርምት ዛቲ ዕለት ወዕፅብት ዛቲ ሰዓት እንተ ባቲ
ይወርድ መንፈስ ቅዱስ እመልዕልተ ሰማያት ወይጼልሎ
ለዝንቱ መሥዋዕት ወይቄድሶ።
ይህች ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት? ይህችስ ሰዓት ምን
ያህል የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከሰማያተ ሰማያት
የሚወርድባት ፤ ይህን መሥዋዕቱን የሚሠውርባትና
የሚያከብርባት።
How awful is this day and how marvelous this hour
wherein the Holy Spirit will descend from Heaven and
over-shadow and hallow this sacrifice.
በጽሙና ወበፍርሀት ቁሙ ወጸልዩ ከመ ሰላሙ ለእግዚአብሔር
የሀሉ ምስሌየ ወምስለ ኵልክሙ።
በጽሞናና በመፍራት ቁሙ ፤ የእግዚአብሔር ሰላም ከእኔና
ከእናንተ ጋራ ይሆን ዘንድ ጸልዩ።
In quietness and in fear, stand up and pray that the
peace of God be with me and with all of you.
አሜን።
Amen.
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
On the days from Monday to Friday
እምነ በሀ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት ዓረፋቲሃ ወስእልት
በዕንቍ ጳዝዮን። እምነ በሀ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን።
እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንልሻለን።
ግድግዳዎችዋ የተሸለሙና በጳዝዮን ዕንቍ ያጌጠች ናት።
እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንልሻለን።
Peace be unto you, our mother, O honorable church.
your walls are embroidered with Topaz. Peace be unto
you, our mother, O honorable church.
በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት - On Saturdays
መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ እምኵሉሰ ፀሐየ
አርአየ። መስቀል አብርሃ! በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ።
መስቀል አበራ ሰማይን በኮከቦች ሸለመ(አስጌጠ)። ከሁሉም
ይልቅ ፀሐይን አሳየ። መስቀል አበራ። በኮከቦች ሰማይን
ሸለመ።
The cross shined and had the heavens embroidered
with stars. Of all the sun is seen. The cross shined and
had the heavens embroidered with stars.
በዕለተ እሑድ - On Sundays
ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ ፤ ኢይበል
ፈላሲ ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ
በጎን የሚያደርግ ፣ ሰንበትንም የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው።
“ወደ እግዚአብሔር አምልኮ የገባ መጻተኛ ከሕዝቡ ሁሉ ይለየኝ
ይሆንን?” አይበል ፤
Blessed is he who does blessed deeds and honors the
Sabbath. Let him not question whether he will be outcast
from the multitudes if he was to enter into the worship of
God.
ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ።
በጎ ያደረገ ሰንበትንም የሚያከብር ጻድቅ ነው።
Blessed is he who does blessed deeds and honors the
Sabbath.
ሃሌ ሉያ እመቦ ብእሲ እምእመናን ዘቦአ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ
ቅዳሴ ወኢሰምዐ መጻሕፍተ ቅዱሳተ ወኢተዐገሠ እስከ ይፌጽሙ
ጸሎተ ወቅዳሴ ወኢተመጠወ እምቍርባን ይሰደድ እምቤተ
ሃሌ ሉያ በቅዳሴ ጊዜ ከምእመናን ወገን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ
ሰው ቢኖር ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት
እስኪጨርሱ ባይታገሥ ከቍርባኑም ባይቀበል ከቤተ ክርስቲያን
Halleluia! If there be anyone of the faithful that has
entered the church the time of mass not heard the Holy
Scriptures, and has not waited until they finish the prayer
of the Mass, and has not received the Holy communion,
let him be driven out of the church:
ክርስቲያን ፤ እስመ አማሰነ ሕገ እግዚአብሔር ወአስተሐቀረ
ቁመተ ቅድመ ንጉሥ ሰማያዊ ንጉሠ ሥጋ ወመንፈስ ከመዝ
መሀሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ።
ይለይ ፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷልና ፤ የነፍስና የሥጋ
ንጉሥ በሚሆን በሰማያዊ ንጉሥ ፊት መቆምን አቃሏልና ፤
ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዲህ አስተማሩን።
for he has violated the law of God and disdained to
stand before the heavenly King, the King of Body and
Spirit. The Apostles have taught us in their canons.
ክርስቶስ አምላክነ ዘበአማን እግዚእነ ዘሖርከ ውስተ ከብካብ አመ
ጸውዑከ በቃና ዘገሊላ ወባረከሎሙ ወረሰይኮ ለማይ ወይነ ከማሁ
ረስዮ ለዝንቱ ወይን ዘክቡር በቅድሜከ።
እውነተኛ አምላካችን ጌታችን ክርስቶስ ሆይ የገሊላ አውራጃ
በምትሆን በቃና በጠሩህ ጊዜ ወደ ሠርግ የሄድህ ውኃውንም
ባርከህ ጠጅ ያደረግህላቸው ፤ በፊትህ የተቀመጠ ይህንን ወይን
እንደርሱ አድርገው።
Christ our God, truly our Lord, Who went to the wedding
when they invited You in Cana of Galilee, and did bless
for them the water and changed it into wine, You do in
like manner unto this wine which is set before You.
ወይዜኒ ባርኮ ወቀድሶ ወአንጽሖ ይኩን ለሕይወተ ነፍስነ
ወሥጋነ ወመንፈስነ በኵሉ ጊዜ። ሀሉ ምስሌነ አብ ወወልድ
ወመንፈስ
አሁንም ባርከው አክብረውም ፤ አንጻውም ሁልጌዜ የሥጋችንና
የነፍሳችን የልቡናችንም ሕይወት ይሆን ዘንድ። አብ ወልድ
Now also please bless it, hallow it and purify it, so that it
may become the life of our soul, body, and spirit at all
times. Father, Son and Holy Spirit,
ቅዱስ ወምላእ ወይነ ትፍሥሕት ወኀሤት ለሠናይ ወለሕይወት
ወለመድኃኒት ወለሥርየተ ኃጢአት ፤ ለልቡና ወለፈውስ
መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ኑር። ለተድላና ለደስታ የሚሆን
ወይኑንም ለበጎ ነገር ምላው። ለሕይወትና ለመድኃኒት ፣
ለኃጢአትም ማስተሠረያ ፣ ለማስተዋል ፣
be with us; and fill the wine with joy and happiness, for
goodness, for life, for salvation and for the remission of
sin, for understanding,
ወለምክረ መንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
አሜን።
ለደኅንነት ለመንፈስ ቅዱስም ምክር ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ
አሜን።
for healing, for the counsel of the Holy Spirit, both now
and ever and world with out end. Amen.
ንጹሕ ወጣዕም ወበረከት ለእለ ይሰትዩ እምደምከ ክቡር
አላትዮን በአማን።
በእውነት ሰው የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ከክቡር ደምህ ለሚጠጡ
ንጹሕ ጣዕም በረከትም ይሁን፤
Purity, sweetness and blessing be to them who honestly
drink of Your precious blood.
አሜን።
Amen.
ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ዓለም አምላክነ።
ዓለሙን ሁሉ የያዘ እግዚአብሔር አብ አምላካችን ቡሩክ ነው።
Blessed be the Lord, Almighty Father, our God.
አሜን።
Amen.
ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድም
ቡሩክ ነው።
And blessed be the only Son, our Lord and our Savior
Jesus Christ.
አሜን።
Amen.
ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ
ኵልነ።
ሁላችንን የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው።
And blessed be the Holy Spirit, the Paraclete, the
comforter and cleanser of us all.
አሜን።
Amen.
ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ዓለም አምላክነ።
ዓለሙን ሁሉ የያዘ እግዚአብሔር አብ አምላካችን ቡሩክ ነው።
Blessed be the Lord, Almighty Father, our God.
አሜን።
Amen.
ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድም
ቡሩክ ነው።
And blessed be the only Son, our Lord and our Savior
Jesus Christ.
አሜን።
Amen.
ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ
ኵልነ።
ሁላችንን የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው።
And blessed be the Holy Spirit, the Paraclete, the
comforter and cleanser of us all.
አሜን።
Amen.
ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ዓለም አምላክነ።
ዓለሙን ሁሉ የያዘ እግዚአብሔር አብ አምላካችን ቡሩክ ነው።
Blessed be the Lord, Almighty Father, our God.
አሜን።
Amen.
ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድም
ቡሩክ ነው።
And blessed be the only Son, our Lord and our Savior
Jesus Christ.
አሜን።
Amen.
ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ
ኵልነ።
ሁላችንን የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው።
And blessed be the Holy Spirit, the Paraclete, the
comforter and cleanser of us all.
አሜን።
Amen.
ስብሐት ወክብር ይደሉ ለሥሉስ ቅዱስ ፤ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ ዕሩይ ኵሎ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ
ዓለም።
ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ሁልጊዜም ለተካከሉ ለአብ ፣ ለወልድ ፣
ለመንፈስ ቅዱስም ክብር ምሥጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም
ለዘላለሙ።
Glory and honour are due to the Holy Trinity, the
Father and the Son and the Holy Spirit always coequal,
both now and ever and world with out end.
አሜን።
Amen.
ጸልዩ አበውየ ወአኃውየ ላዕሌየ ወላዕለ ዝንቱ መሥዋዕት።
አባቶቼና ወንድሞቼ በእኔ ላይ በመሥዋዕቱም ላይ ጸልዩ።
My fathers and my brothers, pray for me and for this
sacrifice.
እግዚአብሔር ይስማዕከ ኵሎ ዘሰአልከ ፤ ወይትወከፍ መሥዋዕተከ
ወቊርባነከ ከመ መሥዋዕተ መልከ ጼዴቅ ፣ ወአሮን ወዘካርያስ
ካህናተ ቤተ ክርስቲያኑ ለበኵር።
እግዚአብሔር የለመንከውን ሁሉ ይስማህ። የበኵር የቤተ ክርስቲያኑ
ካህናቱ የሚሆኑ የመልከ ጼዴቅንና የአሮንን ፣ የዘካርያስንም
መሥዋዕት እንደተቀበለ መሥዋዕትህን ቍርባንህንም ይቀበልልህ።
May God hear you in all that you have asked and accept
your sacrifice and offering like the sacrifice of Melchisedec
and Aaron and Zacharias, the priests of the church of the
first-born.
ቡራኬ።
Benediction
ተዘከረኒ ኦ አቡየ ቀሲስ በጸሎትከ ቅድስት።
ቄሱ አባቴ ሆይ ክብርት በምትሆን በጸሎትህ አስበኝ።
Remember me, my father priest, in your Holy prayers.
እግዚአብሔር ይዕቀባ ለክህነትከ ወይትወከፍ መሥዋዕተከ
ወቍርባነከ በብሩህ ገጽ። ሥመር እግዚኦ ከመ ታድኅነኒ።
እግዚአብሔር ክህነትህን ይጠብቃት። መሥዋዕትህንና
ቊርባንህንም በቡሩህ ገጽ ይቀበልልህ። አቤቱ እኔን ታድነኝ
ዘንድ ማዳንን ውደድ።
The Lord keep your priesthood and accept your
sacrifice and offering with a cheerful countenance. Be
pleased, Lord, to save me.
፩ዱ አብ ቅዱስ።
፩ዱ ወልድ ቅዱስ።
፩ዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
አንዱ አብ ቅዱስ ነው።
አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው።
አንዱ መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው።
One is the Holy Father,
One is the Holy Son,
One is the Holy Spirit.
በአማን አብ ቅዱስ።
በአማን ወልድ ቅዱስ።
በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
አብ በእውነት ቅዱስ ነው።
ወልድም በእውነት ቅዱስ ነው።
መንፈስ ቅዱስም በእውነት ቅዱስ ነው።
Truly the Father is Holy,
Truly the Son is Holy,
Truly the Holy Spirit is Holy.
ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ አሕዛብ።
ሁላችሁም ምዕመናን እግዚአብሔርን አመስግኑት።
Praise The Lord, all you nations.
ወሴብሕዎ ኵሎሙ ሕዝብ።
ሕዝብ ሁሉ ያመሰግኑታል።
And praise Him, all you people.
እስመ ጸንዐት ምሕረቱ ላዕሌነ።
ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና።
For His merciful kindness is great toward us.
ጽድቁሰ ለእግዚአብሔር ይሄሉ ለዓለም።
የእግዚአብሔርስ ቸርነት ለዘለዓለም ይኖራል።
And the Truth of the Lord endures for ever.
ካህኑን በመከተል እንበል - repeat after priest.
ስብሐት ለአብ ፣ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ። ይእዜኒ ወዘልፈኒ
ወለዓለመ ዓለም አሜን ሃሌ ሉያ።
ለአብ ፤ ለወልድ ፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል። ዛሬም
ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን ሃሌሉያ።
Glory be to the Father and to the Son and to the Holy
Spirit. Both now and world without end. Amen.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.3
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with your spirit.
ጸሎተ አኰቴት ዘቅዱስ ባስልዮስ።
የቅዱስ ባስልዮስ የምስጋና ጸሎት።
The “Prayer of Thanksgiving” of St. Basil.
ነአኲቶ ለገባሬ ሠናያት ላዕሌነ እግዚአብሔር መሐሪ አቡሁ
ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ
ሠወረነ
ለእኛ በጎ ነገርን ያደረገ ይቅር ባይ እግዚአብሔርን
እናመሰግነዋለን። ይቅር ባይ የጌታችን የአምላካችንና
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሠውሮናልና ፤
We give thanks unto the doer of good things unto us,
the merciful God, the Father of our Lord and our God
and our Savior Jesus Christ: for He has covered us
ወረድአነ ዐቀበነ ወአቅረበነ ወተወክፈነ ኀቤሁ። ወተማኅፀነነ ፤
ወአጽንዐነ ፤ ወአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት።
ረድቶናልና ፤ ጠብቆ አቅርቦናልና ፤ ወደ እርሱም
ተቀብሎናልና አጽንቶ ጠብቆናልና ፤ እስከዚህም ሰዓት
አድርሶናልና።
and succored us, He has kept us and brought us nigh
and received us unto Himself, and undertaken our
defense, and strengthened us, and brought us unto this
hour.
ንስአሎ እንከ ከመ ይዕቀበነ በዛቲ ዕለት ቅድስት ኵሎ መዋዕለ
ሕይወትነ ወበኵሉ ሰላም አኃዜ ኵሉ እግዚአብሔር አምላክነ።
አሁንም ክብርት በምትሆን በዚህች ዕለት በሕይወታችን ዘመን
ሁሉ በፍጹም ሰላም ሁሉን የሚይዝ አምላካችን እግዚአብሔር
ይጠብቀን ዘንድ እንለምነው።
Let us therefore pray unto Him that the Almighty Lord
our God keep us in this Holy day and all the days of
our life in all peace.
ጸልዩ።
You, pray.
እግዚእ እግዚኦ እግዚአብሔር አኃዜ ኵሉ አቡሁ ለእግዚእነ
ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ነአኵተከ ላዕለ ኵሉ
ግብር በእንተ ኵሉ ግብር ወውስተ ኵሉ ግብር።
ሁሉን የያዝህ ጌታችን እግዚአብሔር የጌታችንና የአምላካችን
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በሥራው ሁሉ ላይ ፤
ስለ ሥራው ሁሉ ፤ በሥራውም ሁሉ ውስጥ እናመሰግንሃለን።
Master, Lord God Almighty, the Father of our Lord and
our God and our Savior Jesus Christ, we render You
thanks upon everything, for everything and in everything,
እስመ ሠወርከነ ወረዳእከነ ፤ ዐቀብከነ ወአቅረብከነ ፤
ወተወከፍከነ ኀቤከ ወተማኅፀንከነ ወአጽናዕከነ ፤ ወአብጻሕከነ
እስከ ዛቲ ሰዓት።
ሠውረኸናልና ፤ ረድተኸናልና ፤ ጠብቀኸናልና ፤ ወዳንተ
አቅርበህ ጠብቀኸናልና ፤ አጽንተህ ጠብቀኸናልና እስከዚህችም
ሰዓት አድርሰኸናልና።
for You have covered us and succoured us, have kept
us and brought us nigh, and received us unto Yourself,
and undertaken our defense, and strengthened us and
brought us unto this hour.
ኅሡ ወአስተብቍዑ ከመ ይምሐረነ እግዚአብሔር ወይሣሀል
ላዕሌነ።
እግዚአብሔር ይምረን ዘንድ በእኛም ላይ ይቅር ይል ዘንድ
እሹ ፤ ለምኑ።
You entreat and beseech that the Lord have pity
upon us and be merciful to us,
ወይትወከፍ ጸሎተ ወስእለተ እምነ ቅዱሳኒሁ በእንቲአነ
በዘይሤኒ ኵሎ ጊዜ ይረስየነ ድልዋነ ከመንንሣእ እምሱታፌ
ምሥጢር ቡሩክ ወይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ስለእኛ ከቅዱሳን ጸሎትን ልመናን ይቀበል ዘንድ ፤ ሁልጊዜ
ባማረ ነገር ቡሩክ ከሚሆን ምሥጢር አንድነት እንድንቀበል
የበቃን ያደርገን ዘንድ።
receive prayer and supplication from His saints on our
behalf, according to what is expedient at all times, so
that He may make us meet to partake of the communion
of the blessed sacrament and forgive us our sins.
ኪርያላይሶን።
አቤቱ ይቅር በለን።
Kyrie eleison..
በእንተ ዝንቱ ንስእለከ። ወነኀሥሥ እምነ ኂሩትከ ኦ መፍቀሬ
ሰብእ ሀበነ ከመ ንፈጽም ዛተ ዕለተ ቅድስተ ኵሎ መዋዕለ
ሕይወትነ ወበኵሉ ሰላም ምስለ ፈሪሆትከ ኵሎ ቅንዓተ
ስለዚህ እንለምንሃለን። ከቸርነትህም እንሻለን። ሰውን የምትወድ
ሆይ ክብርት የምትሆን ይህችን ዕለት እንድንፈጽም ስጠን ፤
የሕይወታችንን ዘመን ሁሉ በፍጹም ሰላም አንተን ከመፍራት
ጋራ።
For this cause we pray and entreat of Your goodness, O
lover of man, grant us to complete this Holy day and all
the days of our life in all peace along with Your fear.
ወኵሎ መከራ ወኵሎ ግብረ ሰይጣን ወምክረ ሰብእ እኩያን
ወእትንሣኤ ፀር ዘኅቡእ ወዘገሃድ። አርኅቅ እግዚኦ እምኔየ
ወእምነ ኵሉ ሕዝብከ ወእምዝቱ መካን ቅዱስ ዘዚአከ።
ቅንዓትን ሁሉ ፣ መከራውንም ሁሉ ፤ የሰይጣንንም ሥራ ሁሉ ፣
የክፉዎች ሰዎችንም ምክር ፣ የጠላትንም መነሣት የተሠወረውንና
የተገለጸውን አቤቱ ከእኔ ፤ ከሕዝቡም ሁሉ ፤ የአንተ ከሚሆን
ከዚህም ቅዱስ ቦታ አርቅ።
All envy, all trial, all the working of Satan, the counsel of
evil, and all the uprisings of adversaries, secret and open,
remove far from me, and from all Your people and from
this Your Holy place. All good things,
ኵሎ ሠናያተ ዘይሤኒ ወዘይኄይስ አዝዝ ለነ እስመ አንተ
ዘወሀብከነ ሥልጣነ ከመ ንኪድ ከይሴ ወአቃርብተ ወዲበ ኵሉ
ኃይለ ጸላዒ።
በጎውን ነገር ሁሉ ፤ ያማረውንና የሚሻለውን እዘዝልን። እባቡን
ጊንጡንም የጠላትንም ኃይል ሁሉ እንረግጥ ዘንድ ሥልጣንን
የሰጠኸን አንተ ነህና።
that are expedient and excellent, command You for us,
for You are He who has given us power to tread upon
serpents and scorpions and upon all the power of the
enemy.
ኢታብአነ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኵሉ
እኩይ በጸጋ ወሣህል ዘለፍቅረ ሰብእ ዘበወልድከ ዋሕድ እግዚእነ
ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘቦቱ ለከ
ወደ መከራ አታግባን ከክፉ አድነን እንጂ። አንድ ልጅህ
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው
ፍቅር ብሎ ባደረገው ቸርነትና ይቅርታ በእርሱ ያለ ምስጋና
Lead us not into temptation, but deliver us and rescue
us from all evil in the grace and loving- kindness, which
were shown by the love towards mankind of Your only-
begotten Son, our Lord, God, and our Saviour Jesus
ስብሐት ወክብር ወእዘዝ ይደሉ ምስሌሁ ወምስለ መንፈስ ቅዱስ
ማሕየዊ ዘዕሩይ ምስሌከ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም
አሜን።
ክብር ጽንዕ ከእርሱ ጋር ለአንተ ይገባል ፤ ከአንተ ጋራ ትክክል
ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም
ለዘላላሙ አሜን።
Christ, through whom to You with Him and with the Holy
Spirit, the life-giver, who is coequal with You are fitting
glory, honour, and dominion, both now and ever, and
world without end. Amen.
ንፍቅ ዲይቆን (Ass’t Deacon)
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ንፍቅ ካህን (Ass’t Priest)
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with your spirit.
ጸሎተ መባእ ዘሐዋርያት
የሐዋርያት የመባ ጸሎት
“The prayer of Oblation” of the Apostles.
ንፍቅ ካህን (Ass’t Priest)
ወካዕበ ናስተበቍዕ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በእንተ እለ ያበውኡ መባአ በውስተ
ቅድስት አሐቲ እንተ ላዕለ ኵሉ ቤተ ክርሲቲያን ፤
ዳግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችንንና የመድኃኒታችንን
የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን። ከሁሉ
በላይ በምትሆን በከበረች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን መባ
ስለሚያስገቡ መስዋዕቱን ቀዳምያቱን ከአሥር አንዱን
And again let us beseech the Almighty Lord, the Father of
the Lord our Savior Jesus Christ, on behalf of those who
bring an oblation within the one Holy universal church,
መስዋዕተ ቀዳማያተ ዐሥራተ አኰቴተ ተዝካር ዘብዙኅ ወዘኅዳጥ
ዘኅቡእ ወዘገሃድ። ወለእለሂ ይፈቅዱ የሀቡ አልቦሙ ዘይሁቡ
የመታሰቢያ ምሥጋና ብዙውንና ጥቂቱን ፤ የተሠወረውንና
የተገለጸውን ይሰጡ ዘንድ ሲወዱ የሚሰጡት ፤ ከሌላቸው ላይ
ፈቃዳቸውን ተቀብሎ መንግሥተ ሰማያትን ይሰጥ ዘንድ
a sacrifice, first-fruits, tithes, a thank-offering, a memorial,
whether much or little, in secret or openly, and of those
who wish to give and have not wherewith to give,
ይትወከፍ ፍትወቶሙ ዘበሰማያት መንግሥተ ይጸጉ ዘለኵሉ
ግብረ በረከት ሥልጣን ቦቱ እግዚአብሔር አምላክነ።
ለሁሉ በረከትን የሚያድልበት ሥልጣን ገንዘቡ የሚሆን
አምላካችን እግዚአብሔር።
that He accept their ready mind, that He vouchsafe to
them the heavenly kingdom; power over all works of
blessing belongs to the Lord our God.
ንፍቅ ዲያቆን (Ass't Deacon)
ጸልዩ በእንተ እለ ያበውኡ መባአ።
መባ ስለሚያገቡ ሰዎች ጸልዩ።
Pray for them who bring an oblation.
ተወከፍ መባኦሙ ለአኃው ፤ ወተወከፍ መባኦን ለአኃት ለነኒ
ተወከፍ መባአነ ወቍርባነነ።
የወንዶችን መባ ተቀበል። የሴቶችን መባ ተቀበል ፤ የእኛንም
መባችንንና ቍርባናችንን ተቀበል።
Accept the oblation of our brothers, accept the oblation
of our sisters, and ours also, accept our oblation and
our offering.
እግዚአብሔር አምላክነ ዘኵሎ ትእኅዝ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ
በእንተ እለ ያበውኡ መባአ በውስተ ቅድስት አሐቲ እንተ ላዕለ
ኵሉ ቤተ ክርስቲያን።
ሁሉን የምትገዛ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ እንለምንሃለን ፤
እንማልድሃለንም። ከሁሉ በላይ የምትሆን በአንዲት ቅድስት
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መባ ስለሚያገቡ ሰዎች።
Lord our God who are Almighty, we pray You and
beseech You for them that bring an oblation within the
one Holy universal church,
መሥዋዕተ ቀዳምያተ ዐሥራተ አኰቴተ ተዝካር ዘብዙኅ
ወዘኅዳጥ ዘኅቡእ ወዘገሃድ ወለእለሂ ይፈቅዱ የሀቡ አልቦሙ
ዘይሁቡ ተወኪፈከ ፍትወቶሙ ሀብ ለኵሎሙ ዐስበ በረከት ክፍለ
ትኩን።
መሥዋዕቱን መጀመሪያውን ፤ ከዐሥር አንዱን የመታሰቢያ
ምስጋናን ብዙውንና ጥቂቱን የተሰወረውንና የተገለጸውን ይሰጡም
ዘንድ ሲወዱ የሚሰጡት ከሌላቸው ላይ ፈቃዳቸውን ተቀብለህ
ለሁሉም የበረከት ዋጋን ስጥ ዕድል ፈንታ ትሆን ዘንድ።
a sacrifice, first-fruits, tithes, a thank-offering, a memorial,
whether much or little, in secret or openly, and have not
wherewith to give. Your acceptance of their ready mind
grant you unto every one: let the recompense of blessing
be a portion to all of them:
በአሐዱ ወልድከ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ
ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን።
በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ላንተ ይገባል፤ ከርሱም
ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ
አሜን።
through Your only-begotten Son, through whom to You
with Him and with the Holy Spirit be glory and dominion,
both now and ever and world without end. Amen.
ንፍቅ ዲይቆን (Ass’t Deacon)
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ንፍቅ ካህን (Ass’t Priest)
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with your spirit.
ጸሎተ እንፎራ
የኅብስት ጸሎት
The prayer of Oblation.
ካህን(priest)
ኦ ሊቅየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሱታፌ ቀዳማዊ ቃለ አብ ንጹሕ
ወቃለ መንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ አንተ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት
ዘወረድከ እምሰማያት፤
መምህሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከቀዳማዊ አብ ጋር አንድ
የምትሆን ንፁሕ የሚሆን የአብ ቃል ፤ የማሕየዊ መንፈስ
ቅዱስም ቃል ፤ ከሰማያት የወረድህ፤
O my Master, Jesus Christ, coeternal pure Word of the
Father, and Word of the Holy Spirit, the life giver, You
are the bread of life which did come down from heaven,
ወአቅደምከ ነጊረ ከመ ትከውን በግዐ ዘአልቦ ነውር በእንተ
ሕይወተ ዓለም ወይእዜኒ ንስእል ወናስተበቊዕ እምነ ኂሩተ
ሠናይቲከ።
የሕይወት ኅብስት አንተ ነህ ስለ ዓለሙ መዳን ነውር የሌለበት
መሥዋዕት እንድትሆን መናገርን አስቀደምህ። አሁንም
ከበጎነትህ ቸርነት እንለምናለን እንማልዳለንም።
and did foretell that You would be the Lamb without spot
for the life of the world: We now pray and beseech of
Your excellent goodness,
ኦ መፍቀሬ ሰብእ አርኢ ገጸከ ላዕለ ዝንቱ ኅብስት ወዲበ
ዝንቱ ጽዋዕ ዘአንበርነ ላዕለ ዝንቱ ታቦት መንፈሳዊ ዘለከ፤
ሰው ወዳጅ ሆይ ያንተ በሚሆን በዚህ በመንፈሳዊ ታቦት ላይ
ባኖርነው በዚህ ኅብስት ላይና በዚህ ጽዋ ላይ ፊትህን ግለጽ።
O lover of man, make Your face to shine upon this
bread, and upon this cup, which we have set upon this
spiritual ark of Yours:
ባርኮ ለዝንቱ ኅብስት። ወቀድሶ ለዝንቱ ጽዋዕ። ወአንጽሖሙ
ለ፪ሆሙ። ወሚጦ ለዝንቱ ኅብስት ይኩን ሥጋከ ንጹሐ
ወዘተደመረ ውስተ ዝንቱ ጽዋዕ ደመከ ክቡረ ወይኩን ለኵልነ
ይህን ኅብስት ባርከው። ይህንንም ጽዋ አክብረው። ሁለቱን
አንጻቸው። ሥጋህን ይሆን ዘንድ ለውጠው በዚህ ጽዋ ውስጥ
የተቀዳውም ወይን የከበረ ደምህን ይሁን ለሁላችንም
Bless this bread and hallow this cup and cleanse them
both, And change this bread to become Your pure Body,
and what is mingled in this cup to become Your
precious Blood;
ዕሩገ ወፈውሰ ለመድኃኒተ ነፍስነ ወሥጋነ ወመንፈስነ። አንተ
ውእቱ ንጉሠ ኵልነ ክርስቶስ አምላክነ ወለከ ንፌኑ ልዑለ
ውዳሴ ወስብሐተ ወስግደተ
ይህ ንጹሕ ያረገ ለነፍሳችንና ለሥጋችን ለልቡናችንም ፈውስ
ይሆን ዘንድ። አምላካችን ክርስቶስ የሁላችን ንጉሥ አንተ ነህ
ከፍ ያለ ምስጋናንና ክብርን ስግደትንም ላንተ እንልካለን ፤
let them be offered for us all for healing and for the
salvation of our soul and our body and our spirit. You
are the King us all, Christ our God, and to You we
send up high praise and glory and worship, with Your
ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ ዘዕሩይ
ምስሌከ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባትህ ጋራ ፤ ካንተ ጋራ ከሚተካከል
ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ
አሜን።
good heavenly Father and the Holy Spirit, the life giver,
who is coequal with You, both now and ever and world
without end. Amen.
ዲያቆን
ትእዛዘ አበዊነ ሐዋርያት ኢያንብር ብእሲ ውስተ ልቡ ቂመ
ወበቀለ ወቅንዓተ ወጽልአ ላዕለ ቢጹ ወኢላዕለ መኑሂ።
ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው። ሰው በልቡናው
ቂምና በቀልን ፤ ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም
ላይ ቢሆን አይያዝ።
This is the order of our fathers the Apostles: Let none
keep in his heart rancour or revenge or envy or hatred
towards his neighbor, or towards any other body.
ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሀት።
በፍርሃት ለእግዚአብሔር ስገዱ።
Worship the Lord with fear.
ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ።
አቤቱ በፊትህ እንሰግዳለን ፤ እናመሰግንሃለንም።
Before You, Lord, we worship, and we do glorify You.
ፍትሐት ዘወልድ (The Absolution of the Son.)
ካህን(priest)
እግዚእ እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድ ቃለ
እግዚአብሔር አብ ዘበተከ እምኔነ ኵሉ ማእሠረ ኃጣውኢነ
በሕማማቲከ ማሕየዊት ወመድኀኒት ፤
አቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድ የእግዚአብሔር
አብ ቃል ማሕየዊት መድኃኒትም በምትሆን በሕማምህ ከእኛ
የኃጢአታችንን ሁሉ ማሠሪያ ያጠፋህ።
Master, Lord Jesus Christ, the only begotten Son, the
word of God the Father, who have broken off from us all
the bonds of our sins through Your life-giving and saving
sufferings,
ዘነፋሕከ ውስተ ገጸ አርዳኢከ ቅዱሳን ወላእካኒከ ንሐን
ወትቤሎሙ ንሥኡ መንፈሰ ቅዱሰ ለእለ ኀደግሙ ኃጢአት
ይትኀደግሎሙ ወለእለ ኢኀደግሙ ኃጢአት ኢይትኀደግሎሙ።
ንጹሐን በሚሆኑ ደቀመዛሙርትህና በንጹሓን አገልጋዮችህ ፊት
እፍ ያልህባቸው “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ይቅር ላላችኋቸው
ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል ይቅርም ላላችኋቸው ኃጢአታቸው
አይቀርላቸውም” ያልካቸው።
who did breathe upon the face of Your Holy disciples
and pure ministers saying to them: “Receive the Holy
Spirit: whatsoever men’s sins you remit they are remitted
unto them, and whatsoever sins you retain they are
retained:”
አንተ ኦ እግዚኦ ይእዜኒ ጸጎከ ክህነተ ለላእካኒከ ንጹሓን ለእለ
ይገብሩ ግብረ ክህነት ኵሎ ጊዜ በቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት
ከመ ይኅድጉ ኃጢአተ በዲበ ምድር ይእሥሩ ወይፍትሑ ኵሎ
ማእሠረ ዐመፃ።
አሁንም በክብርት ቤተ ክርስቲያንህ ሁልጊዜ የክህነት ሥራ
ለሚሠሩ ለንጹሐን አገልጋዮችህ አቤቱ አንተ ክህነትን ሰጠህ
በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ይሉ ዘንድ ያሥሩም ዘንድ
የበደልንም ማሠሪያ ሁሉ ይፈቱ ዘንድ።
You, therefore, O Lord, have now granted the priesthood
to Your pure ministers that do the priests’ office at all
times in Your Holy church that they may remit sin on
earth, may bind and loosen all the bonds of iniquity.
ወይእዜኒ ካዕበ ንስእል ወነኀሥሥ እምነ ኂሩትከ ኦ መፍቀሬ
ሰብእ ፤ በእንተ እሉ አግብርቲከ ወአእማቲከ አበውየ ወአኀውየ
ወአኃትየ ወበእንቲአየሂ አነ ገብርከ ድኩም ፤
አሁንም አቤቱ ሰው ወዳጅ ሆይ ዳግመኛ ከቸርነትህ
እንለምናለን ፤ እንሻለን። ስለነዚህ ስለወንዶችም ስለ ሴቶችም
አገልጋዮችህ አባቶቼና ወንድሞቼ እህቶቼም ደካማ ስለምሆን
ስለእኔም ስለ ባርያህ፤
Now again we pray and entreat of Your goodness, O
lover of man, on behalf of these Your servants and
hand-maids, my fathers and my brothers and my sisters,
and also on my own behalf, on me Your feeble servant,
ወበእንተ እለ አድነኑ አርእስቲሆሙ ቅድመ ምሥዋዒከ ቅዱስ
ጺሕለነ ፍኖተ ምሕረትከ ብትክ ወምትር ኵሎ ማእሠረ
ኃጣውኢነ። ለእመ አበስነ ለከ እግዚኦ በአእምሮ አው ዘእንበለ
አእምሮ አው በጽልሑት፤
በቅዱስ መሠዊያህ ፊት ራሳቸውን ዝቅ ስላደረጉ ሰዎች
የምሕረትን ጎዳና ጥረግልን ፤ የኃጢአታችንን ማሠሪያም ሁሉ
ፈጽመህ አጥፋልን። አቤቱ አንተን ብንበድል በማወቅ ወይም
ባለማወቅ በተንኰልም ቢሆን፤
and on behalf of them that bow their heads before Your
Holy altar: prepare for us the way of Your mercy, break
and sever all the bonds of our sins. Whether we have
trespassed against You, O Lord, wittingly or unwittingly
አው በእከየ ልብ አው በገቢር አው በተናግሮ አው በናእሰ ልብ
እስመ አንተ ተአምር ድካሞ ለሰብእ ፤ ኦ ኄር ወመፍቀሬ ዕጓለ
እመሕያው ወእግዚአ ኵሉ ፍጥረት ጸግወነ ለነ እግዚኦ ሥርየተ
ኃጣውኢነ።
በልቦና ክፋትም ቢሆን ፤ በመሥራትም ቢሆን ፤ በመናገርም
ቢሆን ፤ በዕውቀት ማነስም ቢሆን የሰውን ድካሙን አንተ
ታውቃለህና ፤ ቸር ሰው ወዳጅ ሆይ የፍጥረቱ ሁሉ ጌታ አቤቱ
የኃጢአታችንን ሥርየት ስጠን።
or in deceit or in evilness of heart, whether in deed or in
word or through smallness of understanding, for You know
the feebleness of man. O good lover of man and Lord of
all creation, grant us, O Lord, forgiveness of our sins,
ባርከነ ወቀድሰነ ወአግዕዘነ ወአንጽሐነ ወረስየነ ፍቱሐነ ወግእዛነ
ወለኵሉ ሕዝብከ ፍትሖሙ ፤ ወምላዕ ላዕሌነ ፈሪሆተ ስምከ
ወአቁመነ ኀበ ገቢረ ፈቃድከ ቅዱስ።
ባርከን አክብረንም ነጻም አድርገን ፤ አንጻን የተፈታን ነጻም
የወጣን አድርገን ፤ ሕዝቡንም ሁሉ ፍታቸው ስምህን
መፍራትንም የተመላን አድርገን ቅዱስ ፈቃድህንም በመፍራት
አጽናን።
bless us and purify us and set us free and absolve all
Your people and fill us with the fear of Your name, and
establish us in the doing of Your Holy will.
ኦ ኄር እስመ አንተ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ወለከ ንፌኑ ስብሐተ ወክብረ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ
ወመንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ ዘዕሩይ ምስሌከ ይእዜኒ ወዘልፈኒ
ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ቸር ሆይ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን አንተ ኢየሱስ
ክርስቶስ ነህና ምስጋናንና ክብር ላንተ እናቀርባለን ፤ ሰማያዊ
ከሚሆን ከቸር አባትህ ጋራ ማሕየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም
ጋራ ትክክል የሚሆን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
O Good, for You are our Lord and our God and our
Saviour Jesus Christ, to You we send glory and honour
with Your good heavenly Father, and the Holy Spirit, the
life-giver, who is coequal with You, both now and ever
በየምዕራፉ “አሜን ኪርያላይሶን አቤቱ ይቅር በለን” እንበል።
We shall say after each clause: “Amen Kyrie eleison,
Lord have mercy upon us”
በእንተ ቅድሳት ሰላማዊት ሰላመ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
ያስተሳልመነ በሣህለ ዚአሁ።
አንድ ስለምታደርግ ሥጋውና ደሙ እግዚአብሔር በይቅርታው
አንድ ያደርገን ዘንድ ሰላምን እንማልዳለን።
For the peaceful Holy things we beseech, that God may
grant us peace through His Mercy.
በእንተ ሃይማኖትነ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀበነ
እንቲአሁ ሃይማኖተ በንጹሕ ንዕቀብ።
እግዚአብሔር የእርሱን ሃይማኖት በንጹሕ እንድንጠብቅ
ይሰጠን ዘንድ ስለ ሃይማኖታችን እንማልዳለን።
For our Faith we beseech, that God may grant us to
keep the faith in purity.
በእንተ ማኅበረነ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር እስከ
ፍጻሜነ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ይዕቀበነ።
እስከ ፍጻሜያችን ድረስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ
አንድነት ይጠብቀን ዘንድ ስለ አንድነታችን እንማልዳለን።
For our congregation we beseech, that God may keep
us unto the end in the communion of the Holy Spirit.
በእንተ ትዕግሥታት ነፍሳት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
በኵሉ ምንዳቤነ ፍጻሜ ትዕግሥት ይጸግወነ።
በመከራችን ሁሉ እግዚአብሔር የትዕግሥትን ፍጻሜ ይሰጠን
ዘንድ ፤ ስለ ነፍሳችን ትዕግሥት እንማልዳለን።
For patience of soul we beseech, that God may
vouchsafe us perfect patience in all our tribulation.
በእንተ ነቢያት ቅዱሳን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
ምስሌሆሙ ይኈልቈነ።
ቅዱሳን ስለሚሆኑ ነቢያት ከሳቸው ጋራ እግዚአብሔር
ይቈጥረን ዘንድ እንማልዳለን።
For the Holy prophets we beseech, that God may
number us with them.
በእንተ ሐዋርያት ላዕካን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀበነ
ናሥምር በከመ እሙንቱ አሥመርዎ ወመክፈልቶሙ
ይክፍለነ።
እነሱ ደስ እንዳሰኙት ደስ ልናሰኘው እግዚአብሔር ማገልገሉን
ይሰጠን ዘንድ ፤ ዕድል ፈንታቸውንም ያድለን ዘንድ ፤
አገልጋዮች ስለሚሆኑ ሐዋርያት እንማልዳለን።
For the ministering Apostles we beseech, that God may
grant us to be well pleasing even as they were well
pleasing, and apportion unto us a lot with them.
በእንተ ቅዱሳን ሰማዕታት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
የሀበነ ንፈጽም ኪያሃ ግዕዘ።
እግዚአብሔር ለእኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ፤
ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን።
For the Holy martyrs we beseech, that God may
grant us to perfect the same conversation.
በእንተ ሊቀ ጳጳስነ አባ …… ወብጹዕ ጳጳስ አባ …….
ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀበነ ኪያሆሙ ለነዋህ መዋዕል
በልቡና ያርትዑ ቃለ ሃይማኖት በንጹሕ ዘእንበለ ነውር እስመ
የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እነሱ ናቸውና እግዚአብሔር
እነሱን ለረዥም ወራት ይሰጠን ዘንድ ፤ ያለ ነውር በንጽሕና
ሆነው በዕውቀት የሃይማኖትን ቃል ያቀኑ ዘንድ ፤ ስለ
For our Patriarch Abba …….and the blessed Archbishop
Abba ……we beseech, that God may grant them length
of days to be over us, that with understanding they may
rightly speak the word of faith in purity without spot for
እሙንቱ ቀዋምያኒሃ ለቤተ ክርስቲያን።
ሊቀ ጳጳሳችን ስለ አባ …… ብፁዕ ስለሚሆን ጳጳሳችንም ስለ
አባ ……እንማልዳልን።
that they are the defenders of the church.
በእንተ ቀሳውስት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ኢያሰስል
እምኔሆሙ መንፈሰ ክህነት ጻሕቀ ወፍርሀተ ዚአሁ እስከ ፍጻሜ
ይጸጉ ወፃማሆሙ ይትወከፍ።
የክህነትን ስልጣን ከእነርሱ እግዚአብሔር እንዳያርቅ
መትጋትን ፣ እሱን መፍራትን እስከ ፍጻሜ ይሰጥልን ዘንድ ፤
ድካማቸውንም ይቀበል ዘንድ ፤ ስለ ቀሳውስት እንማልዳለን።
For the priests we beseech, that God may never take
from them the spirit of priesthood, and may give them
the grace of zeal and fear of Him unto the end and
accept their labour.
በእንተ ዲያቆናት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀቦሙ
ምርዋጸ ፍጹመ ይሩጹ ወበቅድስና ይቅረቡ ፃማሆሙ
ወፍቅሮሙ ይዘከር።
ፈጽመው ሊፋጠኑ መፋጠንን እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ
፤ በቅድስናም ይቀርቡ ዘንድ ፤ ድካማቸውንና ፍቅራቸውን
ያስብ ዘንድ ፤ ስለዲያቆናት እንማልዳለን።
For the deacons we beseech, that God may grant
them to run a perfect course, and draw them nigh unto
Him in Holiness, and remember their labour and their
love.
በእንተ ንፍቀ ዲያቆናት ወአናጕንስጢስ ወመዘምራን
ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀቦሙ ፃሕቀ ሃይማኖቶሙ
ይፈጽሙ።
የሃይማኖታቸውን ትጋት ሊፈጽሙ እግዚአብሔር ይሰጣቸው
ዘንድ ፤ ስለ ንፍቀ ዲያቆናት ፤ ስለ አንባቢዎችም ፤
ስለመዘምራንም እንማልዳለን።
For the assistant deacons and the Anagonists (readers)
and the singers we beseech, that God may grant them
to perfect the diligence of their faith.
በእንተ መበለታት ወመዓስባት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
ይስማዕ ስእለቶን ወፈድፋደ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ይጸግዎን
ውስተ አልባቢሆን ወይትወከፍ ፃማሆን።
ልመናቸውን ይሰማቸው ዘንድ ፤ ይልቁንም የመንፈስ ቅዱስን
ሀብት በልቡናቸው ያሳድርባቸው ዘንድ ፤ ድካማቸውንም
ይቀበል ዘንድ ፤ ስለ ባልቴቶች ፤ ረዳትም ስለሌላቸው
እንማልዳለን።
For the widows and the bereaved we beseech, that
God may hear their prayers and vouchsafe them
abundantly in their hearts the grace of the Holy Spirit
and accept their labour.
በእንተ ደናግል ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀቦሙ
አክሊለ ድንግልና ወይኩኑ ለእግዚአብሔር ውሉደ ወአዋልደ
ወይትወከፍ ፃማሆሙ።
እግዚአብሔር የድንግልናቸውን ዋጋ (አክሊል) ይሰጣቸው
ዘንድ ፤ ለእግዚአብሔርም ወንዶችም ሴቶችም ልጆች ይሆኑት
ዘንድ ፤ ድካማቸውንም ይቀበል ዘንድ ፤ ስለ ደናግል
እንማልዳለን።
For the virgins we beseech, that God may grant them
the crown of virginity, and that they maybe unto God
sons and daughters and that He may accept their
labour.
በእንተ መስተዓግሣን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
የሀቦሙ አስቦሙ በትዕግሥት ይንሥኡ።
በመታገሣቸው ዋጋቸውን ይቀበሉ ዘንድ ፤ እግዚአብሔር
እንዲሰጣቸው ስለሚታገሡ ሰዎች እንማልዳለን።
For those who suffer patiently we beseech, that God
may grant them to receive their rewards through
patience.
በእንተ ሕዝባዊያን ወመሃይምናን ናስተበቊዕ ከመ
እግዚአብሔር የሀቦሙ ሃይማኖተ ፍጹመ በንጹሕ ይዕቀቡ።
በንጽሕና ሆነው ይጠብቁ ዘንድ ፤ እግዚአብሔር ሃይማኖትን
እንዲሰጣቸው ስለ ሕዝባውያንና ስለ መሃይምናን እንማልዳለን።
For the laity and faithful we beseech, that God may
grant them complete faith which they may keep in purity.
በእንተ ንዑሰ ክርስቲያን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀቦሙ
መክፈልተ ሠናየ ወሕፅበተ ዳግም ልደት ለሥርየተ ኃጢአት
ወበማኅተመ ቅድስት ሥላሴ ይኅትሞሙ።
በጎውን ዕድል ኃጢአትን ለማስተሥረይ ሁለተኛ መወለድ
የሚገኝበትን ሕፅበት እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ ፤ በቅድስት
ሥላሴም ማኅተም ያከብራቸው ፤ ያትማቸው ዘንድ ፤ ስለ ንዑሰ
ክርስቲያን እንማልዳለን።
For the catechumens we beseech, that God may grant
them a good portion and the washing of regeneration for
the remission of sin, and seal them with the seal of the
Holy Trinity.
በእንተ መፍቀሪተ እግዚአብሔር ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ናስተበቊዕ
ከመ እግዚአብሔር ብዙኃ ሰላመ ይጸጉ በማዕከሌሃ።
ዘወትር ፍጹም ሰላምን እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ ፤
እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ
እንማልዳለን።
For our country Ethiopia Lover of God we beseech, that
God may grant her peace.
በእንተ መኳንንት ወእለ በሥልጣናት ናስተበቊዕ ከመ
እግዚአብሔር ጥበበ ወፍርሀተ ዚአሁ የሀቦሙ።
ዕውቀትን እርሱን መፍራትንም እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ
፤ ስለ መኳንንትና ሥልጣን ስላላቸው እንማልዳለን።
For the rulers and those in authority we beseech, that
God may grant them of His wisdom and His fear.
በእንተ ኵሉ ዓለም ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ያቅድም
ሐልዮ ወየሐሊ ለለ፩ዱ ጻሕቆ ዘይሤኒ ወዘይኄይስ።
ስለ ዓለሙ ሁሉ እግዚአብሔር ማሰብን ያስቀድም ዘንድ ፤
ለእያንዳንዱም የሚያስፈልገውን ፣ ያማረውን የሚሻለውንም
ያስብ ዘንድ ፤ ስለ ዓለም ሁሉ እንማልዳለን።
For the whole world we beseech, that God should
hasten His purpose and put into the mind of all and
each to desire that which is good and expedient.
በእንተ እለ ይነግዱ በባሕር ወበየብስ ናስተበቊዕ ከመ
እግዚአብሔር በየማነ ሣህል ይምርሆሙ ወያግብኦሙ ኀበ
ማኅደሪሆሙ በዳኅና ወበሰላም።
እግዚአብሔር ይቅርታ ባለው ቀኝ መርቶ በፍቅርና በደኅንነት
ወደ ማደሪያቸው ይመልሳቸው ዘንድ ፤ በባሕርና በደረቅ
ስለሚሄዱ ሰዎች እንማልዳለን።
For them that travel by sea and by land we beseech,
that God should guide them with a merciful right hand
and let them enter their home in safety and peace.
በእንተ ርኁባን ወጽሙዓን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
የሀቦሙ ሲሳዮሙ ዘለለዕለቱ፡
እግዚአብሔር የዕለት የዕለት ምግባቸውን ይሰጣቸው ዘንድ ፤
ስለ ተራቡና ስለ ተጠሙ ሰዎች እንማልዳለን።
For the hungry and the thirsty we beseech, that God
should grant them their daily food.
በእንተ ኅዙናን ወትኩዛን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
ይናዝዞሙ ፍጹመ።
እግዚአብሔር ፈጽሞ ያረጋጋቸው ዘንድ ፤ ስለ አዘኑና ስለ
ተከዙ ሰዎች እንማልዳለን።
For the sad and the sorrowful we beseech, that God
may give them perfect consolation
በእንተ ሙቁሓን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይፍትሖሙ
እማዕሠሪሆሙ።
እግዚአብሔር ከእሥራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ፤ ስለታሠሩ
ሰዎች እንማልዳለን።
For the prisoners we beseech, that God may loose
them from their bonds.
በእንተ ፂዉዋን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይሚጦሙ
በሰላም ውስተ ብሔሮሙ።
እግዚአብሔር በሰላም ወደ አገራቸው ይመልሳቸው ዘንድ ፤
ስለ ተማረኩ ሰዎች እንማልዳለን።
For the captives we beseech, that God may restore
them to their county in peace.
በእንተ ስዱዳን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀቦሙ
ትዕግሥተ ወትምህርተ ሠናየ ወይጸጉ ፃማሆሙ ፍጹመ።
እግዚአብሔር ትዕግሥትን ፤ በጎ ትምህርትንም ይሰጣቸው
ዘንድ ፤ የድካማቸውንም ፍጹም ዋጋ ይሰጣቸው ዘንድ ፤ ስለ
ተሰደዱ ሰዎች እንማልዳለን።
For those who were refugees we beseech, that God
may grant them patience and good instruction, and
give them complete reward for their labour.
በእንተ ሕሙማን ወድውያን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር
ፍጡነ ይፈውሶሙ ወይፈኑ ሣህለ ወምሕረተ ላዕሌሆሙ።
እግዚአብሔር ፈጥኖ ያድናቸው ዘንድ ፤ ይቅርታውንና
ቸርነቱንም ይልክላቸው ዘንድ ፤ ስለ ታመሙትና ስለ ድውያኑ
እንማልዳለን።
For the sick and the diseased we beseech, that God
should heal them speedily and send upon them mercy
and compassion.
በእንተ እለኖሙ እምቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናስተበቊዕ
ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ መካነ ዕረፍት።
ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወገን ስለ ሞቱ ሰዎች እግዚአብሔር
የዕረፍት ቦታ ይሰጣቸው ዘንድ እንማልዳለን።
For those who have fallen asleep in his holy church
we beseech, that God may vouchsafe them a place to
rest.
በእንተ እለ አበሱ አበዊነ ወአኀዊነ ናስተበቊዕ ከመ
እግዚአብሔር ኢይትቀየሞሙ ናኅየ ወሣኅተ የሀቦሙ እመዓቱ።
እግዚአብሔር እንዳይቀየማቸው ከመዓትም ተመልሶ ፍጹም
ዕረፍትን ይሰጣቸው ዘንድ ፤ ስለ በደሉ አባቶቻችንና
ወንድሞቻችን እንማልዳለን።
For those who have sinned, our fathers and our
brothers we beseech, that God cherish not anger
against them, but grant them rest and relief from His
wrath.
በእንተ ዝናማት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይፈኑ ዝናመ
ኀበ ዘይትፈቀድ መካን።
በሚሻበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ ፤ ስለ
ዝናም እንማልዳለን።
For the rains we beseech, that God may send rain on
the place that needs it.
በእንተ ማያተ አፍላግ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሐየር ይምላዕ
ኪያሆን እስከ መስፈርት ወዓቅም።
የወንዙን ውኃ ምላልን ብለን እግዚአብሔር እነሱን እስከ
ልካቸውና እስከ ወሰናቸው ይመላ ዘንድ ፤ ስለ ወንዝ ውኃ
እንማልዳለን።
For the water of the rivers we beseech, that God
should fill them unto their due measure and bounds.
በእንተ ፍሬ ምድር ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀባ
ፍሬሃ ለምድር ለዘርዕ ወለማዕረር።
ለዘርና ለመከር ሊሆን እግዚአብሔር ለምድር ፍሬዋን
ይሰጣት ዘንድ ፤ ስለ ምድር ፍሬ እንማልዳለን።
For the fruits of the earth we beseech, that God may
grant to the earth her fruit for sowing and for harvest.
ወለኵልነ እለ በጸሎት ንስእል ወናስተበቊዕ በመንፈሰ ሰላም
ይክድነነ ወይጸግወነ ወያብርህ አዕይንተ አልባቢነ።
በጸሎት የምንለምንና የምንማልድ ሁላችንን በሰላም በመንፈስ
ይጠብቀን። ፍቅርንም ይስጠን። ዓይነ ልቡናችንንም
ያብራልን።
And all of us who ask and beseech in prayer, may He
cover us with the spirit of peace, and give us grace,
and enlighten eyes of our hearts.
ንቅረብ ወንስአሎ ለእግዚአብሔር ከመ ተሠጢዎ ጸሎተነ
ይትወከፍ ፤ ንትነሣእ እንከ በመንፈስ ቅዱስ ከመ ለቢወነ
ንልሐቅ በጸጋሁ ወንትመካህ በስመ ዚአሁ።
ፈቃዱም ሆኖ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ ቀርበን
እግዚአብሔርን እንለምነው። አውቀን በኃብቱ እናድግ ዘንድ ፤
በእርሱም ስም እንመካ ዘንድ ፤
Let us draw high and ask God to accept our prayers
according to His will. Let us therefore rise in the Holy
Spirit, growing in His grace, with understanding, glorying
in His name
ወንትሐነጽ ዲበ መሠረተ ነቢያት ወሐዋርያት ንቅረብ
ወንስአሎ ለእግዚአብሔር አምላክነ ከመ ተሠጢዎ ጸሎተነ
ይትወከፍ።
በነቢያት በሐዋርያትም መሠረት ላይ እንታነጽ ዘንድ ፤
እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ እንነሣ። ቀርበን አምላካችንን
እግዚአብሔርን እንለምነው ወዶ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ።
and built upon the foundation of the prophets and the
apostles. Let us draw high and ask Lord God to
accept our prayers according to His will.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ንስግድ (፫ ጊዜ)
እንስገድ
Let us worship (to be repeated thrice)
ለአብ ፣ ወወልድ ፣ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ።
ሦስት ሲሆኑ አንድ ለሚሆኑ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ
ቅዱስም።
The Father and the Son and the Holy Spirit, three in
one.
ሰላም ለኪ።
ሰላም ላንቺ ይሁን።
Peace be unto You:
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅደረ መለኮት።
የመለኮት ማደሪያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን።
Holy church, dwelling-place of the Godhead.
ሰአሊ ለነ።
ለምኝልን።
Ask for us:
ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ።
አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም።
Virgin Mary, mother of God,
አንቲ ውእቱ።
አንቺ ነሽ።
You are:
ማዕጠንት ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት ቡሩክ ዘነሥአ
እመቅደስ።
ቡሩክ ከቤተ መቅደስ የተቀበላት የእሳትን ፍሕም የተሸከምሽ
የወርቅ ጥና አንቺ ነሽ።
The golden censer which did bear the coal of fire which
the blessed took from the sanctuary,
ዘይሠሪ ኃጢአተ ወይደመስስ ጌጋየ ፤ ዝውእቱ ዘእግዚአብሔር
ቃል ዘተሰብአ እምኔኪ ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ እጣነ
ወመሥዋዕተ ሥሙረ።
ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ፤ በደልንም የሚያጠፋ ይኸውም
ካንቺ ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
and which forgives sin and blots out error, who is
God's Word that was made man from You, who offered
Himself to His Father for incense and an acceptable
sacrifice.
ንሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስከ
ቅዱስ ማሕየዊ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ።
ክርስቶስ ሆይ ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባትህ ጋራ ፤ መድኃኒት
ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ እንሰግድልሃለን ፤ መጥተህ
አድነኸናልና።
We worship You, Christ, with Your good heavenly
Father and the Holy Spirit, the life-giver, for You did
come and save us.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ንፍቅ ካህን (Asst.Priest)
እግዚአ አእምሮ ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ ዘኮነ ሥውረ ውስተ
ማዕምቀ ጽልመት ወሃቤ ቃለ ትፍሥሕት ለእለ ይሰብኩ ዕበየ
ኃይልከ።
የዕውቀት ባለቤት ጥበብን የሚያናግር በጥልቅ ጨለማ ውስጥ
ተሠውሮ የነበረውን የገለጽክልን የኃይልህን ከፍታ ለሚሰብኩ
የደስታ ቃልን የምትሰጥ።
Lord of knowledge, declarer of wisdom, who have
revealed to us what was hidden in the depth of
darkness, giver of a word of gladness to them that
preach the greatness of Your power.
አንተ ውእቱ በብዙኅ ኂሩትከ ጸዋዕኮ ለጳውሎስ ዘኮነ ቀዲሙ
ሰዳዴ ወረይሰኮ ንዋየ ኅሩየ። ወበዝንቱ ሠመርኮ ከመ ይኩን
ሐዋርያ ወሰባኬ ወንጌል መንግሥትከ ጸዋዒ።
ቀድሞ ያሳድድ የነበረ ጳውሎስን በብዙ ቸርነትህ የጠራኸው
የተመረጠ ዕቃም ያደረግኸው አንተ ነህ። በዚህም ወደድኸው
ሐዋርያ ይሆን ዘንድ የምትጠራ የመንግሥትህንም ወንጌል
የሚያስተምር ይሆን ዘንድ።
It was You that, after Your great goodness, did call
Paul who was previously a persecutor, and did make
him a chosen vessel, and were will-pleased with him that
he should become a preacher of the Gospel of Your
kingdom which called him to be an apostle.
ኦ ክርስቶስ አምላክነ አንተ ውእቱ መፍቀሬ ሰብእ። ኦ ኄር
ጸግወነ ልቡና ዘእንበለ ግብር ወሕሊና ንጹሐ ዘኢይትአተት
እምኀቤከ።
አምላካችን ክርስቶስ ሆይ ሰውን የምትወድ አንተ ነህ። ቸር ሆይ
ያለ ሥራ ዕውቀትን ካንተ የማይለይ ንጹሕ ሕሊናን ስጠን።
O Christ our God. You are a lover of man. O Good,
vouchsafe us a mind without distraction and a pure
understanding that departs not from You,
ከመ ናእምር ወንለቡ ወንጠይቅ መጠነ ትምህርትከ ቅድስት
ዘተነበት በላዕሌነ ይእዜኒ እምኀቤሁ። ወበከመ ተመሰለ ብከ ኦ
ርእሰ ሕይወት ከማሁ ለነኒ ረስየነ ድልዋነ ንትመሰል ኪያሁ
በምግባር ወበሃይማኖት፤
ዛሬም ከርሱ ዘንድ በኛ ላይ የተነበበች ክብርት የምትሆን
የትምህርትን ልክ እናውቅ እናስተውል እንረዳ ዘንድ።
የሕይወት ራስ ሆይ አንተን እንደመሰለ እኛም እንደሱ በምግባር
በሃይማኖት እሱን እንመስል ዘንድ የበቃን አድርገን።
that we may both perceive and know how great is Your
Holy teaching which is now read to us out of him, And
as he imitated You, O Prince of life, so make us also
meet to imitate him in deed and in faith,
ወንሰብሕ ለስምከ ቅዱስ ወንትመካህ በክቡር መስቀልከ ኵሎ
ጊዜ፤ እስመ ለከ ይእቲ መንግሥት ወኃይል፤ ዕበይ ወሥልጣን
፤ ክብር ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
ቅዱስ ለሚሆን ለስምህ ምስጋና እናቀርብ ዘንድ ፤ ክቡር
በሚሆን በመስቀልህም እንመካ ዘንድ። መንግሥት ያንተ ናትና
ከሃሊነት ገናንነትና ሥልጣን ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ።
and to glorify Your Holy name and glory in Your
precious cross at all times: for Yours is the kingdom
and might, majesty and sovereignty, honour and glory,
world with out end.
ሕዝብ
አሜን
Amen
ካህናት (Priests) ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ።
ሕዝብ (People) ይደልዎሙ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
ካህናት (Priests) አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሥሉስ ዕሩይ
ኵሎ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
ሕዝብ (People) አሜን።
ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ሁልጊዜ
ክብር ምስጋና ይገባቸዋል ፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Glory and honor are meet to the Holy Trinity, the Father
and the Son and the Holy Spirit at all Both now and
ever and world without end. Amen.
ኵሉ ዘኢያፈቅሮ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ወዘኢየአምን ልደቶ እማርያም እምቅድስት ድንግል በ፪ኤ ታቦተ
መንፈስ ቅዱስ እስከ ምጽአቱ ሐዳስ በከመ ይቤ ጳውሎስ ውጉዝ
ለይኩን።
ጌታችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወደው
የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን
ከቅድስት ማርያም መወለዱን የማያምን ሰው ሁሉ እንግዳ
እስከሚሆን ምጽአቱ ድረስ ጳውሎስ እንደ ተናገረ የተለየ ይሁን።
Every one that loves not our Lord and our Saviour Jesus
Christ, and believes not in His birth from Holy Mary, of
twofold virginity, the ark of the Holy Spirit, until His
coming again, let him be anathema as Paul said.
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት
እየተነበበ ነው።
Reading the Epistle of St. Paul.
ዲያቆን(deacon)
በረከተ አብ ወፍተ ወልድ ወሀብተ መንፈስ ቅዱስ ዘወረደ
ላዕለ ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ቅድስት ከማሁ ይረድ
ወይትመከዐብ ላዕሌየ ወላዕለ ኵልክሙ።
ቅድስት በምትሆን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው
የአብ በረከት የወልድም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ሀብት
በሁላችሁም ላይ ይውረድ ዕፅፍ ድርብም ይሁን።
Holy Apostle The blessing of the Father and the lover of
the Son and the gift of the Holy Spirit who come down
upon the apostles in the upper room of holy Zion, in like
sort come down and be multiplied upon me and all of you.
ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሠናየ መልእክት ፈዋሴ ዱያን ዘነሣእከ
አክሊለ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ ያድኅን ነፍሳተነ በብዝኀ ሣህሉ
ወምሕረቱ በእንተ ስሙ ቅዱስ።
አክሊልን የተቀበልህ ፤ ድውያንን የምታድን ፤ መልእክትህ
የበጀ ፤ ክቡር የምትሆን ጳውሎስ ሆይ ፤ በይቅርታውና ቸርነቱ
ብዛት ስለቅዱስም ስሙ ሰውንታችንን ያድን ዘንድ ስለኛ ለምን
ጸልይም።
Holy Apostle Paul, good messenger, healer of the sick,
who have received the crown, ask and pray for us in
order that He may save our souls in the multitude of
His mercies and in His pity for His Holy name's sake.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ኦ አምላክ ዘለዓለም ቀዳሚ ወደኃሪ ዘአልብከ ጥንት
ወኢተፍጻሜት ዘዐቢይ በተኬንዎቱ ፤ ወኃያል በምግባሩ ፤
ወጠቢብ በምክሩ ፤ ወጽኑዕ በኃይሉ ፤ ዘህልው ውስተ ኵሉ።
የዘላለም አምላክ ሆይ ቀዳማዊ ደኃራዊ የምትሆን ጥንትም
ፍጻሜም የሌለህ። በመፍጠሩ ገናና የሚሆን ፤ በሥራውም ኃያል
የሚሆን በምክሩም ዐዋቂ ፤ በኃይሉም ጽኑ የሚሆን በሁሉ አድሮ
O eternal God, the first and the last, who has neither
beginning nor end, He that is great in his construction
and mighty in his work and wise in his counsel and firm
ንስእለከ እግዚኦ ወናስተበቊዐከ ከመ ተሀሉ ምስሌነ በዛቲ ሰዓት
አርኢ ገጸከ ላዕሌነ ወንበር ምስሌነ በማእከሌነ። ወአንጽሕ
አልባበነ ወቀድስ ነፍስተነ ወሥረይ ኃጢአተነ
የሚኖር። በዚች ሰዓት ከኛ ጋራ ትሆን ዘንድ እንለምንሃለን
እንማልድሃለንም። ለኛ ፊትህን ግለጽልን። ከኛም ጋራ
በመካከላችን ኑር። ልቦናችንንም አንጻ ሰውነታችንንም አክብር፤
in His power, who exists in all: We pray You and
beseech You to be with us in this hour: make Your
face to shine upon us, and abide with us in the midst
of us: And purify our hearts, and sanctify our souls, and
remit our sins,
ዘገበርነ በፈቃድነ ወዘእንበለ ፈቃደከ ረስየነ እግዚኦ ናቅርብ
ኀቤከ መሥዋዕተ ንጹሐ ወቊርባነ ነባቤ ወዕጣነ መንፈሳዌ
ይባእ ውስተ ጽርሐ ቅዱስ ቅዱሳቲከ በዋሕድ ወልድከ
ያለፈቃድህ በፈቃዳችን የሠራነውንም ኃጢአታችንን
አስተሥርይ። ንጹሑን መሥዋዕት ነባቢውን ቊርባንና
መንፈሳዊውን ዕጣን አቤቱ ወዳንተ እንድናቀርብ አድርገን።
ወደ ልዩ ምስጋናህ አዳራሽ ይገባ ዘንድ፤
which we have done with our will against Your will:
make us, Lord, to offer unto You a pure sacrifice, a
reasonable offering and a spiritual incense: let it enter
into the Holy temple of Your Holiness:
እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወወምስለ ቅዱስ
መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
በአንድ ልጅህ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ።
through Your only-begotten Son, Our Lord Jesus Christ,
and through the Holy Spirit.
ዲያቆን ንፍቅ (Asst.Deacon)
ነገር ዘእመልእክተ…….. ረድኡ ወሐዋርያሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስለ ኵልነ ሕዝበ ክርስቲያን
ለዓለመ ዓለም አሜን።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ረድኡ ከሚሆን……….
መልእክት የተገኘ ቃል ይህ ነው። ጸሎቱና በረከቱ በሁላችን
ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ይኑር ለዘlለዓለሙ አሜን።
The word from the Epistle of …….. disciple and apostle
of our Lord Jesus Christ. His prayer and blessing be
with us all for ever. Amen.
፪ኛ መልእክት እየተነበበ ነው።
Reading the 2nd Epistle.
ዲያቆን ንፍቅ (Assistant Deacon)
ኦ አኃውየ ኢታፍቅርዎ ለዓለም ወኢዘሀሎ ውስተ ዓለም።
ዓለሙኒ ኃላፊ ፍትወቱኒ ኀላፊ እስመ ኵሉ ኀላፊ ውእቱ።
ወንድሞቼ ይህን ዓለም አትውደዱት በዓለሙ ውስጥ
ያለውንም። ዓለሙም አላፊ ነው፤ ፈቃዱም አላፊ ነው፤
ሁሉም አላፊ ነውና።
O my brothers, love not the world neither the
things that are in the world. The world passes away
and the lust thereof, for all is passing.
ቅዱስ ሥሉስ ዘኅቡር ህላዌከ ዕቀብ ማኅበረነ በእንተ ቅዱሳን
ኅሩያን አርዳኢከ ናዝዘነ በሣህልከ በእንተ ቅዱስ ስምከ።
ባሕርይህ አንድ የሚሆን ልዩ ሦስት ሆይ አንድነታችንን ጠብቅ
፤ ስለተመረጡ ክቡራን ደቀ መዛሙርትህ በይቅርታህ አጽናን
ክቡር ስለሚሆን ስለ ስምህ ብለህ።
Holy consubstantial Trinity, preserve our congregation
for Your Holy elect disciples' sake: comfort us in the
mercy, for Your Holy name's sake.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
እግዚእነ ወአምላክነ አንተ ውእቱ ለሐዋርያቲከ ቅዱሳን ከሠትከ
ሎሙ ምሥጢረ ስብሐተ ወንጌለ መሢሕከ ፤ ወወሀብኮሙ ዐቢየ
ሀብተ እንተ አልባቲ ኊልቊ።
ጌታችን አምላካችን ሆይ የመሢህን የወንጌል ክብር ምሥጢር
ቅዱሳን ለሚሆኑ ለሐዋርያት የገለጽህላቸው አንተ ነህ። ከቸርነትህ
የምትሆን ስፍር ቊጥር የሌላት ደገኛ ሀብትንም የሰጠሃቸው፡፡
Our Lord and Our God, it was You did reveal to Your
Holy apostles the mystery of the glorious of Your
Messiah, and did give them the great and immeasurable
gift that is of Your grace,
እንተ ይእቲ እምጸጋከ ወፈነውኮሙ ይስብኩ ውስተ ኵሉ
አጽናፈ ዓለም ብዕለ ጸጋከ ዘኢይትዐወቅ ምሕረትከ። ወንሕነኒ
እግዚኦ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ ከመ ትረስየነ ድልዋነ
ለርስቶሙ ወለመክፈልቶሙ ፤
ይህችውም ከቸርነትህ የተገኘች ናት። የማይታወቅ የቸርነትህን
ብዛት በዓለሙ ሁሉ ዳርቻ ያስተምሩ ዘንድ የሰደድሃቸው
አቤቱ እኛም ለዕድላቸውና ለእርስታቸው የበቃን ታደርገን
ዘንድ እንለምንሃለን እንማልድሃለን።
and did send them to proclaim to all the ends of the
world the unsearchable riches of Your grace which is of
the mercy: We pray You also and beseech You,
ንሑር በፍናዊሆሙ ወንትሉ በዐሠሮሙ ወጸግወነ በኵሉ ጊዜ
ንትመሰል ኪያሆሙ ፤ ወንጽናዕ በፍቅሮሙ ወንኩን ክፍለ
ምስሌሆሙ በውስተ ፃማሆሙ በሠናይ አምልኮ።
በመንገዳቸው እንሄድ ዘንድ ፍለጋቸውንም እንከተል ዘንድ
ሁልጊዜም እነርሱን እንመስል ዘንድ መምሰሉን ስጠን።
በፍቅራቸው እንጸና ዘንድ ባማረ አምልኮ በድካማቸው ከሳቸው
ጋራ የታደልን እንሆን ዘንድ መሆኑን ስጠን።
O Lord that You would make us meet for an inheritance
and a portion with them that we may walk in their ways
and follow in their footsteps: and vouchsafe us at all
times to imitate them and to continue in their love and to
have fellowship with them in their labour in true godliness.
ወዕቀባ ለቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት እንተ ሣረርካ በእንቲአሆሙ።
ወባርክ ላዕለ አባግዐ መርዔትከ። ወአብዝኃ ለዛቲ ዐፀደ ወይን
እንተ ተከልካ በየማንከ ቅዱስ።
ስለነሱ የሠራሃትን ቤተ ክርስቲያንንም ጠብቃት። የመንጋህንም
በጎች ባርክ። ጽኑ በሚሆን ቀኝህ የተከልካት ይህችንም የወይን
ቦታ (ቀንድ) ባርክ።
And do You keep Your Holy church which You did
found by their means and bless the sheep of Your flock
and increase the vine which You did plant with Your Holy
right hand:
በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ
ቅዱስ መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ
ዓለም አሜን።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ
ምስጋና ጽንዕ ያለህ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
through Jesus Christ our Lord, through whom to You
with Him and with the Holy Spirit be glory and dominion,
both now and ever and world without end. Amen.
ንፍቅ ካህን (Asst.Priest)
ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ ንጹሐን ዝውእቱ ዜና ግብሮሙ
ለሐዋርያት በረከተ ጸሎቶሙ የሀሉ ምስለ ኵልነ ሕዝበ
ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን።
ንጹሐን ከሚሆኑ ከሕግ ምንጮች የተገኘ ጥሩ ምንጭ ይኸውም
የሐዋርያት የሥራቸው ነገር ነው። የጸሎታቸው በረከት ከሁላችን
ጋራ ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
A pure fountain which is from the pure fountains of the
law, to wit the history of the acts of the apostles. The
blessing of their prayer be with us all forever. Amen.
የሐዋርያት ሥራ እየተነበበ ነው።
Reading the Acts of the Apostles.
መልዐ ወዐብየ ወተለዓለ ቃለ እግዚአብሔር ወበዝኀ ወተወሰከ
ውስተ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት። ወበዝኁ ሕዝብ እለ አምኑ
በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሎቱ ስብሐት ለዓለመ ዓለም
አሜን።
የእግዚአብሔር ቃል ፈጽሞ መላ። ከፍ ከፍ አለ። በቅድስት
ቤተ ክርስቲያንም በዝቶ ተጨመረ ፤ ምስጋና ገንዘቡ በሚሆን
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑት ሕዝብም በዙ፤
ለዘለዓለሙ አሜን።
Full and great and exalted is the Word of God, and it
has increased in the Holy church, and many are they that
believe in our Lord Jesus Christ to whom be glory, world
without end. Amen.
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ አምላከ አብ አኃዜ ኵሉ። ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ አንተ ወልድ ዋሕድ ዘአንተ ቃለ አብ ሕያው።
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ መንፈስ ቅዱስ ዘተአምር ኵሎ።
ሁሉን የያዝህ አብ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ነህ። ሕያው
የአብ ቃል የምትሆን ወልድ ዋሕድ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
አንተ ነህ። ሁሉን የምታውቅ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ አንተ ነህ።
Holy Holy Holy are You, Father Almighty. Holy Holy Holy
are You, only-begotten who are the Word of the living
Father. Holy Holy Holy are You, Holy Sprit who knows
all things.
እግዚአብሔር አምላክነ ዘተወከፍከ መሥዋዕተ አቡነ
አብርሃም ወህየንተ ይስሐቅ ወልዱ ዘአስተዳሎከ ወአውረድከ
ሎቱ ቤዛሁ በግዐ ከማሁ ተወከፍ እግዚኦ መሥዋዕተነ
የአባታችን የአብርሃምን መሥዋዕት የተቀበልክ አምላካችን
እግዚአብሔር ስለ ልጁ ስለ ይስሐቅም ፈንታ ቤዛ ሊሆነው
በጉን አዘጋጅተህ ያወረድህለት፤
Lord our God, who did accept the sacrifice of our
father Abraham, and instead of Isaac his son did
prepare and send down to him a ram for his ransom
ወመዓዛ ዝንቱ ዕጣንነ ወፈኑ ለነ ህየንቴሁ እምላዕሉ ብዕለ
ሣህልከ ወምሕረትከ ከመ ንኩን ንጹሓነ እምኵሉ ጼና ፂዓተ
ኃጣውኢነ።
አቤቱ እንዲሁ መሥዋዕታችንና የዚህን የዕጣናችንን መዓዛ
ተቀበል። በርሱም ፈንታ የይቅርታህንና የቸርነትህን ብዛት ከላይ
ላክልን። ከክፉ ኃጢአታችን ሽታ ሁሉ ንጹሓን እንሆን ዘንድ።
even so, O Lord, accept our sacrifice and the savior
of this our incense, and send unto us from on high
in recompense thereof the riches of Your mercy and
Your compassion, so that we may become pure from all
taint of our sins.
ወረስየነ ድልዋነ ከመ ንትለአክ ቅድመ ውዳሴ ንጽሕከ ኦ
መፍቀሬ ሰብእ በጽድቅ ወበንጽሕ በኵሉ መዋዕለ ሕይወትነ
በትፍሥሕት ወበኀሤት።
ሰውን የምትወድ ሆይ በንጽሕናህ ምስጋና ፊት እናገለግል
ዘንድ የበቃን አድርገን ፤ በሕይወታችን ዘመን ሁሉ በእውነትና
በንጽሕና በደስታና በኀሤት።
And make us, O Lover of man, meet to minister
before Your glorious purity in righteousness and in
purity all the days of our life, in joy and in rejoicing.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ
ሐዋርያት ርትዕት በኀበ እግዚአብሔር።
ሐዋርያት ስለሰበሰቧት በእግዚአብሔር ዘንድ ስለቀናች ፤
ክብርት ስለምትሆን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ።
Pray for the peace of the one Holy apostolic church
orthodox in the Lord.
አሜን ኪርያላይሶን እግዚኦ ተሣሃለነ።
አሜን ኪርያላይሶን ጌታ ሆይ ይቅር በለን።
Amen, Kyrie eleision, Lord have mercy upon us.”
ጸልዩ በእንተ ሊቀ ጳጳስነ አባ …....ወብፁዕ ጳጳስነ አባ….....
ወኵሎሙ ኤጲስ ቆጶሳት ፣ ቀሳውስት ወዲያቆናት ወኵሎሙ
ሕዝበ ክርስቲያን ርቱዓነ ሃይማኖት።
ስለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳችን ስለ አባ ………. ስለ ብፁዕ ሊቀ
ጳጳሳችን አባ …......ስለ ኤጲስ ቆጶሳቱም ሁሉ ስለ ቀሳውስትና
ስለ ዲያቆናም ፤ ሃይማኖታቸው ስለቀና ስለ ክርስቲያን ወገኖች
ሁሉ ጸልዩ።
Pray for our Patriarch Abba... and for our Archbishop
Abba ...... bishops, and all the bishops, priest, deacons
and all the all the Orthodox Christians.
አሜን ኪርያላይሶን እግዚኦ ተሣሃለነ።
አሜን ኪርያላይሶን ጌታ ሆይ ይቅር በለን።
Amen, Kyrie eleison, Lord have mercy upon us.”
ጸልዩ በእንተ ማኅበርነ ወዕቅበተ ለኵልነ።
ስለ አንድነታችን ለሁላችን መጠበቅ ጸልዩ።
Pray for our congregation and for keeping of us all.
አሜን ኪርያላይሶን እግዚኦ ተሣሃለነ።
አሜን ኪርያላይሶን ጌታ ሆይ ይቅር በለን።
Amen, Kyrie eleison, Lord have mercy upon us.”
ተፈሣሒ ኦ ዘንስእለኪ ዳኅና ኦ ቅድስት ምልዕተ ክብር
ድንግል።
ደኅንነትን የምንለምንሽ ክብርን የተሞላሽ ቅድስት ሆይ ደስ
ይበልሽ።
Rejoice, O You of whom we ask healing, O Holy full of
honor ever Virgin.
ተፈሥሒ።
ደስ ይበልሽ።
Rejoice.
በኵሉ ጊዜ ወላዲተ አምላክ እሙ ለክርስቶስ አዕርጊ
ጸሎተነ ዲበ መልዕልት ኀበ ፍቁር ወልድኪ ከመ ይሥረይ
ለነ ኃጣውኢነ።
ሁልጊዜ ድንግል የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ የክርስቶስ
እናት ሆይ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ
ወደ ወዳጅሽ ወደ ላይ ጸሎታችንን አሳርጊ።
Ever-Virgin, parent of God, mother of Christ, offer up
our prayer on high to Your beloved Son that He may
forgive us our sin.
አሜን።
Amen.
ተፈሥሒ ኦ ዘወለድኪ ብርሃነ ጽድቅ ዘበአማን ክርስቶስሃ
አምላክነ።
በእውነት የጽድቅ ብርሃን የሚሆን አምላካችንን ክርስቶስን
የወለድሽልን ንጽሕት ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ።
Rejoice, O You who did bear for us the very light of
righteousness, even Christ our God.
ተፈሥሒ።
ደስ ይበልሽ።
Rejoice
ኦ ድንግል ንጽሕት ሰአሊ ለነ ኀበ እግዚእነ ከመ ይግበር
ምሕረተ ለነፍሳቲነ ወይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ንጽሕት ድንግል ሆይ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግ ዘንድ ፤
ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ጌታችን
ለምኝልን።
O Virgin pure, plead for us unto our Lord that He may
have mercy upon our souls and forgive us our sins.
አሜን።
Amen.
ተፈሥሒ ኦ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ቅድስት
ወንጽሕት ሰአሊት በአማን በእንተ ዘመደ እጓለ እምሕያው።
በእውነት ለሰው ወገን አማላጅ የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ
ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ።
Rejoice, O Virgin Mary, parent of God, Holy and pure,
very pleader for the race of mankind.
ተፈሥሒ።
ደስ ይበልሽ።
Rejoice
ሰአሊ ለነ ቅድመ ክርስቶስ ወልድኪ ከመ ይጸግወነ ሥርየተ
ኃጣውኢነ።
የኃጢያታችንን ሥርየት ይሰጠን ዘንድ በልጅሽ በክርስቶስ
ፊት ለምኝልን።
Plead for us before Christ Your Son, that He may
vouchsafe us remission of our sins.
አሜን ።
Amen
ተፈሥሒ ኦ ድንግል ንጽሕት ዘበአማን ንግሥት።
በእውነት ንግሥት የምትሆኝ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ
ይበልሽ።
Rejoice, O Virgin pure, very Queen.
ተፈሥሒ።
ደስ ይበልሽ።
Rejoice
ተፈሥሒ ኦ ምክሐ ዘመድነ።
የባሕሪያችን መመኪያ ሆይ ደስ ይበልሽ።
Rejoice, O pride of our kind.
ተፈሥሒ።
ደስ ይበልሽ።
Rejoice
ተፈሥሒ ኦ ዘወልድኪ ለነ አማኑኤልሃ አምላክነ።
አምላካችን አማኑኤልን የወለድሽልን ሆይ ደስ ይበልሽ።
Rejoice, O You that bare for us Emmanuel our God.
ተፈሥሒ።
ደስ ይበልሽ።
Rejoice
ንስእለኪ ከመ ትዘከርነ አራቂተ ዘበአማን ቅድመ እግዚእነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይግበር ምሕረተ ለነፍሳቲነ ወይሥረይ
ለነ ኃጣውኢነ።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እውነተኛ አስታራቂ ሆነሽ
ታስቢን ዘንድ እንለምንሻለን ፤ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግልን
ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ።
We ask You to remember us, O true Mediator, before
our Lord Jesus Christ that He may have mercy upon our
souls and forgive us our sins.
ካህናት (Priests)
ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት ወዝ ውእቱ ጊዜ ዕጣን ኅሩይ ጊዜ
ሰብሖቱ ለመድኃኒነ መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ።
የማመስገን ጊዜ ይህ ነው። የተመረጠ የዕጣን ጊዜም ይህ ነው።
ሰው ወዳጅ መድኃኒታችንን ክርስቶስን ማመስገኛ ነው።
This is the time of blessing; this is the time of chosen
incense, the time of the praise of our Savior, lover of
man, Christ.
ዕጣን ይእቲ ማርያም ፤ ዕጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሣ
ዘይትሜዐዝ እምኵሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽአ ወአድኀነነ።
ማርያም ዕጣን ናት። ዕጣን እርሱ ነው ፤ በማኅጸንዋ ያደረው
ከተመረጠ ዕጣን ሁሉ የሚሸት ነውና። የወለደችው መጥቶ
አዳነን።
Mary is the incense, and the incense is He, because
He who was in her womb is more fragrant than all
chosen incense. He whom she bare came and saved
us.
ካህናት (Priests)
ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ንዑ ንስግድ ሎቱ ወንዕቀብ
ትእዛዛቲሁ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ኢየሱስ ክርስቶስ መዓዛ ያለው ሽቱ ነው። ኑ እንስገድለት ፤
ትእዛዞቹንም እንጠብቅ ፤ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ።
The fragrant ointment is Jesus Chris. O come let us
worship Him and keep His commandments that He
may forgive us our sins.
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ፤ ወብሥራት ለገብርኤል ፤
ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
ለሚካኤል ምሕረት ተሰጠው። ለገብርኤልም ማብሠር ፤
ለድንግል ማርያምም ወደ መንግሥተ ሰማያት የምትገባበት
ሀብት ተሰጣት።
To Michael was given mercy, and glad tidings to
Gabriel, and a heavenly gift to the Virgin Mary.
ካህናት (Priests)
ተውህቦ ልቡና ለዳዊት ፤ ወጥበብ ለሰሎሞን ፤ ወቀርነ ቅብዕ
ለሳሙኤል እስመ ውእቱ ዘይቀብዕ ነገሥተ።
ለዳዊት ልቡና ፤ ለሰሎሞን ጥበብ ፤ ለሳሙኤልም ነገሥታቱን
የቀባ እርሱ ነውና የሽቱ ቀንድ ተሰጠው።
To David was given understanding, and wisdom to
Solomon, and an horn of oil to Samuel for he was the
anointer of kings.
ተውህቦ መራኁት ለአቡነ ጴጥሮስ ፤ ወድንግልና ለዮሐንስ ፤
ወመልእክት ለአቡነ ጳውሎስ እስመ ውእቱ ብርሃና ለቤተ
ክርስቲያን።
ለአባታችን ለጴጥሮስ መክፈቻ ፤ ለዮሐንስም ድንግልና ፤
ለአባታችን ለጳውሎስም የቤተ ክርስቲያን ብርሃኗ እርሱ ነውና
መልእክት ተሰጠው።
To our father Peter were given the keys, and virginity to
John, and apostleship to our father Paul, for he was the
light of the church.
ካህናት (Priests)
ዕፍረት ምዕዝት ይእቲ ማርያም ፤ እስመ ዘውስተ ከርሣ
ዘይትሌዐል እምኵሉ ዕጣን መጽአ ወተሠገወ እምኔሃ።
መዓዛ ያላት ሽቱ ማርያም ናት። በማኅጸንዋ ያለው ከዕጣን
ሁሉ የሚበልጥ ነውና መጥቶ ከእርስዋ ሰው ሆነ።
The fragrant ointment is Mary, for He that was in Her
womb, who is more fragrant than all incense, came and
was incarnate of her.
ለማርያም ድንግል ንጽሕት ሠምራ ፤ አብ ወአሠርገዋ ደብተራ
ለማኅደረ ፍቁር ወልዱ።
ንጽሕት ድንግል ማርያምን አብ ወደዳት ፤ ለተወደደ ልጁ
ማደሪያ ልትሆን በንጽሕና አስጌጣት።
In Mary virgin pure the Father was well-pleased, and He
decked her to be a tabernacle for the habitation of his
beloved Son.
ካህናት (Priests)
ተውህቦ ሕግ ለሙሴ ፤ ወክህነት ለአሮን ፤ ተውህቦ ዕጣን
ኅሩይ ለዘካርያስ ካህን።
ለሙሴ ሕግ ፤ ለአሮን ክህነት ተሰጠው ፤ ለካህኑ ዘካርያስም
የተመረጠ ዕጣን ተሰጠው።
To Moses was given the law, and priesthood to Aaron.
To Zacharias the priest was given chosen incense.
ደብተራ ስምዕ ገብርዋ። በከመ ነገረ እግዚእ ወአሮን ካህን
በማእከላ የዐርግ ዕጣነ ኅሩየ።
የምስክር ድንኳን አደረጓት። ጌታ እንደ ተናገረ ካህኑ አሮን
በመካከሏ የተመረጠውን ዕጣን ያሳርጋል።
They made a tabernacle of testimony according to the
word of God; and Aaron the priest, in the midst thereof
made the chosen incense to go up.
ካህናት (Priests)
ሱራፌል ይሰግዱ ሎቱ ፤ ወኪሩቤል ይሴብሕዎ ይጸርሑ እንዘ
ይብሉ።
ሱራፌል ይሰግዱለታል ፤ ኪሩቤልም ያመሰግኑታል። እንዲህም
እያሉ እየጠሩት።
The Seraphim worship Him, and Cherubim praise Him
and cry saying:
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር በኀበ አእላፍ ወክቡር በውስተ
ረበዋት። አንተ ውእቱ ዕጣን ኦ መድኃኒነ እስመ መጻእከ
ወአድኃንከነ ተሣሃለነ።
እግዚአብሔር በአእላፍ መላእክት ዘንድ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ነው እያሉ ይጮሃሉ። በአለቆችም ዘንድ ክቡር ነው።
መድኃኒታችን ሆይ ዕጣን አንተ ነህ መጥተህ አድነኸናልና ፤
ይቅር በለን።
Holy Holy Holy is the Lord among the thousands and
honored among the tens of thousands. You are the
incense, O our savior, for You did come and save us.
Have mercy upon us.
ቅዱስ።
Holy
እግዚአብሔር ፤ ቅዱስ ኃያል ፤ ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
፤ ዘተወልደ እምማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ
እግዚኦ።
እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት ፤
ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ ፤ አቤቱ ይቅር በለን።
God, Holy Mighty, Holy Living Immortal, who was born
from the Holy Virgin Mary, have mercy upon us, Lord.
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ፤ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ
ተሣሃለ እግዚኦ።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት ፤
በዮርዳኖስ የተጠመቀ ፤ በቅዱስ መስቀል ላይ የተሰቀለ አቤቱ
ይቅር በለን።
Holy God, Holy Mighty, Holy Living, Immortal, who was
baptized in Jordan and crucified on the tree of the cross,
have mercy upon us, Lord.
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት
በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ።
Holy God, Holy Mighty, Holy Living Immortal, who did
rise from the dead on the third day,
ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ፤ ዳግመ
ይመጽእ በስብሐት ይኮንን ሕያዋነ ወሙታነ ፤ ተሣሃለነ
እግዚኦ።
በምስጋና ወደ ሰማይ ወጣ ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ፤
ዳግመኛም በክብር ይመጣል ፤ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ
ዘንድ አቤቱ ይቅር በለን።
ascend into heaven in glory, sit at the right hand of
the Father and again wilt come in glory to judge the
quick and the dead, have mercy upon us, Lord.
ስብሐት ለአብ ፤ ስብሐት ለወልድ ፤ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን
ለይኩን።
ለአብ ምስጋና ይሁን ፤ ለወልድም ምስጋና ይሁን ፤ ለመንፈስ
ቅዱስ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ፤
አሜን ይሁን ይሁን።
Glory be to the Father, glory be to the Son, glory
be to the Holy Spirit, both now and ever and world
without end. Amen and Amen, so be it, so be it.
ቅዱስ ሥሉስ እግዚአብሔር ሕያው ተሣሃለነ።
ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን።
O Holy Trinity, living God have mercy upon us.
ፀጋ ዘእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።
The grace of God be with you.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit..
ንሰብሖ ለአምላክነ።
ፈጣሪያችንን እናመስግን።
Let us glory our God.
ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባል።
It is right, it is just.
አጽንዑ ሕሊና ልብክሙ።
የልባችሁን አሳብ አጽኑ።
Strengthen the thought of your heart.
ብነ ኀበ እግዚአብሔር አቡነ ዘበሰማያት አቡነ ዘበሰማያት ፤
አቡነ ዘበሰማያት ፤ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
ከእግዚአብሔር ዘንድ አለን። አባታችን ሆይ ፤ አባታችን ሆይ
፤ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
We lift them unto the Lord our God. Our Father who
are in heaven, Our Father who are in heaven, Our
Father who are in heaven, lead us not into temptation.
ሕዝብ (People) ጧት (in the morning)
ኪያከ ንሴብሕ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግንሃለን።
Oh, we thank You.
ሕዝብ (People) ከሰዓት በኋላ (in the afternoon)
ንሴብሐከ እግዚኦ።
አቤቱ እናመሰግንሃለን።
Oh, we thank You.
ኪያከ ንዌድስ እግዚኦ። ጧት (in the morning)
አቤቱ አንተን እናገንሃለን።
Oh Lord, we praise You.
ሕዝብ (People) ከሰዓት በኋላ (in the afternoon)
ንዌድሰከ እግዚኦ።
አቤቱ እናገንሃለን።
Oh Lord, we praise You.
ካህን (Priest) ጧዋት (in the morning)
….እስመ ለከ እግዚኦ አምላክነ መንግሥት ቡሩክ።
….አቤቱ አምላካችን ክቡር መንግሥት ያትንተ ነውና።
….for Yours is the blessed kingdom, O Lord our God.
ካህን (Priest) ከሰዓት በኋላ (in the afternoon)
……በእንቲአከ ወበእንተ ፍቁር ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ
ዘቦቱ ለከ ስብሐት ወእኂዝ ለዓለመ ዓለም።
……ልጅህ ወዳጅህ ጌታችን ኢየሱስም ስለገለጸልን ምስጋና
ጽንዕ ያለው ለዘላለሙ።
…..Your beloved Son, our Lord Jesus, through whom
be glory and dominion to You, world without end.
አሜን
Amen
ቡራኬ
Benediction
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ። ትምጻእ መንግሥትከ።
ወይኩን ፈቃድከ። በከመ በሰማይ ፤ ከማሁ በምድር።
አባታችን ሆይ ፤ በሰማያት የምትኖር ፤ ስምህ ይቀደስ ፤
መንግሥትህ ትምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም
በምድር ትሁን።
Our Father who are in heaven, hallowed be Your name,
Your kingdom come, Your will be done on earth as it is
in heaven;
ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ፤
ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ።
የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ። በደላችንን ይቅር በለን ፤
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል።
give us this day our daily bread, and forgive us our
trespasses as we forgive them that trespass against us,
ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት ፤ አላ አድኅነነ። ወባልሐነ
እምኵሉ እኩይ። እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል
ወስብሐት ለዓለመ ዓለም አሜን።
አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ፤ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጅ።
መንግሥት ያንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋናም ለዘላለሙ
አሜን።
and lead us not into temptation but deliver us and
rescue us from all evil; for Yours is the kingdom, the
power and the glory for ever and ever.
በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዚእትየ ማርያም ሰላም
ለኪ። ድንግል በሕሊናኪ ፣ ኦ ድንግል በሥጋኪ። እመ
እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ
ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን። በኃሳብሽ ድንግል ነሽ።
በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናቱ ሆይ
ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል።
Our Lady, Virgin St. Mary! In St. Gabriel's greetings,
peace be unto you. You are Virgin in thought and Virgin in
body, O mother of the almighty God! Peace be unto You.
ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርስኪ። ተፈሥሒ
ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ።
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ። የማኅፀንሽም
ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበለሽ ፤ ልዑል
እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና።
Blessed are You amongst women and blessed is the
fruit of Your womb. Hail Mary, full of Grace, the Lord is
with You,
ሰአሊ ወጸልዪ በእንቲአነ ምሕረት ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ
ክርስቶስ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ አሜን።
ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ
ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኚልን
ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።
Beseech and pray for us for our mercy to Your beloved
Son our Lord Jesus Christ that He may forgive us our
sins. Amen.
ኦ ሥሉስ ቅዱስ መሐረነ።
ኦ ሥሉስ ቅዱስ መሐከነ።
ኦ ሥሉስ ቅዱስ ተሣሀለነ።
ልዩ ሦስት ሆይ ማረን ።
ልዩ ሦስት ሆይ ራራልን።
ልዩ ሦስት ሆይ ይቅር በለን።
O Holy Trinity, Pity us,
O Holy Trinity, Spare us,
O Holy Trinity, have mercy upon us.
ቦአ መልአክ ኀቤሃ ወቆመ ቅድሜሃ ወይቤላ ለድንግል ተፈሥሒ
ተፈሥሒ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ድንግል ምልዕተ ጸጋ ።
መልአክ ወደርሷ ገብቶ ፤ በፊቷ ቆሞ ፤ ድንግልን ጸጋን
የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ፤ ደስ ይበልሽ፤ ደስ ይበልሽ አላት።
The angel went in unto Her and stood in front of Her
and said to Virgin : Rejoice, rejoice, rejoice, You that are
full of grace.
.
እግዚአብሔር ምስሌኪ።
እግዚአብሔር ካንቺ ጋራ ነው።
The Lord is with You.
ቡርክት አንቲ እም አንስት።
ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ።
Blessed are You among women:
ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ።
የማኅጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
And blessed is the fruit of Your womb.
ተንብሊ ወሰአሊ።
ለምኝልን አማልጂንም።
Pray for us
ኀበ ፍቁር ወልድኪ።
ከተወደደው ከልጅሽ ዘንድ።
To Your Son.
ኢየሱስ ክርስቶስ
ኢየሱስ ክርስቶስ
Jesus Christ
ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ።
To forgive us our sins.
ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ። ይደልዎሙ ለአብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ። አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኵሉ
ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
ልዩ ሦስት ለሚሆን ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም
ሁልጊዜ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል ፤ ዛሬም ዘወትርም
ለዘለዓለሙ ፤ አሜን።
Glory and honor are meet to the Holy Trinity, the Father
and the Son and the Holy Spirit at all times, both now
and ever and world without end. Amen
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
እግዚአብሔር እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነ ዘትቤሎሙ
ለአርዳኢከ ቅዱሳን ወለሐዋርያቲከ ንጹሓን። እስመ ብዙኃን
ነቢያት ወጻድቃን ፈተዉ ይርአዩ ፤
አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ቅዱሳን
የሚሆኑ ደቀመዛሙርትህንና ንጹሐን ሐዋርያትን እንዲህ
ያልሃቸው “እናንተ የምታዩትን ያዩ ዘንድ ብዙ ነቢያት ፣
ጻድቃን ወደዱ ፤
O Lord Jesus Christ, our God, who did say to Your Holy
disciples and Your pure apostles: Many prophets and
righteous men have desired to see the things which You
አንትሙ ዘትሬእዩ ወኢርእዩ ፤ ወፈተዉ ይስምዑ አንትሙ
ዘትሰምዑ ወኢሰምዑ። ወለክሙሰ ብፁዓት አይንቲክሙ እለ
ርእያ ወአእዛኒክሙ እለ ሰምዓ።
አላዩም። እናንተ ዛሬ የምትሰሙትን ይሰሙ ዘንድ ወደዱ ፤
አልሰሙም። የእናንተ ያዩ ዓይኖቻችሁና የሰሙ ጆሮቻችሁ ግን
የተመሰገኑ ናቸው።
and have desired to hear the things which you hear and
have not heard them, but you, blessed are your eyes
that have seen and your ears that have heard,
ወከማሆሙ ለነኒ ረስየነ ድልዋነ ንስማዕ ወንግበር ቃለ ወንጌልከ
ቅዱስ በጸሎቶሙ ለቅዱሳን።
እኛንም እንደነሱ የበቃን አድርገን። በቅዱሳን ጸሎት የከበረ
ወንጌልን ሰምተን እንሠራ ዘንድ።
Do you make us also like them meet to hear and to do
the word of Your Holy Gospel through the prayer of the
saints.
ጸልዩ በእንተ ወንጌል ቅዱስ።
ክቡር ስለሚሆን ስለ ወንጌል ጸልዩ።
Pray for the Holy Gospel.
ይረስየነ ድልዋነ ለሰሚዐ ወንጌል ቅዱስ።
ቅዱስ ወንጌልን ለመስማት የበቃን ያድርገን።
May He make us meet to hear the Holy Gospel.
ተዘከር ካዕበ እግዚኦ እለ አውሥኡነ ከመ ንዘከሮሙ ጊዜ
ጸሎትነ ወአስተበቊዖትነ እንተ ነኀሥሥ እምኀቤከ።
ዳግመኛ አቤቱ ካንተ ዘንድ የምንሻውን በምንለምንበትና
በምንጸልይበት ጊዜ እናስባቸው ዘንድ አስቡን ያሉትን ዳግመኛ
አስብ።
Remember again, Lord them that have bidden us to
remember them at the time of our prayers and
supplications where with we make request of You.
ኦ እግዚአብሔር አምላክነ ለእለ ቀደሙነ ነዊመ አዕርፎሙ
ወለዱያንሂ ፍጡነ ፈውሶሙ።
አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ከኛ አስቀድመው
የሞቱትን አሳርፋቸው ፤ የታመሙትንም ፈጥነህ አድናቸው።
O Lord our God, give rest to them that have fallen
asleep before us, heal speedily them that are sick,
እስመ አንተ ውእቱ ሕይወተ ኵልነ ፤ ወተስፋ ኵልነ ፤
ወባላሔ ኵልነ ፤ ወመንሥኤ ኵልነ ፤ ወለከ ንፌኑ አኰቲተ
እስከ አርያም ለዓለመ ዓለም።
የሁላችን ሕይወት ፣ የሁላችን ተስፋ ፣ የሁላችን አዳኝ ፣
የሁላችንም አስነሽ አንተ ነህና። ላንተ ምስጋናን እስከ አርያም
ድረስ እንልካለን።
for You are the life of us all, the hope of us all, the
deliverer of us all and the raiser of us all, and to You
we lift up thanksgiving unto the highest heaven, world
without end.
ምስባክ
ሀቡ አኯቴተ ሇእግዚአብሔር። አርውዮ ሇትሇሚሃ። ወሐመሌማሇ ሇቅኔ ዕጓሇ እመሕያው። ዯቂቀ እጓሇ እመሕያው
ሐወጽከኒ ላሉተ ወፈተንኮ ሇሌብየ። ዏርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወሳሙኤሌኒ ምስስ እከ ይጼውዐ ስሞ ዯብረ ጽዮን አፍቀረ።
ሐወጽካ ሇምድር ወአርወይካ። አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ። ወበመንፈስ አዚዝ አጽንዏኒ። ግበሩ በዒሇ በትሥፍሕት በኀበ እሇያተሐምምዎ።
ሇነዳያኒሃኒ አጸግቦሙ እክሇ። አንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኅ። ወተንሥአ፡እግዚአብሔር ከመ ንቃህ፡እምንዋም። ጻድቅሰ ከመ በቀሌት ይፈሪ
ሌበ ንጹሐ ፍጥር ሉተ እግዚኦ። አንተሰ እግዚእ መሐሪ ወመስተ ሣህሌ። ወትሰይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ።
መሐሇ እግዚአብሔር ወኢይኔስሕ አግረረ ሇነ አሕዛበ ወሕዝበ ታሕተ እገሪነ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። ፈኑ እዴከ እምዒርያም።
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅደሳን። ዏፀዯ ወይን አፍሇስከ እምግብፅ። ወንግርዎሙ ሇአሕዛብ ምግባሮ ፍሬ ፃማከ ተሴስይ።
ምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ አፉሁ ሇጻድቅ ይትሜሀር ጥበበ ወአነሂ በኩርየ እሬስዮ።
ሠረገሊቲሁ ሇእግዚአብሔር ምዕሌፊተ አዕሊፍ ፍሡሓን። ኢትዝክር ብነ አበሳነ ትካት። ወአጽንዖ እግዚኦ ሇዝንቱ ሠራዕከ ሇነ
ሣህለ ሇእግዚአብሔር መሌዏ ምድረ። ኢትግፈኒ እምቅድመ ገጽከ። ወእነግር ስምዏከ በቅድመ ነገሥት ወኢትይኀፈር
ሣህሌ ወርትዕ ተራከባ። ዒይነ ኵለ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ሇእሇ ይፈርሁከ።)
ስሚዑ ወሇትየ ወርእዩ ወእጽምዑ እዝነኪ፡፡ እምሥራቀ ፀሐይ እስከነ ዏረብ። ወይሰግዳ ልቱ አዋሌዯ ጢሮስ በአምኃ
ሶበ ትሬእዮሙ ሇጠቢባን ይመውቱ እምነ ጽዮን ይብሌ ሰብእ። ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክሌት ኅበ ሙሐ ማይ።
ርእዩከ ማያት እግዚኦ። እምአፈ ዯቂቅ ወሕፃናት አስተዳልከ ስብሐተ። ወይወስደ ሇንጉሥ ዯናግሇ ድኅሬሃ
ቀዯሰ ማኅዯሮ ሌዐሌ እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ሇፀሐይ
ቃሇ ወሀቡ ዯመናት አሕፃከ ይወፅኡ። እስመ ኀቤከ እጼሉ እግዚኦ ውስተ ኵለ ምድር ወፅአ ነገሮሙ
ቅረቡ ኀቤሁ ወያበርህ ሇክሙ። እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ምሩ ሇእግዚአብሔር የኀድር ውስተ ጽዮን።
በሌዐ ወጸግቡ ጥቀ። እስመ ሰበረ ኖኃተ ብርት። አዝከ መድኀኒቶ ሇያዕቆ
በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ እስመ ቅንዏተ ቤትከ በሌዏኒ። ያበቍሌ ሣዕረ ሇእንሰሳ።
ቡሩክ ይመጽእ በስመ እግዚአብሔር። እስመ በእንቲአሁ ይቀትለነ ኵል አሚረ ይሁብ ሲሳየ ሇኵለ ሥጋ።
ብፁዕ ብእሲ አንተ ገሠጽኮ እግዚኦ እስመ ፈተወ ንጉሥ ስነኪ። ይገሇብቦ ሇሰማይ በዯመና።
ተቀነዩ ሇእግዚአብሔር እበውእ ቤተከ ምስሇ መባእየ ዛቲ ዕሇት እንተ ገብረ እግዚአብሔር።
ተከር ማኅበረከ አቅዯምከ ፈጢረ እግዚአብሔር ስቡሕ በምክረ ቅደሳን። የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዏረብ።
ተከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ። እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ሇነ። የዏርግ ዯመናተ እምአጽናፈ ምድር
ተፅዕነ ሊዕሇ ኪሩቤሌ ወሠረረ እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዏራተ ሕማሙ። ይትነሣእ እግዚአብሔር ወይረዉ ፀሩ።
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤለኒ እግዚአብሔር ነሐውር። እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገበረ። ይትዒየን መሌአከ እግዚአብሔር ዏውዶሙ
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤለኒ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዒሇም። ይእዜ እትነሣእ ይቤ እግዚአብሔር።
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ። እግዚአብሔርሰ ገሀድ ይመጸእ። አሌቦ ነገር ወአሌቦ ነቢብ ኢተሰምዏ ቃልሙ።
ትሴብሖ ኢየሩሳላም ሇእግዚአብሔር። እግዚኦ በኃይሌከ ይትፌሣሕ ንጉሥ ዏረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ
ክነፈ ርግብ በብሩር ግቡር
ነገሥተ ተርሴስ እግዚኦ ኵነኔከ ሀቦ ሇንጉሥ
ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ። ዖፍኒ ረከበት ሊቲ ቤተ።
ንፍሑ ቀርነ በዕሇተ ሠርቅ። ከመ እንግር ፈቀዯከ መከርኵ አምሊኪየ።
ኖሊዊሆሙ ሇእሥራኤሌ አጽምዕ ኵል ፈቀዯ ገብረ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ልዑል ይባርክ ላዕለ ኵልነ። ወይቀድሰነ በኵሉ
በረከት መንፈሳዊት። ወይረሲ በአተነ ውስተ ቤተ ክርስቲያን
ቅድስት።
ልዑል እግዚአብሔር ሁላችንን ይባርክ ፤ በመንፈሳዊም በረከት
ሁሉ ያክብረን። ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መግባታችንንም።
O God, most high, bless us all and sanctify us with every
spiritual blessing, and bring us into the Holy church
ኅቡረ ምስለ መላእክቲሁ ቅዱሳን እለ ይትቀነዩ ሎቱ በፍርሀት
ወበረዓድ ወትረ ወይሴብሕዎ በኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት ይእዜኒ
ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም። አሜን። አ
ዘወትር በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከሚያገለግሉት ቅዱሳን
መላእክት ጋራ በአንድነት ያድርግ። በየጊዜውና በየሰዓቱም ሁሉ
ከሚያመስግኑት ከቅዱሳን መላእክት ጋራ አንድነት ያድርግ
ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ። አሜን
to be joined with His Holy angels who serve Him always
in fear and trembling, and glorify Him at all times and
all hours, both now and ever and world without end.
Amen.
እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ወመፍቀሬ ሰብእ አንተ
ውእቱ ዘፈነውኮሙ ለአርዳኢከ ቅዱሳን ወለላእካኒከ
ወለሐዋርያቲከ ንጹሓን ውስተ ኵሉ አጽናፈ ዓለም።
አምላካችንና መድኃታችን ሰውንም የምትወድ እግዚአብሔር
ሆይ ቅዱሳን የሚሆኑ ደቀ መዛሙርትህንና አገልጋዮችህን
ንጹሓን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ሁሉ ዳርቻ የሰደድሃቸው አንተ
ነህ።
Lord our God and our Saviour and lover of man, You
are He who did send Your Holy disciples and ministers,
and Your pure apostles unto all the ends of the world
ከመ ይስብኩ ወይምህሩ ወንጌለ መንግሥትከ ወይፈውሱ ኵሎ
ደዌ ወኵሎ ሕማመ ዘውስተ ኵሉ ሕዝብከ ወይዜንዉ
ምሥጢረከ ኅቡአ ዘእምቅድመ ዓለም።
የመንግሥትህን ወንጌል ይሰብኩና ያስተምሩ ዘንድ በሕዝብህ
ውስጥ ያለውን ደዌውን ሁሉ በሽታውንም ሁሉ ያድኑ ዘንድ
ከዓለም አስቀድሞ የነበረውን የተሰወረውን ምሥጢርህንም
ያስተምሩ ዘንድ።
to preach and teach the gospel of Your kingdom, and to
heal all the diseases and all the sicknesses which are
among Your people, and to proclaim the mystery hidden
from before the beginning of the world.
ወይእዜኒ እግዚእነ ወአምላክነ ፈኑ ላዕሌነ ብርሃነከ ወጽድቀከ
ወአብርህ አዕይንተ አልባቢነ ወሕሊናነ ወረስየነ ድልዋነ ንስማዕ
በጥብዓት ቃለ ወንጌልከ ቅዱስ።
አሁንም ጌታችን አምላካችን ሆይ ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክልን
ያሳባችንና የልቦናችንን ዓይኖች አብራልን። የከበረ የወንጌልን
ቃል በመጨከን እንሰማ ዘንድ የበቃን አድርገን።
Now also, our Lord and our God, send upon us Your
light and Your righteousness, and enlighten the eyes of
our hearts and of our understanding; make us meet to
persevere in hearing the word of Your Holy gospel,
አኮ ዘንሰምዕ ባሕቲቱ አላ ንግበር በከመ ሰማዕነ ከመ ይፍረይ
ላዕሌነ ፍሬ ሠናየ ህየንተ ፩ ፴ ወ፷ ወ፻ ከመትሥረይ አበሳነ
ለሕዝብከ ወንኩን ድልዋነ ለመንግሥተ ሰማያት።
የምንሰማ ብቻ አይደለም እንደሰማን ልንሠራ ነው እንጂ ስለ
አንዱ ፈንታ ሠላሳና ስድሳ መቶም ያማረ ፍሬ በላያችን ያፈራ
ዘንድ የወገኖችህን ኃጢአት ታስተሠርይ ዘንድ ለመንግሥተ
ሰማያትም የበቃን እንሆን ዘንድ።
and not only to hear but to do according to what we
hear, so that is may hear good fruit in us, remaining not
one only but increasing thirty, sixty, and a hundredfold;
and forgive us our sins, us Your people, so that we
maybe worthy of the kingdom of heaven.
ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ።
ሁሉን የያዘ እግዚአብሔር አብ ብሩክ ነው።
Blessed be God Almighty Father.
አእኵትዎ ለአብ።
አብን አመስግኑት።
Give thanks unto the Father. t
ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ወልድ ዋሕድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቡሩክ ነው።
And blessed be the only-begotten Son our Lord Jesus
Christ.
አእኵትዎ ለወልድ።
ወልድን አመስግኑት።
Give thanks unto Son.
ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ።
አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው።
And blessed be the Holy Spirit Paraclete.
አእኵትዎ ለመንፈስ ቅዱስ።
መንፈስ ቅዱስን አመስግኑት።
Give thanks unto Holy Spirit.
ሃሌ ሉያ ቁሙ ወአጽምዑ ወንጌለ ቅዱሰ ዜናሁ ለእግዚእነ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ሃሌ ሉያ ጌታችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
የተናገረውን ቅዱስ ወንጌል ቆማችሁ አድምጡ።
Halleluiah, stand up and hear to the Holy Gospel, the
message of our Lord and Savior Jesus Christ.
እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።
The Lord be with you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with your Spirit..
ወንጌል ቅዱስ ፤ ዘዜነወ ማቴዎስ / ማርቆስ / ሉቃስ (ዘሰበከ
ዮሐንስ) ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።
(ማቴዎስ / ማርቆስ / ሉቃስ ) የተናገረው (ዮሐንስ የሰበከው)
የእግዚአብሔር ልጅ ቃል የሚሆን ቅዱስ ወንጌል ይህ ነው።
The Holy gospel which as Matthew / Mark / Luke have
proclaimed, (John preached) the Word of the Son of
God.
ስብሐት ለከ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላኪየ ኵሎ ጊዜ።
ጌታዬና አምላኬ ክርስቶስ ሆይ ሁልጊዜ ለአንተ ምስጋና
ይገባል።
Glory be to You, Christ my Lord and my God, at all
times.
የጾም ወቅት ከሆነ ወደሚቀጥለው ገጽ ተሻገር።
For fasting season, go to the next page
ተፈስሑ በእግዚአብሔር ዘረድአነ ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ
ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ
መሰንቆ።
በረዳን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ። የያቆብንም አምላክ
አመስግኑ። መዝሙሩን ያዙ ፤ ከበሮውንም ስጡ ፤ ከበገና ጋራ
የተስማማ ነው።
Sing aloud unto God our strength: make a joyful noise
unto the God of Jacob. Take a psalm, and bring hither
the timbrel, the pleasant harp with the psaltery.
በጾም ጊዜ በ“ተፈስሑ” ፈንታ / replacement of “Sing aloud”
በወንጌል መራህከነ ፤ ወበነቢያት ናዘዝከነ ፤ ዘለሊከ
አቅረብከነ ስብሐት ለከ።
በወንጌል መራኸን ፤ በነቢያትም አጸናኸን ፤ ለአቀረብኸን
ክብር ምስጋና ይገባል።
You have guided us with the Gospel, comforted us
with the prophets, and drawn us nigh unto You. Glory
be to You.
ነዋ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት።
ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ ወንጌል እነሆ።
Behold the Gospel of the kingdom of heaven.
መንግሥቶ ወጽድቆ ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ።
መንግሥቱንና ጽድቁን የሰጠኝን ሰጠሁህ።
His kingdom and His righteousness which He delivered
to me: I deliver to you.
ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት።
መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ።
For the kingdom of heaven is at hand.
የማቴዎስ ፥ ማርቆስና ሉቃስ ወንጌል ሲነበብ
When reading from Matthew, Mark and Luke
ባርክ እግዚኦ ነገረ ዘእምወንጌለ …. ረድኡ ወሐዋርያሁ
ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ሎቱ
የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሐዋርያውና ደቀ መዝሙሩ ከሚሆን … ወንጌል የተገኘውን
Bless, O Lord, the portion of the gospel of …. The
disciple and apostle of our Lord Jesus Christ the Son of
ስብሐት ወትረ እስከ ለዓለም ዓለም አሜን።
ቃል አቤቱ ባርክ። ምስጋና ዘወትር ገንዘቡ ነው ለዘለዓለሙ
አሜን።
the living God ; to Him be glory continually, and unto
the ages of ages. Amen.
ዮሐንስ ወንጌል ሲነበብ - When reading from John
ዝ ቃል ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ለክብረ መንግሥቱ ስብሐት እስከ ለዓለም።
ለመንግሥቱ እስከ ዘላለም ምስጋና ይግባውና ይህ ቃል
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ነው።
This is the word of our Lord and our God and our
Saviour Jesus Christ for the honor of His kingdom,
የዕለቱ የወንጌል ምንባብ
እየተነበበ ነው።
The Gospel of the Day is being read.
የማቴዎስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from Mathew)
ሰማይ ወምድር የኀልፍ ወቃልየሰ ኢየኀልፍ ይቤ እግዚእ
ለአርዳኢሁ።
ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም አለ ጌታ ለደቀ
መዛሙርቱ።
Heaven and earth shall pass away, but My Words, shall
not pass away, said the Lord to his disciple.
የማቴዎስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from Mathew)
ነአምን አበ ዘበአማን ፤ ወነአምን ወልደ ዘበአማን ፤ ወነአምን
መንፈሰ ቅዱሰ ዘበአማን ህልወ ሥላሴሆሙ ነአምን።
አብን በእውነት እናምናለን። ወልድንም በእውነት እናምናለን ።
መንፈስ ቅዱስንም በእውነት እናምናለን። የማይለወጥ
ሦስትነታቸውንም በእውነት እናምናለን።
We believe in the very Father, we believe in the very
Son, and we believe in the very Holy spirit, we believe in
their unchangeable Trinity.
የማርቆስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from Mark)
ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ።
ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ።
He that has ears to hear, let him hear.
የማርቆስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from Mark)
እሉ ኪሩቤል ወሱራፌል ያዐርጉ ሎቱ ስብሐተ እንዘ ይብሉ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር አብ ወወልድ ወመንፈስ
ቅዱስ።
እሊህ ኪሩቤልና ሱራፌል ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር ነህ እያሉ ምስጋናን
ያቀርቡለታል ።
Those cherubim and seraphim offer to Him glory saying;
Holy Holy Holy You are God, Father, Son and the Holy
Spirit.
የሉቃስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from Luke)
ይቀልል ኅልፈተ ሰማይ ወምድር እምትደቅ አሐቲ ቃል
እምኦሪት ወእምነቢያት።
ከኦሪትና ከነቢያት አንዲቱ ቃል ከምትወድቅ የሰማይና የምድር
ማለፍ ይቀላል።
It is easier for heaven and earth to pass, than one little
of the Law to fall.
የሉቃስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from Luke)
መኑ ይመስለከ እምነ አማልክት እግዚኦ አንተ ውእቱ ዘትገብር
መንክረ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኃይለከ ወአድኀንኮሙ ለሕዝብከ
አቤቱ ከአማልክት ወገን የሚመስልህ ማነው? ተአምራትን
የምታደርግ አንተ ነህ። ለወገኖችህ ኃይልህን አሳየሃቸው።
Who is like unto You, O lord, among the gods? You are
the God that does wonders: You have declared your
strength among the people. You have with Your arm
redeemed the people.
በመዝራዕትከ። ሖርከ ውስተ ሲኦል ወአዕረገ ፄዋ እምህየ ወጸጎከነ
ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ በእንተ ዝንቱ
ንሴብሐከ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል
ወገኖችህንም በክንድህ አዳንካቸው። ወደ ሲኦል ሄደህ ከዚያ
ምርኮን አወጣህ። ዳግመኛም አንድ ጊዜ ነጻነትን ሰጠኸን።
መጥተህ አድነኸናልና ስለዚህ እናመሰግንሃለን።
You did go into Hades and the Captives rose up from
there, and thou did grant us again to be set free, for
You did come and save us. For this cause we glorify
You and cry unto You saying,
ቡሩክ አንተ እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ
ወአድኀንከነ።
አቤቱ ኢየሱስ ሆይ ቡሩክ ነሀ እያልን እንጮኻለን ፤ መጥተህ
አድነኸናልና።
Blessed are You, Lord Jesus Christ, for You did come
and save us.
የዮሐንስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from John)
ካህን (priest)
ዘየአምን በወልድ ቦ ሕይወት ዘለዓለም።
በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው።
He that believes on the Son has everlasting life.
የዮሐንስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ (After Reading from John)
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ ቃል ሥጋ
ኮነ ወኀደረ ላዕሌነ ወርኢነ ስብሐቲሁ ከመ ስብሐተ ፩ዱ ዋሕድ
ለአቡሁ።
ቃል በቅድምና ነበር። ይህ ቃል የእግዚአብሔር አብ ቃል ነው።
ያ ቃል ሥጋ ሆነ ፤ በእኛም አደረ። ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ
የሚሆን ክብሩንም አየን።
In the beginning was the Word, the Word was the Word of
God: The Word was made flesh, and dwelt among us,
and we beheld His glory, the glory as of the only
begotten of the Father,
ቃለ አብ ሕያው ወቃል ማሕየዊ ቃለ እግዚአብሔር ተንሥአ
ወሥጋሁኒ ኢማሰነ።
የሕያው የአብ ቃል ነው። ያ ቃልም መድኃኒት ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ተነሣ። ሥጋውም አልጠፋም።
the Word of the living Father, and the life-giving Word,
the Word of God, rose again and His flesh was not
corrupted.
ስብሐት ለከ እግዚአብሔር አምላክነ አኃዜ ኵሉ ዘረሰይከነ
ድልዋነ ንስማዕ ቃለ ወንጌልከ ቅዱስ ወከመ ነአምኖ
ወንትፈሣሕ ቦቱ።
ክቡር የሚሆን የወንጌልን ቃል እንሰማ ዘንድ ፤ እንሳለመውም
ዘንድ ፤ በርሱም ደስ ይለን ዘንድ ለዚህ የበቃን ያደረግኸን
ሁሉን የያዝህ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ለአንተ ምስጋና
ይገባል።
Glory be to You, O our God, the Almighty, we give
thanks to You, for that we may hear and kiss the
glorious word of the gospel and we may rejoice in it.
ወካዕበ ንስእል ወናስተበቊዕ ከመ ትጽሐፍ ውስተ አልባቢነ ቃለ
ወንጌልከ ቅዱስ። ወተወከፍ ስእለተነ በውስተ ዝንቱ ምሥዋዒከ
ኀበ ቦአ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ዳግመኛም ክቡር የሚሆን የወንጌልህን ቃል በልቡናችን ትጽፍ
ዘንድ እንለምናለን ፤ እንማልዳለንም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በገባበት በዚህ በመሠዊያህ ልመናችንን ተቀበል።
Once again, we ask and beseech You to write down the
word of Your glorious gospel in our conscience; and
accept our prayer on this temple where our Lord Jesus
Christ entered.
ወፈኑ ላእሌነ ወላዕለ ሕዝብነ ሣህለከ ወምሕረተከ። በ፩ ወልድከ
እስመ ለከ ስብሐት ወኃይል ለዓለመ ዓለም አሜን።
በእኛም በወገኖቻችንም ላይ ይቅርታህንና ቸርነትህን ላክ።
በአንድ ልጅህ ለአንተ ምስጋና ከሃሊነትም ይገባሃልና
ለዘለዓለሙ። አሜን።
And send Your compassion upon us and upon Your
people, through Your only-begotten Son, for Yours is the
glory and power, world without end. Amen.
ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን።
የክርስቲያን ታናሾች የሆናችሁ ውጡ።
Go out, You catechumens.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ወካዕበ ናስተበቊዕ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ንስእል ወነኀሥሥ እምነ ኂሩትከ፤
ኦ መፍቀሬ ሰብእ፤
ዳግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን ፤ ሰው ወዳጅ ሆይ
ከቸርነትህ እንሻለን እንለምናለን።
Again we beseech the almighty God, the Father of our
Lord and our Saviour, Jesus Christ: we ask and entreat
of Your goodness. O lover of man,
ተዘከር እግዚኦ ሰላመ ቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት አሐቲ ጉባኤ
እንተ ሐዋርያት እንተ ሀለወት እምጽንፍ እስከ አጽናፈ ዓለም።
አቤቱ ሐዋርያት የሰበሰቧት አንዲት የምትሆን የቅድስት ቤተ
ክርስቲያንን ሰላም አስብ ፤ ከዳርቻ እስከ እስከ ዓለምዳርቻ
ድረስ ያለች።
remember Lord, the peace of the one Holy apostolic
Church which reaches from one end of the world to the
other.
ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ
ሐዋርያት ርትዕት በኀበ እግዚአብሔር።
ሐዋርያት ስለሰበሰቧት በእግዚአብሔር ዘንድ ስለቀናች ፤
ለአንዲት ክብርት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ።
Pray for the peace of the one Holy apostolic church
orthodox in the Lord.
ኵሎ ሕዝበ ወኵሎ መራዕየ ባርኮሙ። ኵሎ ሰላመ እንተ
እምሰማያት ፈኑ ውስተ አልባቢነ ለኵልነ ወሰላመ ወሕይወተነ
ጸግወነ ባቲ።
ሕዝቡን ሁሉ መንጋዎችንም ሁሉ ባርካቸው። ከሰማይ የሚገኝ
ሰላምን ሁሉ በሁላችን ልቡና አሳድርብን። በርስዋም የሕይወትን
ሰላም ስጠን።
All the people and the whole flock bless You, all the
peace that is from heaven send You into the hearts of
us all, and vouchsafe us the safety of our life therein.
ጸግዋ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ለታዕካሃ ወለሠራዊታ
ወለመኳንንታ ወለሕዝባ። ወጉባኤ አግዋርነ ዘአፍኣ ወውስጥ
አሠርግዎሙ በኵሉ ሰላም፤
ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ለአንድነቷ ለሠራዊቷም ለመኳንንቷም
ለሕዝቧም ሰላምን ስጣት። በእዳሪና በውስጥ ያሉትን
ጎረቤቶቻችንን ሁሉ በፍጹም ሰላም አስጊጻቸው።
Vouchsafe peace to our country Ethiopia, to her unity, to
her armies, to those who rule her people. And to the
multitude of our neighbors at home and abroad; adorn
them with all peace:
ኦ ንጉሠ ሰላም ሰላመከ ሀበነ እስመ ኵሎ ወሀብከነ አጥርየነ
እግዚአብሔር ወዕሥየነ እስመ ዘእንበሌከ ባዕድ አልቦ ዘነአምር።
የሰላም ንጉሥ ሆይ ሰላምህን ስጠን ፤ ሁሉን ሰጥተኸናልና
እግዚአብሔር ሆይ ጥሪት አድርገን ፤ ዋጋችነንም ስጠን ካንተ
በቀር ሌላ የምናውቀው የለምና።
O King of peace, grant us Your peace for You have
granted us all things. Possess us, O Lord, and requite
us, for beside You we know none other;
ስመከ ቅዱሰ ንሰሚ ወንጼውዕ ፤ ከመ ትሕየው ነፍስነ በመንፈስ
ቅዱስ ወኢይትኀየል ሞተ ኃጢአት ላዕሌነ ለአግብርቲከ
ወለኵሉ ሕዝብከ፤
ቅዱስ የሚሆን ስምህን ፈጽመን እንጠራለን ፤ ነፍሳችን
በመንፈስ ቅዱስ ትድን ዘንድ በኃጢአት የመጣ ሞትም በኛ
ባገልጋዮችህ ላይ በወገኖችህም ሁሉ እንዳይበረታታ
we make mention of Your Holy name and call upon it,
that our souls may live through the Holy Spirit, and that
the death of sin may not have dominion over us Your
servants and all Your people:
በአሐዱ ወልድከ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ
ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ባንድ ልጅህ ከርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ላንተ ይገባል ፤ ከርሱ ጋራ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Through Your only-begotten Son to whom with You and
with the Holy Spirit be glory and dominion, both now
and ever and world without end, Amen.
ኪርያላይሶን።
Kyrie leison.
ዲያቆናት (Deacons)
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us.
upon us.
ካህናት (Priests)
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ካህን ንፍቅ (Asst. priest)
ወካዕበ ናስተበቊዕ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
ዳግመኛም ሁሉን የያዘ የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እንማልዳለን፤
And again we beseech the almighty God, the Father of
our Lord and our Saviour Jesus Christ;
በእንተ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሳት አባ……ከመ ዐቂበ ይዕቀቦ ለነ
ለብዙኅ ዓመታት ወለመዋዕለ ሰላም እስከ ይፌጽም ዘእምኀቤሁ
ሎቱ ዘተአመኖ ለሢመተ ክህነት ዘብዑለ ጸጋ ይጼጉ
እግዚአብሔር አምላክነ።
ብፁዕ ስለሚሆን ሊቀ ጳጳሳት ስለ አባ _____ለብዙ ዘመናት
ለሰላም ወራት መጠበቅን ይጠብቅልን ዘንድ ብዙ ጸጋን የሚሰጥ
አምላካችን እግዚአብሔር ለክህነት ሹመት የታመነለትን ከሱ
ዘንድ እስኪጨርስለት ድረስ።
For the blessed Patriarch Abba ……. that he truly
preserve him to us for many years and in peaceful days
until the Lord our God who is rich in grace grant him to
fulfil that which was committed unto him, the office o
priesthood.
ዲያቆን ንፍቅ (Asst. deacon)
ጸልዩ በእንተ ሊቀ ጳጳሳት አባ ……እግዚእነ ርእሰ ኤጲስ ቆጶሳት
ዘሀገር ዐባይ ኢትዮጵያ ወዲበ ርዕሰ ሀገረ አበዊነ ብፁዕ ሊቀ
ስለ ሊቀ ጳጳሳቱ ስለ አባ ……የደገኛዪቱ አገር የኢትዮጵያ
የኤጲስ ቆጶስ አለቃ ጌታ ስለሚሆን፤ በአባቶቻችን አገርም ብፁዕ
ስለሚሆን ስለ አባ …….ሃይማኖታቸው ስለ ቀና ስለ ኤጲስ
Pray for the Patriarch Abba …… lord chief of the
bishops of the great nation of Ethiopia and for the
blessed Primate of the country of our father Abba.
……..and all the orthodox bishops, priests and deacons.
ጳጳስነ አባ……… ወኵሎሙ ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት
ወዲያቆናት ርቱዓነ ሃይማኖት።
ቆጶሳቱ ስለ ቀሳውስቱና ስለ ዲያቆናቱ ሁሉ ጸልዩ።
……..and all the orthodox bishops, priests and deacons.
ካህን ንፍቅ (Asst. priest)
እግዚአብሔር አምላክነ ዘኵሎ ትእኅዝ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ
በእንተ ብፁእ ጳጳስ አባ…….ከመ ዐቂበ ትዕቀቦ ለነ ለብዙኅ
ዓመታት ወለመዋዕለ ሰላም እስከ ይፌጽም ዘእምኀቤከ ሎቱ
ሁሉን የያዝህ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ እንለምንሃለን
እንማልድሃለንም ፤ ብፁዕ ስለሚሆን ስለ አባ ……. ለብዙ
ዘመናት ለሰላምም ወራት መጠበቅን ትጠብቀው ዘንድ፤
Lord our God almighty, we pray and beseech You for
our blessed archbishop Abba ..…. that You may truly
preserve him to us for many years
ዘተአመንኮ ለሢመተ ክህነት ምስለ ኵሎሙ ኤጲስ ቆጶሳት
ቀሳውስት ወዲያቆናት ርቱዓነ ሃይማኖት።
ካንተ ዘንድ ለክህነት ሹመት እሱን የመረጥህለትን ሥራ
እስኪፈጽም ድረስ ፤ ከኤጲስ ቆጶሳቱ ሁሉ ጋራ ሃይማኖታቸው
ከቀና ከቀሳውስቱና ከዲያቆናቱም ጋራ፡
and in peaceful days to fulfill the office of priesthood
which You have committed unto him, together with all
the orthodox bishops, priests and deacons,
ወምስለ ኵሉ ፍጻሜ ማኅበራ ለቅድስት አሐቲ እንተ ላዕለ ኵሉ
ቤተ ክርስቲያን ወጸሎተኒ ዘይገብር በእንቲአነ ወበእንተ ኵሉ
ሕዝብከ ተወከፎ፤
ከሁሉ በላይ ከምትሆን ከአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ከአንድነትዋም ፍጻሜ ሁሉ ስለ እኛ ስለወገኖችህ ሁሉ
የሚያደርገውን ጸሎት ተቀበለው።
And all the entire congregation of the one holy universal
church; and the prayer which he makes on our behalf
and on behalf of all Your people do You accept;
አርኁ ሎቱ መዝገበ በረከትከ ፤ ዓዲ ፈድፋደ ሎቱ ጸጋ መንፈስ
ቅዱስ ጸግዎ ፀጋ ፤ ወከዐው ላዕሌሁ እምሰማይ በረከተከ ከመ
ይባርክ ሕዝበከ፤
የበረከትህንም መዝገብ ክፈትለት ፤ ዳግመኛ ይልቁን ለእርሱ
የመንፈስ ቅዱስን ሀብት ስጠው። ወገኖችህን ይባርክ ዘንድ
ከሰማይ በረከትህን በላዩ ላይ አፍስስ።
open to him the treasure-house of your blessing, and
especially grant to him abundantly the grace of the Holy
Spirit; pour up on him from heaven Your blessing that
he may bless Your people;
ወኵሎ እንከ ፀሮ ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ አግርር ወቀጥቅጥ
ታሕተ እገሪሁ ፍጡነ ፤ ወኪያሁሰ እንከ ዕቀቦ ለነ በጽድቅ
ወበሰላም ለቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት በስብሐት ወበጸሎት።
የሚታየውንና የማይታየውን ጠላቱን ሁሉ ፈጥነህ ከእግሩ በታች
አድርገህ ቀጥቅጠህ አስገዛለት። እርሱን ግን በእውነት በሰላም
ለክብርት ቤተ ክርስቲያንህ ብለህ በክብር ጠብቅልን።
And all his enemies, visible and invisible, do You subdue
and bruise under his feet speedily; but himself do You
preserve unto us in righteousness and peace and glory,
for Your Holy church;
በ፩ ወልድከ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ ስብሐት
ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ላንተ ይገባል ከርሱ ጋራ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ ፤ አሜን።
Through Your only-begotten Son through whom to You
with Him and with the Holy Spirit be glory and dominion,
both now and ever and world without end, Amen.
ዲያቆናት (Deacons)
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ካህናት (Priests)
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ካህን(priest)
ወካዕበ ናስተበቊዕ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ንስእል ወነኀሥሥ እምነ
ኂሩትከ ኦ መፍቀሬ ሰብእ።
ዳግመኛም ሁሉን የያዘ የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ
ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን ፤ ሰው ወዳጅ
ሆይ ከቸርነትህ እንሻለን እንለምናለን።
And again we make our supplication to the almighty
God, the Father of our Lord and our Saviour Jesus
Christ; we ask and entreat of Your goodness, O lover of
man:
ተዘከር እግዚኦ ማኅበረነ ባርኮሙ።
አቤቱ አንድነታችንን አስብ ፤ ባርካቸው።
Remember, Lord, our congregation; bless them.
ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወማኅበርነ
በውስቴታ።
ክብርት ስለምትሆን ስለዚህች ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ስለአለ
አንድነታችንም ጸልዩ።
Pray for this Holy church and our congregation therein.
ማኅበረነ ባርክ ዕቀብ በሰላም።
አንድነታችንን ባርክ ፤ በሰላም ጠብቅ።
Bless our congregation and keep them in peace.
ካህን (priest)
ወጸግዎሙ ከመ ይኩኑ ለከ ዘእንበለ ጽርዓት ወኢክልዓት
ይግበሩ ፈቃደከ ቅድስተ ወብፅዕተ ቤተ ጸሎት ቤተ ንጽሕ
ወቤተ በረከት፤
የተደነቀችና የከበረች ፈቃድህን ያለ ማቋረጥና ያለመከልከል
እንዲሠሩ ያንተ ይሆኑ ዘንድ፤ የጸሎትን ቤት ፤ የንጽሕናንም
ቤት የበረከትንም ቤት ስጣቸው።
Grant that they maybe Yours that without slothfulness or
hindrance they may do Your Holy and blessed will, a
house of prayer, a house purity and a house of blessing.
ጸግወነ እግዚኦ ለነኒ ለአግብርቲከ ወለእለ ይመጽኡ እምድኅሬነ
እስከ ለዓለም መዋዕለ ጸጉ። ተንሥእ እግዚኦ አምላኪየ
ወይዘረዉ ፀርከ ወይጕየዩ ኵሎሙ እምቅድመ ገጽከ እለ
ይጸልዑ ቅዱሰ ወቡሩከ ስመከ።
ለእኛም ለአገልጋዮችህ ከኛም በኋላ ለሚነሡ ፤ አቤቱ ስጠን።
እስከ ዘለዓለምም ዘመንን ስጥ። አቤቱ አምላኬ ሆይ ተነሥ
ጠላቶችህም ይበተኑ ፤ ቅዱስ ምስጉን የሚሆን ስምህን የሚጠሉ
ሁሉም ከፊትህ ይሽሹ።
Give us also, Lord, us Your servants, and to them that
shall come after us, vouchsafe us to the end of the
world, length of days. Arise, Lord my God, and let Your
enemies be scattered, and let them that hate Your Holy
and blessed name flee before You.
ወሕዝብከሰ ይኩኑ ቡሩካነ በበረከተ አእላፈ አእላፋት
ወትእልፊተ አእላፋት እለ ይገብሩ ፈቃደከ ለዝሉፉ በኵሉ
ጊዜ።
በጊዜው ሁሉ ፈቃድህን የሚሠሩ ወገኖችህ ግን እልፍ አእላፋት
ትእልፊተ አእላፋት በሚሆኑ መላእክት በረከት የተባረኩ
ይሁኑ።
But let Your people who do Your will at all times be
blessed with blessings a thousand thousands and ten
thousand times
በ፩ዱ ወልድከ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ
ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ባንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል ፤ ከእርሱ
ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ፤
አሜን።
ten thousand through Your only-begotten Son through
whom to You with Him and with the Holy Spirit be
glory and dominion, both now and ever and world
without end, Amen.
ንበል ኵልነ በጥበበ እግዚአብሔር ጸሎተ ሃይማኖት።
በእግዚአብሔር ጥበብ ሁነን ሁላችን የሃይማኖት ጸሎት
እንበል።
Let us all say, in the wisdom of God, the prayer of
faith.
ነአምን በ፩ዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ
ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን ፥ የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ
በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
We Believe in one God the Father almighty, maker of
heaven, earth and all things visible and invisible.
ወነአምን በአሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ዋሕድ
ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም። ብርሃን
ዘእምብርሃን አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን።
ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋራ በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን
በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን
የተገኘ ብርሃን ፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ ፤
And we believe in one Lord Jesus Christ, the only-
begotten Son of the Father who was with Him before
the creation of the world: Light from light, true God
from true God,
ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ፤ ዘቦቱ
ኵሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ ዘበሰማይኒ
ወዘበምድርኒ።
የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል።
ሁሉ በርሱ የሆነ ፤ በሰማይ ካለው በምድርም ካለው ያለ እርሱ
ምንም ምን የሆነ የለም።
begotten not made, of one essence with His Father: All
things were made by Him, and without Him nothing
whatsoever was made, in Heavens or on Earth.
ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት።
ተሰብአ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት
ድንግል ኮነ ብእሴ
ስለእኛ ስለሰው ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ። ከመንፈስ ቅዱስ
የተነሣ ከቅድስት ድንግል ማርያምም ፈጽሞ ሰው ሆነ።
Who for us men and for our salivation came down from
heaven, was made man and was incarnate from the Holy
Spirit and from the Holy Virgin Mary. Became man,
ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጴንጤናዊ። ሐመ ወሞተ
ወተቀብረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ
ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት። ዐርገ በስብሐት
ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ፤
ታመመ ፤ ሞተ ፤ ተቀበረም። በሦስተኛውም ቀን ከሙታን
ተለይቶ ተነሣ። በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር ወደ
ሰማይ አረገ ፤
was crucified for our sakes in the days of Pontius Pilate,
suffered, died, was buried and rose from the dead on
the third day as was written in the Holy scriptures:
Ascended in glory into heaven,
ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ
በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማኅለቅት
ለመንግሥቱ።
በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ። ዳግመኛ ሕያዋንን ሙታንንም ይገዛ
ዘንድ በጌትነት ይመጣል። ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
sat at the right hand of His Father, and will come again
in glory to judge the living and the dead; there is no
end of His reign.
ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማሕየዊ ዘሠረፀ እምአብ
ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት።
ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም
እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና
ከወልድ ጋራ በነቢያት የተናገረ።
And we believe in the Holy Spirit, the life- giving God,
who proceeds from the Father; we worship and glorify
Him with the Father and the Son; who spoke by the
prophets;
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ
ጉባኤ ዘሐዋርያት። ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ
ኃጢአት።
ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት
ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።
And we believe in One Holy, universal, apostolic church;
And we believe in One baptism for the remission of
sins,
ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም
አሜን።
የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን ፤ የሚመጣውንም
ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።
and wait for the resurrection from the dead and the life
to come, world without end. Amen!
ዘኮነ ንጹሐ ይንሣእ እምቍርባን ፤ ወዘኢኮነ ንጹሐ ኢይንሣእ
ከመ ኢየዐይ በእሳተ መለኮት ዘተደለወ ለሰይጣን
ወለመላእክቲሁ።
ንጹሕ የሆነ ከቍርባኑ ይቀበል ፤ ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል ፤
ለሰይጣንና ለመላክተኞቹ በተዘጋጀ በመለኮት እሳት
እዳይቃጠል።
He that is pure let him receive of oblation and he that is
not pure let him not receive it, that he may not be
consumed by the fire of the godhead which is prepared
for the devil and his angles.
ዘቦ ቂም ውስተ ልቡ ወዘቦ ውስቴቱ ሕሊና ነኪር ወዝሙት
ኢይቅረብ። በከመ አንጻሕኩ እደውየ እምርስሐት አፋአዊ
ከማሁ ንጹሕ አነ እምደመ ኵልክሙ።
በልቡናው ቂምን የያዘ ፤ ልዩ አሳብና ዝሙትም ያለበት ቢኖር
አይቅረብ። እጄን ከአፍአዊ እድፍ ንጹሕ እንዳደረግሁ
እንደዚሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ።
Whosoever has revenge in his heart and who ever has
in him strange thoughts and fornication let him not draw
near. As I have cleansed my hands from outward
pollution, so also I am pure from the blood of you all.
በድፍረትክሙ ለእመ ቀረብክሙ ኀበ ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ
አልቦ ላዕሌየ ትኅላፍ ለተመጥዎትክሙ እምኔሁ። ንጹሕ አነ
እምጌጋይክሙ ዳዕሙ ኃጢአትክሙ ይገብእ ዲበ ርእስክሙ
ለእመ በንጹሕ ኢቀረብክሙ።
ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከርሱ
ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም ፤ ኃጢአታችሁ በራሳችሁ
ይመለሳል እንጅ። በንጽሕና ሆናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ
ንጹሕ ነኝ።
If you presumptuously draw near to the body and blood
of Christ I will not be responsible for your reception
thereof. I am pure of your wickedness, but your sin will
return upon yourself if you do not draw nigh in purity.
እመቦ ዘአስተሐቀረ ዘንተ ቃለ ቀሲስ ፤ አው ዘሰሐቀ ወዘተናገረ፤
አው ዘቆመ በእከይ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ለያእምር ወይጠይቅ
ከመ አምዕዖ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወአንሰሐስሐ ላዕሌሁ
ይህንን የካህኑን ቃል ያቃለለ ፤ ወይም የሳቀና የተነጋገረ ፤
ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክፋት የቆመ ቢኖር ፤
ጌታችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘነው ፤
If there is any who disdains this word of the priest or
laughs or speaks or stands in the church in an evil
manner, let him Know and understand that he is
provoking to wraith our Lord Jesus Christ.
ህይንተ ቡራኬ መርገመ ፤ ወህይንተ ሥርየተ ኃጢአት እሳተ
ገሃነም ይረክብ እምኀበ እግዚአብሔር።
በርሱም እንደተነሣሣ ይወቅ ይረዳ። ስለ በረከት ፈንታ
መርገምን ፤ ስለ ኃጢአት ሥርየት ፈንታም ገሃነመ እሳትን
ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
and bringing upon himself a curse instead of a blessing,
and will get from God the fire of hell instead of the
remission of sin.
ካህን(priest)
ኦ እግዚእየ ወአምላኪየ ገባሬ ሥርዓት ወሃቤ ሰላም ወፍቅር
አሰስል እምላዕሌየ ኵሎ ሕሊና እኩየ ቂመ ወቅንዓተ ወኵሎ
ፍትወታተ ሥጋውያተ ወክፍለኒ እደመር
አቤቱ ጌታዬ አምላኬ ሆይ ሥርዓትን የሠራህ ሰላምንና ፍቅርን
የምትሰጥ ክፉውን ሕሊና ሁሉ ቂምን ቅንዓትንም ሥጋዊ
ፈቃድንም ሁሉ ከኔ አርቅልኝ።
O my Lord and my God, author of the Law, giver of
peace and love, take away from me every evil thought,
revenge, envy, and all the lusts of the flesh.
ምስለ አግብርቲከ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ በሥነ ሕይወቶሙ
በመዋዕለ ፍቅር ወሰላም ፤ እስመ አንተ ውእቱ ዘወረድከ
እምሰማይ ወገበርከ ሰላመ ምስለ ሰማያውያን ወምድራውያን
በበጎ ሕይወታቸው በሰላምና በፍቅር ወራት ካገለገሉህ ከክቡራን
አገልጋዮችህ ጋራ አንድ እንድሆን አድለኝ። ከሰማይ የወረድህ
ከሰማያውያንና ከምድራውያን ጋራ ሰላምን ያደረግህ።
Make me meet to be added to Your Holy servants who
pleased You by the beauty of their lives in the days of
love and peace፡ Because it is You who did come down
from heaven and make peace between the inhabitants of
heaven and the inhabitants of earth,
ወአስተጋባእኮሙ ለኵሎሙ ሕዝብከ ከመ ይሰብሑ ኪያከ
እስመ ለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም አሜን።
አንተንም ያመሰግኑ ዘንድ ወገኖችህንም ሁሉ የሰበሰብሃቸው
አንተ ነህና ምስጋና የሚገባህ ስለ ሆነ ለዘለዓለሙ አሜን።
and did gather together all Your people to glorify You,
for Yours is the glory, world without end. Amen.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us. upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ጸሎተ አምኃ ዘባስልዮስ
ባስልዮስ የተናገረው የስጦታ ጸሎት
Prayer of Salutation Basil
እግዚአብሔር ዐቢይ ዘለዓለም ዘለሐኮ ለሰብእ እንበለ ሙስና።
ለዘላለሙ ገናና የምትሆን እግዚአብሔር ሆይ ፣ ያለጥፋት ሰውን
የፈጠርኸው ፤
God, great eternal, Who did form man uncorrupt,
ሞተ ዘቦአ ቀዳሚ በቅንዓተ ሰይጣን አብጠልከ በምጽአቱ
ለሕያው ወልድከ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ
ክርስቶስ።
አስቀድሞ በሰይጣን ቅንዓት የገባውን ሞት ሕያው በሚሆን
ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ መምጣት አጠፋህ።
You did abolish death that came first through the envy
of Satan, by the advent of Your living Son our Lord,
and our God, and Saviour Jesus Christ,
ወመላዕከ ኵላ ምድረ ሰላመከ እንተ እምሰማያት እንተ ባቲ
ሠራዊተ ሰማያት ይሴብሑከ እንዘ ይብሉ ስብሐት
ለእግዚአብሔር በሰማያት ፤ ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ።
የሰማይ ሠራዊት እንዲህ እያሉ አንተን ያመሰገኑባትን ከሰማይ
የተገኘች ሰላምን በምድር ሁሉ መላህ። “በሰማይ ለእግዚአብሔር
ምሥጋና ይገባል ፤ በምድርም ሰላም የሰው ፈቃድ።”
and You did fill all the earth with Your peace which is
from heaven wherein the armies of heaven glorify You
saying : “Glory to God in heaven and on earth peace,
His goodwill toward men.”
ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ፤ ወሰላም በምድር ሥምረቱ
ለሰብእ።
በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል። በምድርም ሰላም ፤
የሰው ፈቃድ።
Glory to God in heaven and on earth peace, His
goodwill toward men.
ካህን(priest)
ኦ እግዚኦ በሥምረትከ ምላዕ ውስተ አልባቢነ ለኵልነ
ወአንጽሐነ እምኵሉ ደነስ ወእምኵሉ ምርዓት ፤ ወእምኵሉ ቂም
ወቅንዓት ፤ ወእምኵሉ ምግባር ሕሱም ወእምተዘክሮ እከይ
እንተ ታለብስ ሞተ።
አቤቱ ፈቃድህን በሁላችን ልቡና ሙላ ፤ ከኃጢአትም ሁሉ
ከጽርዓትም ሁሉ አንጻን። ከቂምና ከቅንዓት ሁሉ ፤ ከክፉም
ሥራ ሁሉ ሞትን ከምታለብስ ክፉን ነገር ከማሰብ አንጻን።
O Lord, in Your Goodwill fill the hearts of us all and
purify us from all corruption and from all excess, and
from all revenge and envy, and from all wrongdoing and
from the remembrance of ill which clothes with death.
ወረስየነ ለኵልነ ድልዋነ ከመ ንትአማኅ በበይናቲነ በአምኃ
ቅድሳት።
በተለየች እማኄ እርስ በርሳችን እጅ እንነሳ ዘንድ ሁላችንንም
የበቃን አድርገን።
And make us all meet to salute one another with a Holy
salutation.
ጸልዩ በእንተ ሰላም ፍጽምት ወፍቅር ተአምኁ በበይናቲክሙ
በአምኃ ቅድሳት።
ፍጽምት ስለምትሆን ሰላምና ፍቅር ጸልዩ። እርስ በእርሳችሁ
በተለየች ሰላምታ እጅ ተነሣሡ።
Pray for the perfect peace and love. Salute one another
with a Holy salutation.
ክርስቶስ አምላክነ ረስየነ ድልዋነ ከመ ንትአማኅ በበይናቲነ
በአምኃ ቅድሳት።
አምላካችን ክርስቶስ ሆይ እርስ በርሳችን በተለየች ሰላምታ
እጅ እንነሣሣ ዘንድ የበቃን አድርገን።
Christ our God, make us meet to salute one another
with Holy salutation.
ወንትመጦ እንበለ ኵነኔ እምሀብትከ ቅድስት እንተ ይእቲ
እንበለ ሞት ሰማያዊት በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ።
ክብርት ከምትሆን ስጦታህ ሳይፈረድብን እንቀበል። ይህችውም
የማታልፍ ሰማያዊት ናት።
And to partake, without condemnation, of Your Holy
immortal heavenly gift, through Jesus Christ our Lord:
ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ፤ ከርሱ
ጋራ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ለአንተ ምስጋና ይገባል ዛሬም
ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Through whom to You with Him and with the Holy Spirit
be glory and dominion, both now and ever and world
without end. Amen.
አኮቴተ ቁርባን ዘቅዱስ ቄርሎስ። ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ
ኵልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን።
የቅዱስ ቄርሎስ የቁርባን ምስጋና። ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን
ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
The Anaphora of St. Cyril, may his prayer and
blessing be with us all Christian people, world without
end.
እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
The Lord be with you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with your spirit.
አእኵትዎ ለአምላክነ።
አምላካችንን አመስግኑት።
Give thanks unto our God.
ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባዋል።
It is right, it is just.
አልዕሉ አልባቢክሙ።
ልቡናችሁ ሰማያዊ ነገርን ያስብ።
Lift up your hearts.
ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ።
በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ አለን።
We have lifted them up unto the Lord our God.
ቡራኬ
Benediction
ኀቤከ እግዚኦ አምላከ አማልክት ወእግዚአ አጋእዝት አምላክ
ኅቡእ በህላዌሁ ዘኢይትዌለጥ ልዑል ውእቱ እምኵሉ ህላዌሁ
ዘኢይትረከብ።
የአማልክት አምላክ የአጋዕዝት ጌታ አቤቱ ወዳንተ አነዋወሩ
የማይፈጸም ኅቡእ አምላክ ከሁሉ ይልቅ ልዑል ነው አነዋወሩ
የማይገኝ ነው።
The Lord, God of gods, Lord of Lords, the invisible God,
whose existence is unsearchable, is higher than all, yes,
His nature is unsearchable.
እሳት በላዒ ፤ ወእሳት ማሕየዊ ፤ አምላከ አማልእክት
፤ወእግዚአ አጋእዝት ፤ ዘመልዕልተ ሰማያት መንበሩ ወምድር
መከየደ እገሪሁ ልዑል ወምጡቅ ዘውስተ ብርሃን የኀድር።
የሚያቃጥል እሳት ፤ የሚያድንም እሳት ፤ የአማልክት አምላክ
የጌቶችም ጌታ ነው። ዙፋኑ ከሰማያት በላይ የእግሩም
መመላለሻ ምድር ነው። በብርሃን የሚኖር ልዑል ምጡቅ ነው።
He is consuming fire, the life-giving fire, the God of gods
and the Lord of lords whose throne is above the
heavens and whose footstool is the earth; He is high
and far away and dwells in light.
ልዑል ወግኑዝ ዘበሰማያት ፤ ማኅደሩ ልብሰ እሳት ዘይትዐፀፍ
ወሥርግው በነደ እሳት ዘዲበ አርእስተ እሳት መንበሩ ወዲበ
አየር ዘኢይትገሠሥ ነሶሳዉ።
በሰማይ ያለ ፤ ማደሪያው ሥውር ልዑል ነው ፤ የእሳት
መጐናፀፊያ የሚጐናፀፍ በነደ እሳትም ያጌጠ ነው ፤ ዙፋኑ
ከእሳት አለቆች በላይ የሚሆን መመላለሻው በማይዳሰስ በአየር
ላይ።
High and invisible is He who dwells in heaven. He is
clothed in garments of fire and adorned with flames of
fire; His throne is on the heads of fire; His going to and
from is through impalpable air;
ወበሰማይ ልዑል ጠፈሩ ፤ ደመናት መንኵራኵሩ ፤ ወዲበ
መንኵራኵረ (ማዕበል) ባሕር ፍኖቱ ወውስተ አርእስተ እሳት እለ
ይትለአክዎ ይሠሩ።
ጠፈሩም በልዑል ሰማይ ፤ መንኰራኵሩ ደመና ፤ ጎዳናውም
በባሕር ማዕበል ላይ በሚላኩት በእሳት አለቆችም ነው።
His high firmament is in heaven; clouds are His chariot;
His was is in the stormy sea and on the heads of fire
who minister Him.
ዲያቆን (Dacon)
እለ ትነብሩ ተንሥኡ።
የተቀመጣችሁ ተነሡ።
You, that are sitting, stand up.
በ፪ኤ ክነፊሆሙ ዘእሳት ይከድኑ ገጾሙ ከመ ኢይብልዖሙ
እሳት በላዒ ፤ ወበ፪ኤ ክነፊሆሙ ዘጸዳል ይከድኑ እግሮሙ ከመ
ኢይዝብጦሙ ጸዳሉ ግሩም።
የሚያቃጥል እሳት እንዳያቃጥላቸው በሁለቱ የእሳት ክንፋቸው
ፊታቸውን ይሸፍናሉ ፤ ግሩም የሚሆን ብርሃኑ (ነበልባሉ)
እንዳይመታቸው በሁለት የብርሃን ክንፋቸው እግራቸውን
ይሸፍናሉ።
With their two wings of fire they cover their face that the
consuming fire may not consume them; with their two
luminous wings they cover their feet that His terrible light
may not burn them;
ወበ፪ኤ ክነፊሆሙ ዘመንፈስ ይሠሩ እስከ አጽናፈ ዓለም።
ሱራፌል በአርእስቲሆሙ ፤ ወኪሩቤል በቅዳሴሆሙ
ረቂቅ በሚሆን ሁለት ክንፋቸው እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣሉ።
ሱራፌል በአለቆቻቸው ፤ ኪሩቤልም በምስጋናቸው
and with their two spiritual wings they fly unto the ends
of the world. Seraphim together with their leaders,
Cherubim according to their sanctification,
መላእክት በበሥርዓቶሙ ፤ ወትጉሃን በበሠራዊቶሙ ፤ ሊቃናት
ትጉሃን በበፆታሆሙ ፤ መላእክተ እሳት በጸዳሎሙ ፤
መንፈሳዊያን በበህላዌሆሙ የአኵቱ ወይቄድሱ በግሩም ቃል።
መላእክትም በየሥርዓታቸው ፤ ትጉሃን በየሠራዊታቸው የትጉሃን
አለቆች በየወገናቸው ፤እሳትነት ያላቸው መላእክት በብርሃናቸው
መንፈሳዊያን በአነዋወራቸው ግሩም በሚሆን ቃል ያመሰግናሉ።
the angels in their ranks, the watchful according to their
tribes, the angels of fire according to their light, and the
spiritual according to their position – give thanks and
hallow with terrible voice,
ይጸርሑ ወይብሉ በቃል ዐቢይ ወልዑል ፤ ወእንዘ ይቄድሱ
ከመዝ ይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባኦት ፍጹም
ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
ይቀድሳሉ ከፍ ባለና በታላቅ ቃል ይጮሃሉ። ሲያመሰግኑም
እንዲህ ይላሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር
የጌትነትህ ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው።
cry aloud and on high, and while sanctifying they say:
Holy Holy Holy, perfect Lord of hosts, heaven and earth
are full of the holiness of the glory.
አውሥኡ።
ተሰጥኦውን መልሱ።
You answer.
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ
ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር
የጌትነትህ ምስጋና በሰማይ የመላ ነው።
Holy Holy Holy, perfect Lord of hosts, heaven and earth
are full of the Holiness of Your Glory.
ወንሕነኒ ንብል ምስሌሆሙ ኅቡረ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
እግዚአብሔር ቅዱስ አንተ ወግሩም ቅድሳተ ስብሐቲከ አቡሁ
ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
እኛም ከእነርሱ ጋራ በአንድነት “የጌታችንና የአምላካችን
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት አንተ ቅዱስ ነህ
የጌትነትህም ምስጋና ግሩም ነው” እንላለን።
And we say together with them, “You are Holy; and
wonderful is the holiness of Your glory, Father of our
Lord and our Saviour Jesus Christ.”
ዘውእቱ ባሕቲቱ ዘበአማን ወልድከ ወአንተ ባሕቲትከ አቡሁ
በጽድቅ፤
ይኸውም ብቻውን በእውነት ልጅህ ነው ፤ አንተም ብቻህን
በእውነት አባቱ ነህ።
Truly He alone is Your Son, and You alone truly are
His Father.
ኢይትረከብ ልደቱ እምኔከ ፤ ዘከመ አልቦቱ ጥንት ለህላዌከ ሎቱ
ለወልድከ አልቦቱ ጥንት ፤ ወአልቦቱ ተፍጻሜት። ወበከመ
አልቦቱ ጥንት ለመዋዕሊከ አልቦቱ ጥንት ለመዋዕሊሁ።
ከአንተ መወለዱ አይገኝም። ለአነዋወርህ ጥንት እንደሌለው
ለርሱም ለልጅህ ጥንት የለውም ፤ ፍጻሜም የለውም።
ለዘመንህም ጥንት እንደ ሌለው ለዘመኑ ጥንት የለውም።
His birth from You is unsearchable. As Your existence
has no beginning so Your Son has neither beginning nor
end; and as Your days have no beginning his days also
have no beginning.
አልቦ ዘይነብር በየማንከ ዘእንበለ ወልድከ ዘእምኔከ ተወልደ።
ወአልቦ ዘይነብር ዲበ መንበርከ አላ አርኣያከ ዘከማከ
ወአምሳሊከ።
ከአንተ ከተወለደ ከልጅህ በቀር በቀኝህ የሚቀመጥ የለም።
በዙፋንህም ላይ የሚቀመጥ የለም እንደ አንተ ያለ አርኣያህና
አምሳልህ ነው እንጂ።
None sits at Your right hand except Your Son born from
You, and none sits on Your throne but Your image that
is like You and is Your likeness.
ወውእቱ ወልድከ ወመልአከ ምክርከ ወፍቁርከ ዘእምኔከ
አምሳሊከ ወመልክዕከ ሕሊናከ ወኃይልከ ጥበብከ ወምክርከ
የማንከ ወመዝራዕትከ አምላክ ዘበአማን ዘእምህላዌከ ዘበአማን
ይኸውም ልጅህ የምክርህ አበጋዝ ነው ከአንተ የተገኘ ወዳጅህ
አምሳልህና መልክህ ሕሊናህና ኃይልህ ጥበብህና ምክርህ ቀኝህና
ክንድህ ከእውነተኛ ባሕርይህ የተወለደ እውነተኛ አምላክ
He is Your Son and the messenger of Your counsel,
Your beloved who is of You, Your image, Your
appearance, Your mind Your power, Your wisdom, Your
counsel, Your right hand, and Your arm; He is true God
from Your essence,
ተወልደ ወልድ ዋሕድ። ወሠረቀ እምህላዌከ ቃል ፍጹም
በኵሉ ዘእምኔከ ተወልደ አርኣያ ዚአከ ወዕሩይ ፤
ወልድ ዋሕድ ነው። በሁሉ ፍጹም የሚሆን ቃል ከባሕርይህ
ወጣ ፤ ከአንተ የተወለደ አርኣያህ ከአንተ ጋራ የሚተካል ፤
the only Son truly begotten. He was born from Your
essence, the Word perfect in all who is Your image
born from You and equal to You;
ዘከማከ ልዑል ወግሩም ዘምስሌከ ይሰግዱ ሎቱ መላእክት
ወሊቃነ መላእክት። ዘበአፍቅሮትከ ሰብአ ፈነውኮ ኀቤነ እስመ
አፍቀርከነ።
ከአንተ ጋራ ልዑል ግሩም የሚሆን ፤ መላእክትና የመላእክት
አለቆች ይሰግዱለታል። ሰውን በመውደድህ ወደኛ ሰደድኸው
ወደኸናልና።
He is like You high and wonderful. Angels and
archangels worship Him; through Your live to man You
did send Him to us because You have loved us.
አትሒቶ ርእሶ ውእቱ ቤዘወነ ዘተወልደ እምኔከ ዘከማከ ፤
ተወልደ እምኔነ በአምሳሊነ ዘውእቱ አርኣያ ዚአከ። ወአንሶሰወ
ማእከሌነ ዝኩ በአምሳሊነ ዘዕሩይ ፍጻሜሁ ምስሌከ ወአርኣያ
ዚአከ ውእቱ ዘከማከ።
እርሱ ራሱን አዋርዶ አዳነን ከአንተ የተወለደ እንዳንተ የሆነው
በእኛ አምሳል ከእኛ ተወለደ ፤ ይኸውም የሚመስልህ ነው። ይህ
በእኛ አምሳል በመካከላችን ተመላለሰ ፤ ፍጹምነቱ ከአንተ ጋራ
የሚተካከል የሚመስልህና እንዳንተ ያለ እርሱ ነው።
Humbling Himself He redeemed us. He who was born
from You and is like You was born from us in our
likeness which is Your image. He, who is perfect like
You and is Your image, walked among us in our image.
ወውእቱ ነገረነ በእንተ ህላዌከ። ወኮነ ሥጋ ከማነ ወሐመ ካዕበ
በፈቃዱ ዘያደነገፆሙ ለሱራፌል እምአርያም።
የአነዋወርህን ነገር እርሱ ነገረን። እንደ እኛ ሥጋ ሆነ
ዳግመኛም በአርያም ሱራፌልን የሚያስደነግፃቸው እርሱ
በፈቃዱ ታመመ።
He told us about Your being, and was made flesh like
us. He who overawes the Seraphim from the highest
heaven suffered at his own will.
ርኢናሁ ወመነንናሁ ፤ ከመ ዐቢይ ውእቱ በኀቤከ እግዚእ
ወስቡሕ በኀቤነ።፡ወሥውር ውእቱ እምትጉሃን ፤ በአማን
አስተርአየ ገሃደ ተወሊዶ እምህላዌነ።
አይተን አቃለልነው ፤ በአንተ ዘንድ ገናና እንደ መሆኑ መጠን
በእኛ ዘንድ ጌታ የተመሰገነ ነው። ከትጉሃንም የተሠወረ ነው ፤
ከእኛ ባሕርይ ተወልዶ በእውነት ተገልጦ ታየ።
We saw Him and despised Him who is great before You.
He is the glorious Lord among us; yet He is hidden from
the watchful. Truly He appeared, and was born openly of
our nature.
ኪያከ ይመስል በአርኣያ ወበፀዳል። ተሰብአ ወተመሰለ በሥጋነ።
ወበአርኣያነ ነበረ ኀቤነ። ወስቡሕ ውእቱ ዘከማከ። ሠረረ ወወረደ
ኀቤነ ወተፅዕለ ከማነ። ሠረረ ወዐርገ ኀቤከ ወክቡር ውእቱ
ዘከማከ።
በመልክ በብርሃን አንተን ይመስላል። ሰው ሆኖ ሥጋችንን
መሰለ። በእኛም አምሰሳል ከእኛ ዘንድ ኖረ። እንደ አንተም
የተመሰገነ ነው። ወጣ ወደ እኛም ወረደ እንደ እኛ ተሰደበ።
ወጣ ወደ አንተም ዐረገ እንዳንተም የከበረ ነው።
He resembles You in image and appearance; was made
man, came in the likeness of our flesh; lived among us
in our image, and He is glorious like You.
ዘየአኵትዎ ትጉሃን በሰማያት ተቀጸለ አክሊለ ዘሦክ ወዲበ ዕፀ
መስቀል ምስለ ፈያት ተሰቅለ። ዘያቴሕቱ ርእሶሙ ልዑላን
ቅድሜሁ በፍርሃት አትሐተ ርእሶ ቅድመ ሰቃልያን ለሕማም።
ትጉሃን በሰማያት የሚያመሰግኑት እርሱ የእሾህ ዘውድ ደፋ
ከወንበዴዎችም ጋራ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቀለ። ልዑላኑ እየፈሩ
በፊቱ ራሳቸውን የሚያዋርዱለት እርሱ በሚሰቅሉት ፊት
ለሕማም ራሱን አዋረደ።
He, to whom the watchful give thanks in heaven, was
crowned with a crown of thorns and was crucified on the
tree of the cross with thieves. He, before whom the high
ones bow their heads in awe, bowed His head before
the crucifiers to suffer.
ለጸዋሬ ሰማያት ወምድር ፆሮ ዕፅ ድኩም ዲበ ዕፀ መስቀል
ለዘእምኔሁ ይርዕዱ ሰማያት ወምድር አግመሮ መቃብር ጸባብ
አመ ተቀብረ ዲቤሁ።
ሰማይንና ምድርን የተሸከመውን በዕፀ መስቀል ላይ ደካማ
ዕንጨት ተሸከመው ሰማይና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ጠባብ
መቃብር በተቀበረበት ጊዜ ወሰነው።
A weak tree carried Him who carries heaven and earth.
A narrow grave limited Him, before whom heaven and
earth tremble, when He was buried in it.
ዘአስተጋብእ አጽናፈ ምድር በእራኁ ወዘዘገነ አብሕርተ ዓለም
በሕፍኑ ጠብለልዎ በሰንዱናት ወቀበርዎ ውስተ መቃብር ዘ፫ቱ
እመቱ ወሰፍሐ ርእሶ ክቡረ ወተመልዐ እምኔሁ መቃብር።
የዓለምን ዳርቻ በመኻል እጁ የሰበሰበውን የዓለምንም ባሕር
በእፍኙ የዘገነውን በበፍታ ገንዘው በሦስት ክንድ ከስንዝር
መቃብር ቀበሩት ክቡር ራሱን ዘረጋ ከእርሱም የተነሣ መቃብር
ተመላ።
He who gathered the ends of earth in His palm and held
the seas of the world in His palm and held the seas of
the world in the hollow of His hand they wrapped with
linen cloths and buried in a grave of three cubits.
ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ወቦአ ኀበ ሀለዉ
አርዳኢሁ እንዘ ዕፅው ኆኅት ፤ ወወፅአ እምኀበ አርዳኢሁ።
በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ደቀመዛሙርቱም
ወዳሉበት ደጅ ተዘግቶ ሳለ ገባ። ከደቀ መዛሙርቱም ተለይቶ
ወጣ።
He stretched forth His honourable head and the grave
was filled with Him. He rose from the dead on the third
day and entered where His disciples were His disciples
were while the door was closed, and then departed from
His disciples.
ወእንዘ ሀሎ ህየ ከደነ ሰማያተ ስኑ ወዐርገ ሰማያተ ወነበረ
በየማነ አቡሁ ወኮነ ሰማይ መንበሮ ወምድር ወከየደ እገሪሁ።
በዚህም ሳለ ጌትነቱ ሰማያትን መላ ወደ ሰማይም ዐረገ
በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ሰማይ ዙፋኑ ሆነ ምድርም የእግሩ
መመላለሻ።
While He was there His glory covered the heaven, sat
at the right hand of His Father, heaven became His
throne and the earth His footstool.
ወይመጽእ ዳግመ ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ወያንጐደጕድ
በላዕሉ ወያድለቀልቅ ቃሉ መሠረታተ ምድር ወይወፅኡ ኀቤሁ
ዳግመኛም ሕያዋንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ ይመጣል ፤ ከላይ
ነጐድጓዱ ይሰማል ፤ ቃሉም የምድርን መሠረት ያናውጣል ፤
He will come again to judge the living and the dead, He
will thunder above and hHs voice will shake the
foundations of the earth,
ሙታን እመቃብሪሆሙ ዘሎቱ ስብሐት ወክብር ምስለ አቡሁ
ወምስለ መንፈስ ቅዱስ ለዓለመ ዓለም።
ሙታንም ከመቃብራቸው ወደርሱ ይመጣሉ ከአባቱ ከመንፈስ
ቅዱስም ጋራ ክብር ምስጋና ለዘላለሙ የርሱ የሚሆን።
and the dead will come out unto Him from their graves,
to whom be glory and honour together with His Father
and the Holy Spirit, world without end.
ውስተ ጽባሕ ነጽሩ።
ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ።
Look to the east.
እወ እግዚኦ ዘታነሥእ ኵሎ በቃልከ ፤ ወሙታነ እለ አንሣእከ
በሞትከ። ወእምከሐድያን እለ አምኑ በመስቀልከ ወእምስሑታን
እለ ተመይጡ በቅትለትከ ወእምርኩሳን እለ ተቀደሱ
አቤቱ በእውነት በቃልህ ሁሉን በሞትህ ያስነሣሃቸው ሙታንንም
የምታስነሣ አንተ ነህ። ከከሐድያንም ወገን በመስቀልህ ያመኑብህ
ከስሑታንም ወገን በመሞትህ የተመለሱ በኃጢአት ከተዳደፉት
Yes, Lord, it is You who raise all with Your word, who
raised the dead through Your death. There are among the
unbelievers those who believed in Your cross, there are
among the sinners those who returned through Your
በሕማምከ ወእሙታን እለ አንሣእከ በትንሣኤከ ወአምኑ ብከ እለ
ተጋብኡ ለኵነኔ ዚአከ። ወአርኀውከ ኆኃተ ሐፂን ወታነሥኦሙ
ለእለ በልየ ሥጋሆሙ ውስተ መቃብር ወታነቅሖሙ
ወገን በመከራህ የተቀደሱ ከሙታንም ወገን በትንሣኤህ
ያስነሣሃቸው በአንተ ለመፍረድ ከተሰበሰቡ ወገን ያመኑብህ
የብረትን መዝጊያ ከፍተህ ሥጋቸው በመቃብር የጠፋውን
death, there are among the unclean those who were
sanctified through Your suffering, there are among the
dead those whom You did raise through your
resurrection, and among those who were gathered
together to judge You there were those who believed in
You.
ለእለ ኖሙ በሕይወቶሙ። ወታነሥኦሙ ለእለ ሰከቡ ውስተ
መሬት። ወታግዕዞሙ ለአግብርት ኃጥኣን። ወታጸድቆሙ ለእለ
ረስሑ በምሕረትከ።
ታስነሣቸዋለህ። በሕይወታቸው ያንቀላፉትን ታነቃቸዋለህ።
በመሬት የተኙትንም ታስነሣቸዋለህ። ኃጥኣን ባሮችን ነፃ
ታደርጋቸዋለህ። የተዳደፉትን በምሕረትህ ታከብራቸዋለህ።
You did open the iron gate and will raise those whose
bodies waxed old in the grave, and will awaken those
who fell asleep in their life time, and will raise those
lying in the earth, and will set free the sinful slaves, and
will justify through Your mercy those who were defiled.
በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ። (፫ ጊዜ )
አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን
አይሁን። (፫ ጊዜ)
According to Your mercy, our God, and not according to
our sins. (three times)
ወታስተናሥኦሙ ለዐላውያን በሣህልከ። ወታጸንዖሙ ለእለ
ተመይጡ በቃልከ። ወትመይጦሙ ለዐላውያን ፤ ከመ ይሑሩ
ውስተ ፍኖትከ ወለዝርዋን ታስተጋብኦሙ ከመ ይባኡ ውስተ
በይቅርታህ ዐላውያንን አንድ ታደርጋቸዋለህ (ታስማማቸዋለህ)።
የተመለሱትን በቃልህ ታጸናቸዋለህ። በጎዳናህ ይሄዱ ዘንድ
ዐላውያንን ትመልሳቸዋለህ ፤ ወደ ቦታህ ይገቡ ዘንድ የተበተኑት
through Your mercy You reconcile the heretics,
strengthen with You word those who return to You,
cause the heretics to return that they may walk in Your
way, gather the scattered to enter into Your paradise.
ዐጸድከ። ወለእለ ስሕቱ እምውስተ ሕዝብከ ትመይጦሙ ውስተ
ዘዚአከ ሃይማኖት። አንተ እግዚኦ ታጸንዖሙ ለድኩማነ መንፈስ
ከመ ያእምሩከ ኵሎሙ እለ ይነብሩ ውስተ ምድር፡፡
ትሰበስባቸዋለህ። ከወገኖችህ የበደሉትን አንተን ወደ ማመን
ትመልሳቸዋለህ። የመንፈስ ደካሞችን አቤቱ አንተ ታጸናቸዋለህ
በምድር የሚኖሩ ሁሉ አንተ አምላክ እንደሆንህ ያውቁህ ዘንድ።
Those among Your people who committed sin You cause
to return unto Your faith. O Lord, You strengthen the
weak in spirit that all who live on earth may know You
are God
ከመ አንተ ውእቱ አምላክ ወዘፈነውኮ ወልድከ ኢየሱስ ክርስቶስ
ወልድከ ወፍቁርከ ዘታፈቅር ዘእምኔከ ተወልደ ዘለከ ምስሌሁ
ስብሐት ወምስለ መንፈስ ቅዱስ ሥዉር ለዓለመ ዓለም።
ከአንተ የተወለደ የምትወደው ልጅህና ወዳጅህ የላክኸው ኢየሱስ
ክርስቶስንም ከርሱ ጋራ ክብር ያለህ ሥውር ከሚሆን ከመንፈስ
ቅዱስም ጋራ ለዘላለሙ።
and know Your Son Jesus Christ whom You did send,
Your beloved Son whom You love and who was born
from You . Glory be to You with him and with the
invisible holy Spirit, world without end.
ንነጽር።
እናስተውል።
Let us give heed.
ናቄርብ ለከ ዘንተ ቊርባነ ንጹሐ ወቅዱሰ በቅድሜከ። በእንተ
አቤል ወሴት ወሄኖስ ወመልከ ጼዴቅ ፤ በእንተ አብርሃም ፤
ይስሐቅ ወያዕቆብ ፤ በእንተ ሙሴ ወአሮን ወኵሎሙ ነቢያት።
ይህን ንጹሕ ቅዱስ መሥዋዕት በፊትህ እናቀርብልሃለን ስለ
አቤልና ስለ ሴት ፤ ስለ ሄኖስ ፤ ስለ መልከ ጼዴቅም ፤ ስለ
አብርሃም ስለ ይስሐቅና ስለ ያዕቆብ ፤ ስለ ሙሴና ስለ አሮን
ስለ ነቢያትም ሁሉ።
We offer before You this pure and holy offering for the
sake of Abel, Seth, Enoch, and Melchisedec, for the
sake of Abraham, Isaac and Jacob, for the sake of
Moses, Aaron and all the prophets.
በእንተ ስምዖን ጴጥሮስ ወዮሐንስ መጥምቅ ወኵሎሙ ሐዋርያት
በእንተ ዳዊት ወሕዝቅያስ ወኢዮስያስ ወቈስጠንጢኖስ ንጉሥ
ወኵሎሙ ነገሥት እለ አዕረፉ በርትዕት ሃይማኖት፡፡
ስለ ስምዖን ጴጥሮስ ስለ ዮሐንስ መጥምቅም ስለ ሐዋርያም ሁሉ
ስለ ዳዊትና ስለ ሕዝቅያስ ስለ ኢዮስያስና ስለ ንጉሡ
ቈስጠንጢኖስ በቀናች ሃይማኖት ስለ ሞቱት ነገሥታት ሁሉ፡፡
For the sake of Simon Peter, John the Baptist and all
the apostles. For the sake of David, Hezekiah, Josiah,
King Constantine and all the kings who have gone to
their rest in the true faith.
ወበእንተ ኵሎሙ ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ወንፍቀ
ዲያቆናት ወአናጕስጢስ ወወራዙት ወደናግል ወበእንተ ኵሉ
ነፍስ እንተ ኀደረ ላዕሌሃ መንፈስ ቅዱስ ወተፈጸመ ላዕሌሃ
መንፈሰ ሕይወት።
ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ስለ ቀሳውስትና ስለ ዲያቆናት ስለ ንፍቅ
ዲያቆናትና ስለ አናጕስጢሳውያን ስለ ወራዙትና ስለ ደናግልም
ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በላይዋ ላይ ስላደረባትና የሕይወት መንፈስ
ስለ ተፈጸመላት ነፍስ።
For the sake of all the bishops, priests, deacons,
anagonastis deacon, young men and virgins. For the
sake of all souls in which the Holy Spirit dwelt and to
which the perfect Spirit of life was given.
ወበእንተ ኵላ መልክዕ እንተ ተለክአት በአምሳሊሁ ለእግዚእነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድከ ወፍቁርከ ዘታፈቅር።
በምትወደው በልጅህና በወዳጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
አምሳል ስለ ተቀረጸች መልክ ሁሉ።
For the Sake of all creatures formed after the likeness of
our Lord Jesus Christ Your beloved Son whom You love.
ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን እለ ተገብረ ሎሙ ዝንቱ ቊርባን
ወአብእዎሙ ውስተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንከ ወአቅረብዎሙ
ቅድመ ምሥዋዒከ ዐቢይ ወቅዱስ።
ይህ ቊርባን ስለተደረገላቸው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ
ስላገቧቸውና ደገኛ ቅዱስ ወደሚሆን ወደ ወሠዊያህ ፊት
ስላቀረቧቸው ቅዱሳንም ሁሉ።
For the sake of all Holy men for whom this offering has
been prepared and whom they have led unto Your holy
Church and have drawn near before Your great and holy
altar.
ወበእንተ ኵሎሙ ነጋድያን ወፈላሲያን እለ ሀለዉ ውስተ ኵሉ
ገጻ ለምድር በርትዕት ሃይማኖት ወወፅኡ እምዝንቱ ዓለም።
በቀናች ሃይማኖት በምድር ላይ ሁሉ ስለሚኖሩ ስለ
መንገደኞችና ስለ ስደተኞችም ሁሉ ከዚህ ዓለም የወጡ።
For the sake of all travelers and wanderers on the face
of the whole earth in true faith, and for the sake of
those who have departed from this world.
ወበእንተ ኵሉ አፍ ወልሳን እለ አምኑ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ወልድከ ወፍቅሩከ ዘታፈቅር ዘለከ ስብሐት ምስሌሁ
ወምስለ መንፈስ ቅዱስ ሥውር ለዓለመ ዓለም።
በምትወደው በልጅህና በወዳጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም
ስላመኑ አፍና አንደበት ሁሉ ከርሱ ጋራ ክብር ያለህ ሥውር
ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ለዘለዓለሙ።
For the sake of every mouth and tongue which believed
in the name of our Lord Jesus Christ Your beloved Son
whom You love. Glory be to You with Him and with the
invisible Holy Spirit, world without end.
በእንተ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ…………፣ ወብፁዕ
ጳጳስ አባ……………………...።
ብፁዕ ቅዱስ ስለሚሆን ስለ ርእሰ ጳጳሳት ስለ አባ………………
ብፁዕም ስለሚሆን ስለ አባ ………
For the sake of the blessed and holy Patriarch Abba
............ and the
blessed Archbishop Abba ......…………..
እንዘ የአኵቱከ በጸሎቶሙ ወበስእለቶሙ እስጢፋኖስ ቀዳሜ
ሰማዕት ዘካርያስ ካህን ወዮሐንስ መጥምቅ።
በጸሎታቸውና በልመናቸው ሲያመሰግኑህ የሰማዕታት
መጀመሪያ እስጢፋኖስ። ካህኑ ዘካርያስና መጥምቁ ዮሐንስ
While they yet give thee thanks in their prayer and in
their supplication: Stephen the first martyr, Zacharias the
priest and John the Baptist.
ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሰማዕት እለ አዕረፉ በርትዕት
በሃይማኖት ማቴዎስ ወማርቆስ ሊቃስ ወዮሐንስ ፬ቱ
ወንጌላውያን። ማርያም ወላዲተ አምላክ። …….
በሃይማኖት ስላረፉ ስለ ቅዱሳንና ስለ ሰማዕታት ሁሉ፤ አራቱ
ወንጌላውያን ማቴዎስና ማርቆስ ሉቃስና ዮሐንስ፤ አምላክን
የወለደች ማርያም።…….
And for the sake of all the saints and martyrs who have
gone to their rest in faith Matthew and mark, Luke and
John the four Evangelist; Mary the mother of God,…….
ኦ ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ባርክ ዲበ
ሕዝብከ ፍቁራን ክርስቶሳውያን በበረከተ ሰማያውያን
ወምድራውያን ወፈኑ ላዕሌነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ።
ልዩ ሦስት የምትሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የሚፋቀሩ
የክርስቶስ ወገኖች የሚሆኑ ሕዝብህን በሰማያውያንና ምድራውያን
በረከት ባርክ። በእኛ ላይም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላክ።
O; Holy Trinity Father and Son and Holy Spirit, bless
Your people, Christians beloved, with blessings heavenly
and earthly and send upon us the grace of the Holy
Spirit
ወረሲ ኀዋኅወ ቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት ርኅዋተ ለነ በምሕረት
ወበአሚን ወፈጽም ለነ አሚነ ሥላሴከ ቅድስት እስከ ደኃሪት
እስትንፋስ።
የቅድስት ቤተ ክርስቲያንህም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት
እንዲከፈቱ አድርግልን እስከ መጨረሻዪቱ ሕቅታም ድረስ ልዩ
ሦስትነትህን ማመንን ፈጽምልን።
and make the doors of Your Holy Church open unto us
in mercy and in faith; and perfect unto us the faith of
Your Holy Trinity unto our latest breath .
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐውጽ ሕሙማነ ሕዝበከ ፈውሶሙ
ወምርሖሙ ለአበዊነ ወለአኀዊነ እለ ሖሩ ወተአንገዱ ወሚጦሙ
ኀበ ማኅደሪሆሙ በሰላም ወበጥዒና ባርክ ነፋሳተ ሰማይ።
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የታመሙ ወገኖችህን ጐብኝ
የሄዱትንና እንግዶች የሆኑትን አባቶቻችንን ወንድሞቻችንን
መርተህ በሰላምና በጤና ወደ ቤታቸው መልሳቸው። የሰማዩን
ነፋስ ባርክ።
O my Lord Jesus Christ visit the sick of Your people;
heal them; and guide our fathers and our brothers who
have gone forth and become strangers bring them back
to their dwelling places in peace and in health. Bless the
airs of heaven
ወዝናማተ ወፍሬያተ ምድር ዘዛቲ ዓመት በከመ ጸጋከ ወረሲ
ፍግዓ ወተድላ ወትረ ዲበ ገጻ ለምድር ወአጽንዕ ለነ ሰላመከ
ሚጥ ልበ ነገሥት አዚዛን ለአሠንዮ ላዕሌነ በኵሉ ጊዜ።
ዝናሙንም በዚህች ዓመት የሚያፈራውን የምድሩን ፍሬ እንደ
ቸርነትህ ባርክ ዘወትር ተድላንና ደስታን አድርግ ሰላምህንም
አጽናልን ሁልጊዜ ለኛ በጎ ነገርን ሊያደርጉልን ጽኑዓን የሚሆኑ
የኃያላኑን ልቡና መልስ።
and the rains and the fruits of the earth of this year, in
accordance with Your grace, and make joy and gladness
prevail perpetually on the face of the earth And establish
for us Your peace. Turn the hearts of mighty kings to
deal Kindly with us always.
ጸጉ ሰላመ ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲን እለ ጉቡኣን ውስተ ቤተ
ክርስቲን ቅድስት ኵሎ ጊዜ ለኵሉ ለለአሐዱ በበአስማቲሆሙ
በቅድመ ኃያላን አምላክነ አንኅ ሎሙ።
በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ ሁል ጊዜ ለሚሰበሰቡ ለቤተ
ክርስቲያን ሊቃውንት ፍቅርን ስጥ ለሁሉም ለያንዳንዱ
በየስማቸው ኃያላን በሚሆኑ ፊት ሰላምን አብዛላቸው።
Grant peace of the scholars of the church who are
continually gathered in Your Holy Church; to all, to each
by their own names; in the presence of powerful kings, O
our God, increase Your peace,
ወአዕርፍ ነፍሳተ አበዊነ ወአኀዊነ ወአኃቲነ እለ ኖሙ ወአዕረፉ
በርትዕት ሃይማኖት።
አምላካችን ሆይ በቀናች ሃይማኖት ሆነው ያንቀላፉትንና
ያረፉትን ያባቶቻችንንና የወንድሞቻችንን የእኅቶቻችንንም ነፍስ
አሳርፍ።
Rest the souls of our fathers and our brothers and our
fathers and our brothers and our sisters who have fallen
asleep and gained their rest in the right faith.
ወባርክ ዲበ እለ ያስተነትኑ በዕጣን ወቊርባን ወወይን ወቅብዕ
ወዘይት ወመንጠዋልዕ ወመጻሕፍተ ምንባባት ወንዋያተ መቅደስ
ከመ ክርስቶስ አምላክነ ይዕሥዮሙ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት።
አምላካችን ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ዋጋቸውን
ይከፍላቸው ዘንድ ዕጣንና ቊርባን ወይንና ሜሮን ዘይትም
መጋረጃም የንባብ መጽሐፍቶችን የቤተ መቅደስንም ንዋያት
በመስጠት የሚያገለግሉትን ባርክ።
And bless those who give gifts of incense and bread and
wine, and ointment and lamp oil, and hangings and
reading books and vessels for the sanctuary, that Christ
our God may give them their reward in the heavenly
Jerusalem.
ወለኵሎሙ እለ ተጋብኡ ምስሌነ ይኅሥሡ ምሕረተ ክርስቶስ
አምላክነ ተሣሃል ላዕሌሆሙ ወለኵሎሙ እለ አምጽኡ ምጽዋተ
በቅድመ መንበርከ መፍርህ ወመደንግፅ ተወከፎሙ።
ይቅርታን ያገኙ ዘንድ ከእኛ ጋራ የተሰበሰቡትን ሁሉ
አምላካችን ክርስቶስ ሆይ ይቅር በላቸው በሚያስፈራና
በሚያስደነግጥ በመንበርህ ፊት ምጽዋት ያመጡትንም ሁሉ
ተቀበላቸው።
And all them that are assembled with us to entreat for
mercy: Christ our God have mercy upon them: and all
them that give alms before Your awful and terrifying
throne, receive.
ወአንኂ ለኵላ ነፍስ ዕፅብት ወእለ እሡራን በመዋቅሕት ወእለ
ሀለዉ ውስተ ስደት ወፂዋዌ ወእለ እኁዛን በቅኔ መሪር አምላክነ
አድኅኖሙ በምሕረትከ።
የተጨነቀችዪቱን ነፍስ ሁሉ አሳርፍ በሰንሰለት የታሰሩትን
በስደትና በምርኮ ያሉትንም መሪር በሆነ አገዛዝ የተያዙትንም
አምላካችን ሆይ በቸርነትህ አድናቸው።
And comfort every straitened soul, them that are in
chains and them that are in exile or captivity. And them
that are held in bitter servitude: our God, deliver them in
Your mercy.
ኦ ሊቅነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኵሎሙ እለ አዘዙነ ከመ ንዘከሮሙ
በጊዜ አስተብቊዖትነ ኀቤከ ተዘከሮሙ በመንግሥትከ ሰማያዊት
ወሊተኒ ለኃጥእ ገብርከ ተዘከረኒ።
መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ በምንማልድበት ጊዜ
እንድናስባቸው ያዘዙንን ሁሉ በሰማያዊት መንግሥትህ
አስባቸው፡፡ ኃጥእ ባርያህን እኔንም አስበኝ።
And all them that have entrusted it to us to remember
them in our supplications to You: Our Master Jesus
Christ, remember them in Your heavenly kingdom, and
remember me, Your sinful servant.
ኦ እግዚኦ አድኅን ሕዝበከ ወባርክ ርስተከ። ረዓዮሙ
ወአልዕሎሙ እስከ ለዓለም።
አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ። ጠብቃቸው እስከ
ዘላለምም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
O Lord, save Your people and bless Your inheritance
feed them and lift them up for ever.
መሐሮሙ እግዚኦ ወተሣሃሎሙ ለሊቃነ ጳጳሳት ፤ ጳጳሳት
ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ወኵሎሙ ሕዝበ
ክርስቲያን።
አቤቱ የጳጳሳት አለቆችን ፤ ጳጳሳቱንና ኤጲስ ቆጶሳቱን ፣
ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን ፤ የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ ማራቸው
፤ ይቅርም በላቸው።
Lord pity and have mercy upon the patriarchs, March
bishops, bishops, priest, deacons and all the Christian
people.
ሎሙኒ ወለኵሎሙ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ትሰግድ ለከ ቤተ ክርስቲያንከ ፤ ወታሌዕለከ መርዓትከ
በበቊዔቶሙ ለልዑላን ፤ በቅዳሴሆሙ ለሱራፌል ወበውዳሴሆሙ
ለነርሱም ለሁሉም ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ሆይ ቤተ ክርስቲያንህ ትሰግድልሃለች ሙሽራህም ከፍ
ከፍ ታደርግሃለች። በልዑላን ጥቅም ፤ በሱራፌል ቅዳሴና
For the sake of those and all, our Lord and our God
Jesus Christ, Your Church worships You and Your bride
exalts You with the goodness of the high ones, with the
Sanctification of the Seraphim, with the praise of the
Cherubim,
ለኪሩቤል ፤ ወበአኰቴቶሙ ለመላእክት ፤ ወበስእለቶሙ
ለትጉሃን ፤ ወበፍጻሜሆሙ ለቅዱሳን ፤ በንጽሑ ለአዳም
ወበመሥዋዕቱ ለኖኅ ፤
በኪሩቤል ውዳሴ ፤ በመላእክትም ምስጋና ፤ በትጉሃን ልመና ፤
በቅዱሳንም ፍጹምነት ፤ በአዳም ንጽሕና ፤ በኖኅም መሥዋዕት
with the thanksgiving of the angels, with the prayer of
the watchful and with the perfection of the saints: With
the purity of Adam, with the sacrifice of Noah,
ወበተወክፎሙ ፤ ለአብርሃም ወበኂሩቱ ፤ ለይስሐቅ
ወበአስተርእዮቱ ለያዕቆብ ፤ ወበመዋቅሕቲሁ ለዮሴፍ
በትዕግሥቱ ለኢዮብ ፤ ወበየውሃቱ ለሙሴ
በአብርሃም እንግዳ ተቀባይነት ፤ በይስሐቅ ቸርነት ፤ በያዕቆብ
መገለጽ ፤ በዮሴፍ እሥራት ፤ በኢዮብ ትዕግሥት ፤ በሙሴም
የዋህነት ፤
with the hospitality of Abraham. With the kindness of
Isaac and with the vision of Jacob: With the
imprisonment of Joseph, with the patience of Job, with
the meekness of Moses
ወበአፍቅሮቶሙ ለሐዋርያት ፤ ወበስእሎቶሙ ለቅዱሳን ፤
በፃማሆሙ ለፈላስያን ፤ ወበጽድቆሙ ለእለ ኢአበሱ ፤
በትሕትናሆሙ ለእለ አድምዑ ንጽሐ።
በኤልያስም ምስጋና ፤ በሐዋርያትም ማፍቀር ፤ በቅዱሳንም
ልመና በተሰደዱ ሰዎች ድካም ፤ ባልበደሉ ሰዎች ጽድቅ ፤
ንጽሕናን ባገኙ ሰዎች ትሕትና።
and with praise of Elijah: With the love of the apostles,
with the prayer of the saints, with the labour of the
anchorites, with the righteousness of the sinless, and with
the humility of the pure:
በገድሎሙ ለንጹሓን ፤ በሕርመቶሙ ለተአህራምያን ፤
ወበጽድቆሙ ለቅዱሳን ፍጹማን ፤ በርኅቀተ አጽናፈ ምድር ፤
ወበዕመቆሙ ለልጐታተ ባሕር ፤ በንጥረ መባርቅት ፤
በንጹሓን ገድል ፤ ከምግብ በተለዩ ሰዎች ትምህርት ፤ ፍጹማን
ስለሆኑ ቅዱሳን ጽድቅ ፤ በምድር ዳርቻ ርኅቀት ፤ በባሕር
አዝዋሪም ጥልቅነት ፤ በመባርቅት ብልጭታ ፤
With the courage of the pure, with the bereavement of
the bereaved, and with the righteousness of the perfect
saints: With the remoteness of the ends of the earth,
with the depth of the sea’s whirlpools, with the flesh of
lightening,
ወበሥረቶሙ ለደመናት ፤ በአኰቴቶሙ ለመላእክት
ወበስብሐቶሙ ለቅዱሳን ፤ በንጽሖሙ ለትጉሃን ወበቅድስናሆሙ
ለልዑላን ወበጸዳሎሙ ለመንፈሳውያን
በደመናትም መውጣት ፤ በመላእክት ምስጋና ፤ በቅዱሳንም
ምስጋና በትጉሃን ንጽሕና ፤ በልዑላንም መስማማት
በመንፈሳውያን ብርሃን
and with the flight of the clouds: With the thanks giving
of the angels, with the glory of the saint, with the purity
of the watchful, with the agreement of the high ones,
and with the light of the spiritual ones:
ወበየማኖሙ ለካህናት ፤ በቅትለቶሙ ለሰማዕታት ፤ ወበደሞሙ
ለመሃይምናን ወበዕበዮሙ ለመላእክት ብርሃናውያን፡፡
በካህናት ቀኝ ፤ በሰማዕታት መሞት ፤ በምእመናንም ደም ፤
በብርሃናውያን መላእክትም ገናንነት።
With the right hand of the priests, with the death of the
martyrs, with the blood of the believers, and with the
greatness of the luminous angels:
በጽፍዓቱ ለወልድከ ፤ ወበሕማማቲሁ ለዋሕድከ ፤ ወበሥልጣንከ
አኃዜ ኵሉ ፤ ወበጸሎት እንተ ተዐርግ ኀበ አቡሁ ለእግዚእነ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
በልጅህም መመታት (ተጸፍኦ) ፤ በአንድ ልጅህ ሕማማት ፤
ሁሉን በያዘ ሥልጣንህም ፤ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን
ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አባት በምታርግ ጸሎት።
With the striking of Your Son, with the suffering of Your
only One, and with Your authority which holds all: And
with the prayer which ascends to the Father of our Lord
and our Saviour Jesus Christ.
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። ተዘከረነ እግዚኦ ኦ
ሊቅነ በውስተ መንግሥትከ። ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ
መንግሥትከ።
አቤቱ በመንግሥትህ አስበን። ሊቅ ሆይ አቤቱ በመንግሥትህ
አስበን። አቤቱ በመንግሥትህ አስበን።
Remember us, Lord, in Your kingdom; remember us,
Lord, Master, in Your kingdom; remember us, Lord, in
Your kingdom,
በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ
መስቀል ቅዱስ።
ቅዱስ በሚሆን በዕፀ መስቀል ላይ ሳለህ ፈያታዊ ዘየማንን
እንዳሰብከው አቤቱ በመንግሥትህ አስበን።
as You did remember the thief on the right hand when
You were on the tree of the Holy Cross.
በይእቲ ሌሊት እንተ ባቲ አመ ያገብእዎ፤
እርሱን በያዙባት በዚያች ሌሊት፤
In the same night in which they betrayed Him,
አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስት።
ቀስውስት እጆቻችሁን አንሡ።
Priests, raise up your hands.
ነሥአ ኅብስተ በእደዊሁ ቅዱሳት ወብፁዓት እለ እንበለ ርስሐት
፤ አንቃዕደወ ሰማየ ኀቤከ ኀበ አቡሁ።
ክቡራትና ብፁዓት በሚሆኑ እድፍ በሌለባቸው እጆቹ ኅብስቱን
ያዘ ፤ ወደ አንተ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ አቅንቶ አየ።
He took bread in His Holy, blessed and spotless hands,
looked up unto heaven, towards You, His Father.
ነአምን ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
ይህ እርሱ እንደ ሆነ በእውነት እናምናለን።
We believe that this is He, truly we believe.
አእኰተ ፤ ባረክ ፤ ወፈተተ። ወይቤሎሙ ንሥኡ ብልዑ ዝ
ኅብስት ሥጋየ ውእቱ ለዘበእንቲአክሙ ይትፌተት ወይትወሀብ
ለቤዛ ኵሉ ዓለም በዘይትኀደግ ኃጢአት።
አመሰገነ ፤ ባረክ ፤ ቈረሰ ፤ አላቸውም ፤ “ንሡ ፤ ብሉ ይህ
ኅብስት ኃጢአት በሚሠረይ ገንዘብ ለዓለሙ ሁሉ ቤዛ ስለ
እናንተ የሚፈተት ሥጋዬ ነው።”
And said unto them, “Take, eat, this bread is My body
which will be broken for you as a propitiation for all the
world for the remission of sin.”
አሜን አሜን አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ
ወአምላክነ። ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
አሜን አሜን እናምናለን ፤ እንታመናለን። ጌታችንና
አምላክችን እናመሰግንሃለን ፤ ይህ እርሱ እንደሆነ በእውነት
እናምናለን።
Amen amen amen: We believe and confess, we glorify
You, O our Lord and our God; that this is He we truly
believe.
ወካዕበ እምድኅረ ተደሩ ነሥአ ጽዋዐ አእኰተ ፤ ባረከ ፤
ወቀደሰ።
ዳግመኛም ራታቸውን ከበሉ በኋላ ጽዋውን አንሥቶ ይዞ
አመሰገነ ፤ ባረከ ፤ አከበረም።
Again after they had supped, He took a cup, gave
thanks, blessed, hallowed
ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ
ዘሐዲስ ሥርዓት ለዘበእንቲአክሙ ይትከዐው ወይትወሀብ ለቤዛ
ኵሉ ዓለም ለኅድገተ ኃጢአት።
ደቀመዛሙርቱንም አላቸው ፤ “ንሡ ጠጡ ይህ ጽዋ ኃጢአትን
ለማስተሥረይ ስለእናንተ የሚፈስና ለዓለሙ ሁሉ ቤዛ የሚሰጥ
ሐዲስ ሥርዓት የሚሆን ደሜ ነው።”
and said unto His disciples, :Take, drink, this cup is My
blood of the new testament which will be shed for you
and given as a propitiation for all the world for the
remission of sin.”
አሜን አሜን አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ
ወአምላክነ። ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
አሜን አሜን እናምናለን ፤ እንታመናለን። ጌታችንና
አምላክችን እናመሰግንሃለን ፤ ይህ እርሱ እንደሆነ በእውነት
እናምናለን።
Amen amen amen: We believe and confess, we glorify
You, O our Lord and our God; that this is He we truly
believe.
እወ እግዚኦ አምላክነ ስምዖሙ ጸሎቶሙ ለአግብርቲከ
ወተወከፎሙ ለእለ ይሰግዱ ለከ እምቅድመ ገጽከ።
አቤቱ አምላካችን የባሮችህን ጸሎታቸውን በእውነት ስማቸው ፤
በፊትህ የሚሰግዱልህንም ተቀበላቸው።
Yes, Lord our God, hearken to the prayer of Your
servants and accept those who worship You before
Your face.
ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ ነአምን ዕርገተከ
ወዳግመ ምጽአተከ ንሴብሐከ ወንትአምነከ ንስእለከ
ወናስተበቍአከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ።
አቤቱ ሞትህንና ቅድስት ትንሣኤህን እንናገራለን። ዕርገትህን
ዳግመኛም መምጣትህን እናምናለን። እናመሰግንሃለን ፤
እናምንሃለንም። ጌታችንና አምላካችን ሆይ እንለምንሃለን
እንማልድሃለንም።
We proclaim Your death, Lord, and Your Holy resurrection;
we believe in Your ascension and Your second advent. We
glorify You, and confess You, we offer our prayer unto
You and supplicate You, O our Lord and our God.
ሜሎስ ሰይፈ እሳት ዘይነድድ ይትከሠት ፤ ወይትረኀው ሰማየ
ሰማያት በጽድቅከ ፤ ወበፈቃድከ ወይትፈኖ መንፈስከ ሕያው
ወቅዱስ ይረድ ወይምጻእ ወያዕርፍ ዲበ ዝንቱ ኅብስት ወጽዋዕ።
የሚነድ የእሳት ሰይፍ ሜሎስ(መንፈስ ቅዱስ) ይገለጽ ፤ ሰማየ
ሰማያትም በቸርነትህ ይከፈት በፈቃድህም ሕያውና ቅዱስ
መንፈስህ ይላክ ይውረድ ይምጣም በዚህም ኅብስትና ጽዋ ላይ
ይረፍ።
Let the flaming sword of fire, called “Melos” be drawn,
and let the heaven of heavens be opened, through Your
righteousness, and with Your will let Your living Holy
Spirit descend, come and rest upon this bread and cup,
ይባርክ ወይቀድስ ይኩን ሱታፌ ሥጋሁ ወደሙ ለዋሕድ
ወልድከ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ይባርከው ይቀድሰውም ከአንድ ልጅህ ከጌታችንና ከአምላካችን
ከመድኃኒታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ጋራ አንድ
bless and sanctify them to be the communion of the
body and blood of Your only-begotten Son, our Lord and
our God and our Savior Jesus Christ:
ከመ ይኩን ለኅድገተ አበሳ ለእለ ይቀርብዎ ፤ ወለሥርየተ
ኃጢአት ለእለ ይነሥእዎ።
ይሆን ዘንድ ለሚቀርቡት የበደል ማስተሥረያ ለሚቀበሉትም
የኃጢአት ይቅርታ ይሆን ዘንድ።
for the forgiveness of the iniquity to those who draw
near to it and remission of sin to those who partake of
it.
አሜን እግዚኦ መሐረነ ፤ እግዚኦ መሐከነ ፤ እግዚኦ
ተሣሃለነ።
አቤቱ ማረን ፤ አቤቱ ራራልን ፤ አቤቱ ይቅር በለን።
Amen; Lord have pity upon us, Lord spare us, Lord
have mercy upon us.
በኵሉ ልብ ናስተብቊዖ ለእግዚአብሔር አምላክነ ኅብረተ
መንፈስ ቅዱስ ሠናየ ከመ ይጸግወነ።
ያማረ የመንፈስ ቅዱስን አንድነት ይሰጠን ዘንድ በፍጹም ልብ
አምላካችንን እግዚአብሔርን እንማልደው።
With all the heart let us beseech the Lord our God that
He grant unto us good communion of the Holy Spirit.
በከመ ሀሎ ህልወ ወይሄሉ ለትውልደ ትውልድ ለዓለመ ዓለም።
በፊት እንደነበረ ለዘለዓለሙ ለልጅ ልጁ ይኖራል።
As it was, is and shall be unto generations of
generations, world without end.
ካህን (priest)
ወለኵሎሙ እለ በርትዕት ሃይማኖት ይሳተፉ ወይነሥኡ
እምኔሁ ይኩኖሙ ለሣህል ወለምሕረት ፤ ለፈውሰ ወለረድኤት
በቀናች ሃይማኖት አንድ ሁነው ከእርሱ ለሚቀበሉት ሰዎች
ሁሉ ለይቅርታና ለምሕረት ፤ ለደኅንነትና ለረድኤት ፣
And to all those who in true faith partake of it and
receive it may it be for mercy, compassion, healing,
ለሕይወተ ነፍስ ወሥጋ ፤ ለኅድገተ አበሳ ወለሥርየተ ኃጢአት
ወለትንሣኤ ሙታን ወለሕየወት ሐዲስ ለዓለመ ዓለም።
ለነፍስና ለሥጋ ሕይወት ይሁንላቸው። ለበደል ማስተሥረያ ፣
ለኃጢአት ይቅርታ ፣ ለትንሣኤ ሙታንና ለሐዲስም ሕይወት
ይሁንላቸው ለዘላለሙ።
help, life of soul and body, forgiveness of iniquity,
remission of sin, resurrection from the dead, and new
life, unto the ages of ages.
አሜን።
Amen.
ሀበነ ንኅበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ ፤ወፈውሰነ ፤ በዝንቱ
ጵርስፎራ ፤ ከመብከ ንሕየው ዘለኵሉ ዓለም ፤ ወለዓለመ
ዓለም።
የአንተ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ በዚሁም
በሥጋው በደሙ አድነን። ለዓለሙ ሁሉ በምትሆን በአንተ
ለዘለዓለሙ ሕያው እንሆን ዘንድ።
Grant us to be untied through Your Holy Spirit, and
heal us by this oblation that we may live in You for
ever.
ቡሩክ ስሙ ለእግዚአብሔር። ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ
እግዚአብሔር። ወይትባረክ ፤ ስመ ስብሐቲሁ ፤ ለይኩን ፤
ለይኩን ፤ ቡሩከ ለይኩን። ፈኑ ፤ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ።
የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው። በእግዚአብሔር ስም
የሚመጣውም ምስጉን ነው ፤ ጌትነቱም ይመስገን ይሁን
ይመስገን ይሁን። የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ላክልን።
Blessed be the name of the Lord, and blessed be He
that cometh in the name of the Lord, and Let the name
of His Glory be blessed. So be it, so be it, so be it
blessed. Send the grace of the Holy Spirit upon us.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ጸሎተ ፈትቶ
የመፈተት ጸሎት
“ Prayer Of Fraction”
ወካዕበ ናስተበቊዕ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ኀቤከ እግዚኦ አንቃዕዶነ
አዕይንተነ እንዘ ንትሜነይ ርደተ መንፈስ ቅዱስ ፤
ዳግመኛ ሁሉን የሚይዝ የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን። አቤቱ የመንፈስ
ቅዱስን መውረድ እየተመኘን ዓይኖቻችንን ወዳንተ እንሰቅላለን
Again we beseech the almighty God, Father of our Lord
and Savior Jesus Christ, O Lord, we have lifted up our
eyes unto You desiring the descent of the Holy Spirit,
ወለከ ንሰግድ በአብራከ ልብነ። ወለከ ናደንን አርእስተ ሕሊናነ
ወመንፈስነ።
በአብራከ ልቡናችንም እንሰግድልሃለን የሕሊናችንንና
የመንፈሳችንን ራስ እናዋርድልሃለን።
we kneel to You with the knees of our heart, and we
bow unto You the heads of our minds and spirits.
ቀድሰነ እግዚኦ በቅድሳቲከ ፤ ወአንጽሐነ በምሕረትከ ፤ ወረስየነ
ድልዋነ ወሱቱፋነ ለነሢአ ምሥጢርከ ቅዱስ።
አቤቱ በቅድስናህ ቀድሰን ፤ በምሕረትህም አንጻን ፤ ቅዱስ
ምሥጢርህንም ለመቀበል የተገባንና አንድ የሆን አድርገን።
O Lord, You sanctify us with Your sanctification, and
purify us through Your mercy, and make us worthy to
partake of Your Holy mystery.
ዝ አፍሐመ እሳት ዘአንበርኖ በቅድሜከ ቅድመ ምሥዋዒከ
ቅዱስ ኢይኩነነ ዘይሰክየነ። ወዝ ኅብስተ አምልኮ ዘፈተትኖ
ኢይኩነነ ለበቀለ
በቅዱስ መሠውያህ ፊትህ ያኖርነው ይህ የእሳት ፍሕም
የሚከሰን አይሁን። የፈተትነው ይህ የአምልኮ ኅብስት ለበቀል
አይሁንብን ፤
Let not this coal of fire which we have laid before You
upon Your Holy altar be our accuser, and let not this
bread of worship which we break be for vengeance
በእንተ ዘኢያንጻሕነ ነፍሰነ ወሥጋነ መፍርህኬ አብቅዎ ከናፍር
ለበሊዐ እሳት ውዑይ ወውሂጠ አፍሐም ርሱን ለእመ
ኢያንጽሐት ከርሥ ውሳጤሃ እምጽልሑት።
ነፍሳችንንና ሥጋችንን ስላላነጻን የሚያቃጥል እሳትን ለመብላት
የጋለ ፍህምንም ለመዋጥ ከንፈርን መክፈት የሚያስፈራ ነው
ነፍስ ውስጥዋን ከሽንገላ ካላነጻች።
because we did not purify our soul and our body. It is
fearful to open the lips to eat burning fire and swallow
glowing coal if the belly is not purified from deceit
መፍርህኬ ነጽሮ ሕርደቱ ለመርዓዊ ንጹሕ በውስተ ፒላሳሁ ፤
መፍርህኬ ርእየ ጥብሐቱ ለወልደ አምላክ ሕያው በቅድመ
አቡሁ ሰማያዊ ፤
በድንኳኑ ውስጥ የንጹሕ ሙሽራን መሠዋቱን ማየት የሚያስፈራ
ነው ፤ ሕያው የሚሆን የአምላክን ልጅ በሰማያዊ አባቱ ፊት
መሠዋቱን ማየት የሚያስፈራ ነው።
It is fearful to see the slaughter of the pure bridegroom
in His pavilion. It is fearful to see the killing of the Son
of the living God before His heavenly Father.
መፍርህኬ ቀሪቦቱ ለንጥረ መለኮት ወለኪፎቱ ለመብረቀ
ስብሐት።
የመለኮትን ብልጭታ መቅረብ የጌትነት ብርሃንንም (መብረቅ)
መንካት የሚያስፈራ ነው።
It is fearful to draw near the flame of the Deity and to
touch the lightning of glory.
ዲያቆን /deacon/
ጸልዩ።
ጸልዩ።
You pray.
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ። ትምጻእ መንግሥትከ።
ወይኩን ፈቃደከ። በከመ በሰማይ ፤ ከማሁ በምድር።
አባታችን ሆይ ፤ በሰማያት የምትኖር ፤ ስምህ ይቀደስ
መንግስትህ ትምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም
በምድር ትሁን።
Our Father who are in heaven, hallowed be Your name,
Your kingdom come, Your will be done on earth as it is
in heaven;
ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ፤
ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ።
የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ። በደላችንን ይቅር በለን ፤
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል።
give us this day our daily bread, and forgive us our
trespasses as we forgive them that trespass against us,
ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት ፤ አላ አድኅነነ። ወባልሐነ
እምኵሉ እኩይ። እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል
ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ፤ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጅ።
መንግሥት ያንተ ናትና ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
and lead us not into temptation but deliver us and
rescue us from all evil; for Yours is the kingdom, the
power and the glory for ever and ever.
ናንጽሕ ርእሰነ ለነሢኦቱ ፤ ወንቀድስ ነፍሰነ ለተመጥዎቱ ፤
ወንበል ስብሐት ለአብ ዘሠምረ ይጠባሕ መግዝዐ ላህም ንጹሕ።
ለመያዙ ራሳችንን እናንጻጻ ለመቀበሉም ነፍሳችንን እንቀድስ።
ንጹሕ መግዝዐ ላህም ሆኖ ይሠዋ ዘንድ ለወደደ አብ ምስጋና
ይገባዋል እንበል።
Let us, therefore, purify ourselves to take it and sanctify
our souls to receive it and say: Glory be to the Father
who has been pleased that the pure fatted Calf may be
killed.
ስብሐት ለወልድ ዘውእቱ መግዝዐ ላህም ንጹሕ። ስብሐት
ለመንፈስ ቅዱስ ለዝ ኅብስት ዘረሰዮ ከመ ይኩን ሥጋሁ
ለመግዝዐ ላህም ንጹሕ።
ለወልድም ምስጋና ይገባዋል ይኸውም ንጹሕ የሚሆን መግዝዐ
ላህም ነው። ይህን ኅብስት ንጹሕ የሚሆን የመግዝዐ ላህም ሥጋ
ላደረገው ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባዋል።
Glory be to the Son who is the pure fatted Calf. Glory
be to the Holy Spirit who has made this bread the flesh
of the pure fatted Calf.
፫ቱ አስማት ወ፩ዱ እግዚአብሔር ፤ ፫ቱ ገጽ ፩ዱ ራእይ ፤ ፫ቱ
አካል ወ፩ዱ ህላዌ።
ሦስቱ ስም አንድ እግዚአብሔር ነው። ሦስት ገጽ አንድ መልክ ፤
ሦስት አካል አንድ ባሕርይ ነው።
Three names and one God, three liknesses and one
appearance, three persons and one essence.
ሎቱ ስብሐት አምአፈ መላእክት ትጉሃን ፤ ወሎቱ ቅድሳት
እምአፈ ነቢያት ወሐዋርያት እምይእዜ ወእስከ ለዓለም ወእስከ
ዳግም ጉባኤ።
በትጉሃን መላእክት አፍ መመስገን ይገባዋል በነቢያትና
በሐዋርትም አፍ መመስገን ቅዱስ መባል ይገባዋል፤ ከዛሬ
ጀምሮ እስከ ዘለዓለሙ እስከ ሁለተኛውም ጉባኤ ድረስ።
Worthy is He to be glorified by the mouths of the
watchful angels, worthy is He to be sanctified by the
mouths of the prophets and apostles from now till the
end of the world and till the second advent.
ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔ ዓለም። ይቀውሙ ቅድሜሁ
ለመድኃኔ ዓለም።
የመድኃኔ ዓለም አገልጋዮች የሚሆኑ የመላእክት ሠራዊት
በመድኃኔ ዓለም ፊት ይቆማሉ።
The hosts of the angels of the Savior of the world,
stand before the Savior of the world and encircle the
Savior of the world
ወይኬልልዎ ለመድኃኔ ዓለም። ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔ
ዓለም።
መድኃኔ ዓለምን ያመሰግኑታል የመድኃኔ ዓለም ሥጋውና ደሙ
and encircle the Savior of the world even the body and
blood of the Savior of the world.
ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔ ዓለም። በአሚነ ዚአሁ
ለክርስቶስ ንገኒ።
ወደ መድኃኔ ዓለም ፊት እንቅረብ እርሱንም በማመን
ለክርስቶስ እንገዛለን።
Let us draw near the face of the Saviour of the world.
In the faith that is of Him, let us let us submit ourselves
to Christ.
ንፍቅ ዲያቆን (Ass’t Deacon)
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት።
መኳንንት ደጆችን ክፈቱ።
Open the gates, princes.
ዲያቆን Deacon
እለ ትቀውሙ አትሕቱ ርእሰክሙ።
የቆማችሁ ሰዎች ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
You Who are standing, bow your heads.
ህልው አብ ምስለ ወልዱ ወምስለ መንፈስ ቅዱስ እምቅድመ
ሰዓት ወዕለት እምቅድመ አውራኅ ወዓመታት። አልቦ ቀዲመ
ህላዌሁ ለ፩ዱ እምካልዑ ወለካልዑ እምሣልሱ።
አብ ከልጁ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ከሰዓትና ከዕለት፤
ከአውራኅና ከዓመታት አስቀድሞ የነበረ ነው። በአነዋወር ለአንዱ
ከሁለተኛው፤ ለሁለተኛውም ከሦስተኛው መቅደም የለም።
The Father was with His Son and the Holy Spirit before
there were hours and days, before there were months
and years. The One was not before the Other, and the
Second was not before the Third.
ሚመጠን ሩጸተ መባርቅት ፤ ወሚመጠን ንፍሐተ አክናፈ
ንስር። ኅቡራን በኢቡዓዴ ወድሙራን በኢቱሳሔ ህልዋን
በትሥልስት ወእኁዛን በጽምረት ዕሩያን በአካል ፤
የመባርቅት ፍጥነታቸው ምን ያህል ነው፤ የንስር ክንፎች
ፍጥነት ምን ያህል ነው። ባለመለያየት አንድ ናቸው ፤
ባለመቀላቀልም አንድ ናቸው ፤ በሦስትነት ይኖራሉ፤ ባንድነት
የተያያዙ ናቸው፤ በአካል የተካከሉ ናቸው፤
How swift is the speed of lightning and how swift is the
movement of eagles’ wings! They are united without
separation, connected without being mixed, they live in
Trinity, they are joined in oneness, equal in persons and
similar in light and appearance.
ወዕዩያን በሱራኄ ወበጸዳል። አኮ ለመርድአ ግብር ዘወለዶ አብ
ለወልድ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ወአኮ ለአስተዋጽኦ ኪን
ወተግባር ዘኮነ ህላዌሁ ለመንፈስ ቅዱስ።
በብርሃና በጸዳል የተመሳሰሉ ናቸው። አብ ልጁን ዓለም
ሳይፈጠር የወለደው በሥራ ሊረዳው አይደለም። የመንፈስ
ቅዱስም ባሕርይ የተገኘ ብልሀትና ሥራ ለማወጣጣት አይደለም
The Father did not beget His Son to help Him in His
work before the world was created, and the existence of
the Holy Spirit is not to contribute wisdom and work.
ንንግርኬ ልደቶ እምአብ ባሕቲቱ እግዚአብሔር አልቦቱ እም
አሜሃ እስመ ኢያስተርአየ ህላዌሆሙ ለፍጡራን።
ከእግዚአብሔር አብ ብቻ መወለዱን እንናገር ፤ ያን ጊዜ እናት
አልነበረችውም ፤ የፍጡራን አነዋወር ገና አልታየም ነበርና።
Let us speak of His birth from God the Father only. At
that time He had no mother because the existence of the
creatures had not yet appeared.
ወካዕበ ንንግር ወንዜኑ ልደቶ እምድንግል ባሕቲቱ ወልደ
አምላክ ዘእምባሕቲታ ወለተ ዳዊት ዘእንበለ አብ ምድራዊ።
ዳግመኛም ምድራዊ አባት ሳይኖረው የአምላክ ልጅ ብቻውን
ከዳዊት ልጅ ከድንግል ብቻ መወለዱን እንናገር እናውራ።
Again let us speak of and proclaim the birth of Him who
is alone the Son of God and who alone was born
without an earthly Father from the Virgin, the daughter of
David.
ኢሐዖ ፍና ትስብእት በእንተ ዘአልቦቱ አብ ለዘርዐ ሙላድ አላ
ፍጹመ ተሰብአ ዘእምባሕቲታ ድንግል።
በዘር ለመወለድ አባት ስላልነበረው የሰውነት ሥራ
አልጐደለበትም ፤ ከድንግል ብቻ ፈጽሞ ሰው ሆነ እንጂ።
and as the building of the body of the first Adam did
not lose anything when a bone of his side was taken
away,
በከመ ኢሐፃ ለሔዋን ጠባይዐ አንስት በእንተ ዘአልባቲ እም
አመ ተነድቀት እምዐፅመ ገቦሁ ለአዳም ፤
ከአዳም ጐን አጥንት በተፈጠረች ጊዜ እናት ስላልነበረቻት
ሔዋን የሴቶች ባሕርይ እንዳልጐደለባት።
As Eve’s female nature was not inferior through having
had no mother when she was formed from the bone of
Adam’s side,
ወበከመ ኢሐዖ ለአዳም እምሕንፃ ሥጋሁ ዘቀዲሙ በእንተ
ዘተነቅለ ዐጽመ ገቦሁ ፤ ከማሁ ኢሐፀ ማኅተመ ድንግልናሃ
ለማርያም አመ ወለደቶ ለአበ አዳም በሥጋ።
አዳምም የጐኑ አጥንት ስለ ተነቀለ ከቀደመው የሥጋው ፍጥረት
እንዳልጐደለበት፤ እንደዚሁ የአዳምን አባት በሥጋ በወለደችው
ጊዜ የማርያም ማኅተመ ድንግልናዋ አልጐደለም።
and as the building of the body o the first Adam did not
lose anything when a bone of his side was taken away,
so also the seal of Mary’s virginity was not destroyed
when she gave birth to the Father of Adam in the flesh;
ወበከመ ኢያሕመሞ ለአዳም ሶበ ተነቅለ ዐፅመ ገቦሁ ከማሁ
ኢረከባ ሕማመ ወሊድ ለእመ አምላክ ገሊላዊ።
አዳምን ከጐኑ አጥንት በተነቀለ ጊዜ እንዳላሳመመው እንደዚሁ
የገሊላ ወገን የምትሆን የአምላክን እናት ሕማመ ወሊድ
አላገኛትም።
And as Adam did not feel pain when a bone was taken
from his side, so also the Galilean Mother of God did
not feel travail.
ከመዝ ነአምን ወከመዝ ንትአመን ከመ ዝንቱ ኅብስት ዘንፌትቶ
ሥጋ ክርስቶስ ውእቱ ዘነሥአ እምወለቶሙ ለዕብራዊያን። ወካዕበ
ነአምን ከመ ዝንቱ ጽዕ ደመ መለኮት ውእቱ ዘውኅዘ እምገቦ
በግዑ ለእግዚአብሔር።
እንዲህ እናምናለን እንዲህም አንታመናለን ይህ የምንፈትተው
ኅብስት ከዕብራዊያን ልጅ የነሣው የክርስቶስ ሥጋ እንደ ሆነ።
ዳግመኛ ይህ ጽዋ የእግዚአብሔር በግ ከሚሆን የፈሰሰ ደም
መለኮት እንደሆነ እናምናለን፤
Thus we believe and thus we affirm that this bread which
we break is the body of Christ which He took from the
daughter of the Hebrews. We also believe that this cup is
the blood of the Deity shed from the side of God’s Lamb.
ወዓዲ ነአምን ከመ ዘንቱ ትእምርተ መስቀል አርኣያ ስቅለቱ
ለክርስቶስ ዘተንጦልዐ አመ ሕማማቲሁ።
ዳግመኛ ይህ ትእምርተ መስቀል በሕማማቱ ጊዜ የተዘረጋ
የክርስቶስ የመስቀሉ ምሳሌ እንደ ሆነ እናምናለን።
We also believe that this sign of the cross is the image
of Christ’s crucifixion when He was stretched out at the
time of his suffering.
ንሰግድ ቅድመ ምሥዋዒሁ ለዘይለብስ አልባሰ ዘንዙኅ በደም
ወለይእቲ ልብስ ዘንዝኅት በደም ለዓለም ዓለም።
ደም የተረጨች ልብስን ለለበሰ ለርሱ በመሠዊያው ፊት
እንሰግዳለን፤ ደምን ለተረጨች ለዚያችም ልብስ ለዘላለሙ።
We bow before the altar of Him who is clothed with a
vesture dipped in blood, world without end.
ዲያቆን Deacon
ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት።
በፍርሃት ሆናችሁም ለእግዚአብሔር ስገዱ።
Worship the Lord with fear.
ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ።
አቤቱ በፊትህ እንሰግዳለን እናመሰግንሃለንም።
Before You, Lord, we worship, and we do glorify You.
ጸሎተ ንስሓ።
የንስሓ ጸሎት።
"Prayer of Pentence”
እግዚእ እግዚኦ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ዓለም አንተ
ውእቱ ዘትፌውስ ቊስለ ነፍስነ ወሥጋነ ወመንፈስነ እስመ አንተ
ትቤ በአፈ ዋሕድ ወልድከ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ፤
አቤቱ ዓለሙን ሁሉ የያዝህ ጌታችን እግዚአብሔር አብ
የነፍሳችንንና የሥጋችንን የደመ ነፍሳችንንም ቊስል የምታድን
አንተ ነህ ባንድ ልጅህ በጌታችንና በመድኃታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ አፍ ተናግረሃልና፤
O Lord God, the Father almighty, it is You that heal the
wounds of our soul and our spirit, Because You have
said, with the mouth of Your only-begotten Son, our Lord
and our God and our Savior Jesus Christ,
ዘይቤሎ ለአቡነ ጴጥሮስ አንተ ኰኵሕ ወዲበ ዛቲ ኰኵሕ
አሐንጻ ለቤተ ክርስቲያንየ ቅድስት ወኢክልዋ አናቅጸ ሲኦል
አማስኖታ ወአንቀልቅሎታ
ለአባታችን ለጴጥሮስ እንዲህ ብሎ የተናገረውን አንተ አለት
መሠረት ነህ በዚችም አለት መሠረት ላይ ክብርት ቤተ
ክርስቲያኔን እሠራታለሁ የሲኦልም ደጆች ሊያጠፏትና
ሊያነዋውጧት አይችሉም።
that which He said to our father Peter, you are a rock I
will build My Holy Church and the gates of hell shall not
prevail against it,
ወለከ እሁበከ መራኁተ ዘመንግሥተ ሰማያት ዘአሠርከ በምድር
ይኩን እሡረ በሰማያት፤ ወዘፈታሕከ በምድር ይኩን ፍቱሐ
በሰማያት።
ለአንተም የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ እሰጥሃለሁ በምድር
ያሠርኸው በሰማይ የታሠረ ይሆን ዘንድ በምድር የፈታኸው
በሰማይ የተፈታ ይሆን ዘንድ።
and unto you I give the keys of the Kingdom of heaven;
what you have bound on earth shall be bound in
heaven, and what you have loosed on earth shall be
loosed in heaven:
ወይኩኑ ፍቱሓነ ወግዑዛነ ኵሎሙ አግብርቲከ በበአስማቲሆሙ
በአፉሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወበአፈ ዚአየኒ አነ ገብርከ እገሌ ኃጥእ
ወአባሲ እመሂ በአእምሮ አው በኢያእምሮ ገብሩ፡፡
ወንዶችም ሴቶችም ባሮችህ ሁሉ በየስማቸው የተፈቱ ነጻም
የወጡ ይሁኑ በመንፈስ ቅዱስ ቃል ኃጥእ በደለኛ በምሆን በኔም
በባሪያህ ቃል፤በማወቅ ወይም ባለማወቅ ቢሠሩ::
Let us all Your servants and Your handmaids, according
to their several names, be absolved and set free out of
the mouth of the Holy Spirit, and out of the mouth of me
also Your sinful and guilty servant….. whether they have
wrought wittingly or unwittingly
ወዓዲ ለትሕትና ዚአየኒ አነ ገብርከ ኃጥእ ወአባሲ ፍትሐኒ
ወይኩኑ ፍቱሓነ ወግዑዛነ እምአፈ ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ ወእምአፈ ዚአየኒ አነ ገብርከ ኃጥእ ወአባሲ።
ዳግመኛም ኃጥእ በደለኛም የምሆን እኔንም ወራዳነቴን አይተህ
ፍታኝ ልዩ ሦስት በሚሆኑ በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስም
ቃል የተፈቱ ነጻ የወጡ ይሁኑ ኃጥእ በደለኛ በምሆን በኔም
በባሪያህ ቃል።
And absolve them and set them free out of the mouth of
the Holy Trinity, the Father and the Son and the Holy
Spirit, and out of the mouth of me Your sinful and
unrighteous servant.
ኦ መሐሪ ወመስተሣህል ወመፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር
አምላክነ ዘታአትት ኃጢአተ ዓለም ተወከፍ ንስሓሆሙ
ለአግብርቲከ ወለአእማቲከ ወአሥርቅ ላዕሌሆሙ።
መሐሪ ይቅር ባይ ሰውንም የምትወድ አምላካችን እግዚአብሔር
ሆይ የዓለሙን ኃጢአት የምታቅ የወንዶቹንና የሴቶቹን
ባሮችህን ንስሓቸውን ተቀበል።
O pitiful, merciful and lover of man, Lord our God, that
take away the sin of the world, accept the penitence of
Your servants and Your handmaids,
ብርሃነ ሕይወት ዘለዓለም ወሥረይ ሎሙ እግዚኦ ኵሎ
ኃጢአቶሙ እስመ ኄር አንተ ወመፍቀሬ ሰብእ ኦ እግዚአብሔር
አምላክነ ወመስተሣህል
የዘላለም ደኅንነት የሚሆን ብርሃንንም ግለጽላቸው፤ አቤቱ
ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር በላቸው ቸር ሰውንም የምትወድ
አንተ ነህና ይቅር ባይ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ
and shine upon them with the light of ever lasting life,
and forgive them, Lord, all their sins; for You are good
and the lover of man.
ርኁቀ መዓት ወብዙኃ ምሕረት ወጻድቅ ሥረይ ሊተ
ኃጢአትየወለኵሎሙ አግብርቲከ ወአእማቲከ አድኅኖሙ
እምኵሉ አበሳ ወመርገም።
መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ እውነተኛም የምትሆን የኔን
ኃጢአቴን አስተሥርይልኝ ወንዶችና ሴቶችን ባሮችህን ሁሉ
ከበደልም ከመርገምም ሁሉ አድናቸው፡፡
O Lord our God, merciful, slow to anger, plenteous in
mercy and righteous, forgive my sins; And deliver all Your
servants and hand-maids from all transgression and curse
ለእመ አበስነ ለከ እግዚኦ እመሂ በቃልነ ወእመሂ በምግባርነ
ወእመሂ በሕሊናነ ኅድግ ወሥረይ ወአናሕሲ ወተሣሃል እስመ
ኄር አንተ ወመፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር አምላክነ።
በቃላችንም ቢሆን በሥራችንም ቢሆን በአሳባችንም ቢሆን አቤቱ
አንተን ብንበድል ተውልን አስተሥርይ አቃልልን ይቅርም በለን
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አንተ ቸር ሰውን ወዳጅ ነህና።
If we have transgressed against you, Lord, whether in
our word or in our deed or in our thought, release, remit,
pardon and have mercy, for You are good and the lover
of man, Lord our God.
ኦ እግዚኦ ረሥየነ ፍቱሓነ ወግዑዛነ ወለኵሎሙ ሕዝብከ
ፍትሖሙ ወሊተኒ ለኃእ ገብርከ ፍትሐኒ ተዘከሮ እግዚኦ ለአብ
ክቡር ሊቃነ ጳጳሳት አባ ……..
አቤቱ የተፈታን ነፃም የወጣን አድርገን ወገኖችህንም ሁሉ
ፍታቸው፤ ኃጥእ የምሆን እኔንም ባርያህን ፍታኝ ክቡር የሚሆን
የጳጳሳቱን አለቃ አባ …….. አስበው፤
O Lord, absolve us and set us free, and absolve all
Your people, and absolve me Your sinful servant.
Remember, Lord, the honorable father, our Patriarch
Abba …….
ወብፁዕ ጳጳስነ አባ ……..አምላክነ ዐቂበ ዕቀቦሙ ለነ ዓመታተ
ብዙኀ ወመዋዕለ ነዊኀ በጽድቅ ወበሰላም። ተዘከራ እግዚኦ
ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወዕቀባ በጽድቅ ወበሰላም አግርር ፀራ
ወጸላዕታ ፍጡነ።
ብፁዕ የሚሆን አባ……. አስበው። አምላካችን ሆይ ለብዙ
ዘመናት ለረጅም ወራት በእውነትና በሰላም መጠበቅን ጠብቅልን
አቤቱ ሀገራችንን ኢትዮጵያን አስባት የሚጣሏትንና ጠላቶቿን
ፈጥነህ አስገዛላት።
and the blessed Archbishop Abba …… Our God, keep
them for us many years and length of days in
righteousness and peace. Remember, O Lord, our
country Ethiopia. Subdue her adversaries and her
enemies under her feet speedily.
ተዘከር እግዚኦ ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳተ ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት
ወዲያቆናተ አናጕንስጢሳውያነ ወመዘምራነ ደናግለ ወመነኰሳተ
ዕቤራተ ወእጓለ ማውታ እደ ወአንስተ አእሩገ ወሕፃናተ
የጳጳሳቱን አለቆች ጳጳሳቱንና ኤጲስ ቆሳቱን ቀሳውስቱንና
ዲያቆናቱንአንባቢዎችንና መዘምራኑን ደናግሉንና መነኰሳቱን
ባልቴቶቹንና አባት እናት የሞቱባቸውን ወንዶቹንና ሴቶቹን
ሽማግሌዎቹንና ልጆቹን
Remember, Lord, the patriarchs, archbishops, bishops,
priests and deacons, anagunsts(readers) and singers,
virgins and monks, widows and orphans, men and
women, aged and children;
ወኵሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን እለ ሀለዉ ወቆሙ ውስተ ዛቲ ቤተ
ክርስቲያን ቅድስት አጽንዖሙ በሃይማኖተ ክርስቶስ ፤ ተዘከሮሙ
እግዚኦ ለኵሎሙ አበዊነ ወአኀዊነ ወአኃቲነ እለ ኖሙ ወአዕረፉ
በርትዕት ሃይማኖት።
ክብርት በምትሆን በዚህች ቤተ ክርስቲያን ያሉትን የቆሙትንም
የክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ክርስቶስን በማመን አጽናቸው አቤቱ
በቀናች ሃይማኖት ሁነው የሞቱትንና ያረፉትን አባቶቻችንንና
ወንድሞቻችንን እኅቶቻችንን ሁሉ አስባቸው።
and all Christian people that are standing in this holy
church; strengthen them in the faith of Christ. Remember,
Lord, all our fathers, brothers and sisters that are asleep
and resting in the orthodox faith,
ወደምር ነፍሳቲሆሙ ውስተ ሕዕነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ
ወለነኒ አድኅነነ እምኵሉ አበሳ ወመረወገም ወእምኵሉ ጌጋይ
ወእምኵሉ ክሕደት ወእምኵሉ መሐላ በሐሰት ወእምኵሉ
ግዘት።
ነፍሶቻቸውንም በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም አጠገብ አኑር
እኛን ከኃጢአት ሁሉ ከመርገምም ከበደልም ሁሉ ከክህደትም
ሁሉ በሐሰትም ከመማል ሁሉ ከመገዘትም ሁሉ አድነን።
and lay their souls in the bosom of Abraham, Isaac and
Jacob. and as for us, deliver us from every transgression
and curse and from all wickedness and from all rebellion
and from all false swearing and from all anathemas
ወእምተደምሮ በዕልወት ወርኵስ ምስለ ዓላውያን ወአረማውያን
ጸግወነ እንዚኦ ጥበበ ወኃይለ ልበ ወልቡና ወአእምሮ፤
በክህደትና በርኵሰት ከዓላማውያንና ከአረማውያን ጋራ አንድ
ከመሆን አድነን አቤቱ ጥበብንና ኃይልን ልብንና ልቦናን
ዕውቀትንም ስጠን።
and from all perjury and from mingling with heretics and
gentiles in error and defilement. Grant us, Lord, wisdom
and power and reason and understanding and knowledge
ከመ ንርሐቅ ወንጕየይ እንከ እስከ ለዝሉፉ እምኵሉ
ምግባራቲሁ ለሰይጣን ዘያሜክር ሀበነ እግዚኦ ንግበር ፈቃደከ
ወሥምረተከ በኵሉ ጊዜ ወጸሐፍ አስማቲነ ውስተ መጽሐፈ
ሕይወት በመንግሥተ ሰማያት
እንግዲህ ከሚፈታተነን ከሠይጣን ሥራ ሁሉ እስከ ዘላለሙ
እንርቅ እንሸሽም ዘንድ አቤቱ ሁል ጊዜ ፈቃድህን ውድህንም
እንሠራ ዘንድ ስጠን ስማችንንም በመንግሥተ ሰማያት
በሕይወት መጽሐፍ
that we may depart and flee for evermore from all works
of Satan the tempter. Grant us, Lord, to do Your will and
Your good pleasure at all times, and write our names in
the book of life in the kingdom of heaven
ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሰማዕት በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ
ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ከቅዱሳንና ከሰማዕታት ሁሉ ጋራ ጻፍ በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል ከርሱ ጋራ
ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
with all saints and martyrs, through Jesus Christ our
Lord, through whom to You with Him and with the Holy
Spirit be glory and dominion, both now and ever and
world without end. Amen.
ነጽር።
አስተውል።
Give heed.
ካህን
ቅድሳት ለቅዱሳን።
ቅድሳት ለቅዱሳን።
Holy things for the Holy.
አሐዱ አብ ቅዱስ።
አሐዱ ወልድ ቅዱስ።
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
አንዱ ቅዱስ አብ ነው።
አንዱ ቅዱስ ወልድ ነው።
አንዱ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ነው።
One is the Holy Father,
one is the Holy Son,
one is the Holy Spirit.
እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
The Lord be with you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ካህኑን በመከተል ደግመን እንበል። / Repeat after the priest.
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ።
አቤቱ ክርስቶስ ማረን።
Lord have compassion upon us O! Christ!
እለ ውስተ ንስሓ ሀለውክሙ አትሕቱ ርእሰክሙ።
በንስሓ ወስጥ ያላችሁ ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
You, that are penitent, bow your heads.
እግዚአብሔር አምላክነ ነጽር ዲበ ሕዝበከ እለ ውስተ ንስሐ
ሀለዉ ወተሣሃሎሙ በከመ ዕበየ ሣህልከ ወበከመ ብዝኀ ምሕረትከ
ደምስስ አበሳሆሙ ክድኖሙ ወዕቀቦሙ እምኵሉ እኩይ።
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በንስሐ ውስጥ ስላሉት ወገኖችህ
ተመልከት እንደ ይቅርታህም ብዛት ይቅር በላቸው እንደ
ቸርነትህም ብዛት በደላቸውን አጥፋላቸው ከክፉ ነገርም ሁሉ
ጠብቃቸው ሰውራቸውም።
Lord our God, look upon Your people that are penitent,
and according to Your great mercy have mercy upon them
and according to the multitude of Your compassion blot
out their iniquity, cover them and keep them from all evil.
ወቤዙ ነፍሳቲሆሙ በሰላም አኅጺረከ ዘቀዳሚ ምግባሮሙ
ደምሮሙ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት በሞገሱ ወበምሕረቱ
ለዋሕድ ወልድከ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ
ክርስቶስ።
የቀደመ ሥራቸውን ይቅር ብለህ በሰላም ነፍሳቸውን አድን
ከቅድስት ቤተ ክርስትያንህ አንድ አድርጋቸው ተቀዳሚ ተከታይ
በሌለው በአንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን
በመድኃኒታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ፤
And redeem their souls in peace, forgive their former
works. Join them with Your Holy church: through the
grace and compassion of Your only-begotten Son our
Lord and our God and our Savior Jesus Christ,
ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
በይቅርታውና በምሕረቱ ከቅድስት ቤተ ክርስትያንህ ጨምራቸው
በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ላንተ ይገባል ከርሱ ጋራ ከመንፈስ
ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
through whom to You with Him and with the Holy Spirit
be glory and dominion, both now and ever and world
without end. Amen.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
ሥጋ ቅዱስ ዘበአማን ዝውእቱ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘይትወሀብ ለሕይወት ወለመድኃኒት
ወለሥርየተ ኃጢአት ለእለ ይነሥኡ እምኔሁ በአሚን።
በእውነት ክቡር የሚሆን የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ይህ ነው። አምነው ከእርሱ ለሚቀበሉ
ሕይወትና መድኃኒት የኃጠአት ማስተሥረያም ሊሆን የሚሰጥ።
This is the true holy body of our Lord, God, and Saviour
Jesus Christ, that is given for life, salvation, remission of
sin unto them that receive of it in faith.
ሕዝብ / People
አሜን
Amen.
ደም ክቡር ዘበአማን ዝ ውእቱ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘይትወሀብ ለሕይወት ወለመድኃኒት
ወለሥርየተ ኃጢአት ለእለ ይትሜጠው እምኔሁ በአሚን።
በእውነት አምነው ከእርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት ፥
የኃጢአት ማሥተሪያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና የአምላካችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ ነው።
This is the true precious blood of our Lord, God, and
Saviour Jesus Christ, which is given for life, salvation,
and remission of sins into those who drink of it in faith.
ሕዝብ / People
አሜን
Amen.
(Priest) Priest)
እስመ ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ወደሙ ለአማኑኤል አምላክነ
ዘበአማን።
በእውነት የአምላካችን የአማኑኤል ሥጋውና ደሙ ይህ ነው።
For this is the body and blood of Emmanuel our very
God.
ሕዝብ People
አሜን
Amen.
አአምን አአምን አአምን ወእትአመን እስከ ደኃሪት እስትንፋስ።
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ እስከ መጨርሻይቱም እስትንፋስ
እታመናለሁ።
I believe, I believe, I believe and I confess, unto my last
breath,
ከመዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ወደሙ ለእግዚእነ ወአምላክነ
ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘነሥአ እምእግዝእትነ ኵልነ
ቅድስ ድንግል በክልኤ ማርያም።
በሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን ከሁላችን እመቤት ከቅድስት
ድንግል ማርያም የነሣው የጌታችንና የአምላካችን
የመድኃኒታችንም የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ይህ
እንደሆነ።
that this is the body and blood of our Lord, God, and
Saviour Jesus Christ, which He took from the Lady of us
all, the holy Mary of twofold virginity,
ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ ወኮነ
ሰማዕተ በስምዕ ሠናይ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ ወመጠዎ
በእንቲአነ ወበእንተ ሕይወት ኵልነ።
ያለመቀላቀልና ያለትድምርት ፥ ያለመለወጥና ያለመለየት
ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው በጴንጤናዊ ጲላጦስም ዘመን
በአማረ ምስክርነት ምስክር የሆነ ስለ እኛና ስለ ሁላችንም
ሕይወት አሳልፎ የሰጠው።
and made it one with His godhead without mixture or
confusion, without division or alteration; and He verily
confessed with a good testimony in the days of Pontius
Pilate, and this body He gave up for our sakes and for
the life of us all.
ሕዝብ People
አሜን
Amen.
አአምን አአምን አአምን ወእትአመን ከመ ኢፈልጠ መለኮቱ
እምትስብእቱ ኢአሐተ ሰዓተ ወኢከመ ቅጽበት ዓይን
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ መለኮቱ ከሰውነቱ አንዲት ሰዓት
እንኳን እንደ ዓይን ቅጽበት እንኳ እንዳልተለየም እታመናለሁ።
I believe, I believe, I believe and I confess that His
godhead was not separated from His manhood, not for
an hour nor for the twinkling of an eye,
አላ መጠዎ በእንቲአነ ለሕይወት ወለመድኃኒት ወለሥርየተ
ኃጢአት ለእለ ይትሜጠዉ እምኔሁ በአሚን።
ስለ እኛ ሰጠው እንጂ ለሕይወትና ለመድኃኒት ለኃጢአትም
ማስተሥረያ ሊሆን አምነው ለሚቀበሉ ሰዎች ስለ እኛ አሳልፎ
ሰጠው እንጂ።
but He gave it up for our sakes for life, salvation, and
remission of sin unto them that partake of it in faith.
ሕዝብ / People
አሜን
Amen.
አአምን አአምን አአምን ወእትአመን ከመ ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ
ወደሙ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ የጌታችንና የአምላካችን
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ይህ እንደሆነ
እታመናለሁ።
I believe, I believe, I believe and I confess that this is
the body and blood of our Lord, God, and Saviour Jesus
Christ, and that to Him are rightly due honour and
ዝውእቱ ዘሎቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወስግደት ምስለ አቡሁ
ኄር ሰማያዊ ወመንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ ይእዜኒ ወዘልፈኒ
ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ክብርና ምስጋና ስግደትም ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባቱ ጋራ
የሚገባው ይህ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
glory and adoration with His kind heavenly Father and
the Holy Spirit, the life-giver, both now and ever and
unto the ages of ages. Amen.
ቁርባኑን ከመቀበል አስቀድሞ ከቅዱስ ምሥጢር የሚቀበሉ
ሁሉ የሚከተለውን ይበሉ።
Before receiving the Holy communion, all communicant
shall say the following.
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አኮ ዘይደልወኒ ትባእ ታሕተ
ጠፈረ ቤትየ ርኵስት እስመ አነ አስተቈጣዕኩከ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ ርኵስት ከሆነች ከቤቴ
ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም እኔ
አሳዝኜሃለሁና፤
O my Lord Jesus Christ, I am not worthy for You to
come under the roof of my polluted house, for I have
provoked You to wrath,
ወገበርኩ እኩየ በቅድሜከ ወአርኰስኩ ነፍስየ ወሥጋየ ዘፈጠርከ
በአርአያከ ወበአምሳሊከ በዐሊወ ትእዛዝከ ፣ ወአ ልብየ ምግባር
ወኢምንትኒ።
በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና ፣ በአርአያህና በአምሳልህ
የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ
አሳድፌያለሁና ፣ ሥራም ምንም ምን የለኝምና።
and have done evil in Your sight, and through the
transgression of Your commandment have polluted my
soul and my body which You did create after Your image
and Your likeness, and in me dwells no good thing.
ወባሕቱ በእንተ ተኬንዎትከ ወበእንተ ትስብእትከ በእንተ
መድኃኒትየ ወበእንተ መስቀልከ ክቡር ወበእንተ ሞትከ
ማሕየዊት፤
ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ ፣ ስለ
ክቡር መስቀልህም ፣ ማሕየዊት ስለምትሆን ስለ ሞትህ፣
But for the sake of Your contrivance and Your incarnation
for my salvation, for the sake of Your precious cross and
Your life-giving death,.
ወበእንተ ትንሣኤከ በሣልስት ዕለት እስእለከ ወአስተበቍዐከ ኦ
እግዚእየ ከመታንጽሐኒ እምኵሉ አበሳ ወመርገም ወእምኵሉ
ኃጢአት ወርኵስ።
በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም
ሁሉ ከኃጢአ ትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምን
ሃለሁ፣ እማልድሃለሁም።
for the sake of Your resurrection on the third day, I pray
You and beseech You, O my Lord, that You would purge
me from all guilt and curse and from all sin and
defilement
ወሶበ እትሜጠዎ ለምሥጢረ ቅድሳቲከ ኢይኩነኒ ለቅስት
ወኢለኵነኔ ፣ አላ መሐረኒ ወተሣሃለኒ ፣ ወሀበኒ ቦቱ ሥርየተ
ኃጢአትየ ወሕይወተ ነፍስየ፤
የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልሁት ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ
አይሁንብኝ ፣ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ፣ የዓለም ሕይወት
ሆይ፣ በርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ
እንጂ፣
When I received Your Holy mystery let it not be unto me
for judgment nor for condemnation, but have compassion
upon me and have mercy upon me; and through it grant
me remission of my sin and life for my soul,
ኦ ሕይወተ ዓለም በስእለታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል በ፪ኤ
ማርያም ወላዲትከ ወዮሐንስ መጥምቅ ፣ ወበጸሎተ ኵሎሙ
ቅዱሳን መላእክት ወኵሎሙ ሰማዕት ወጻድቃን መስተጋድላን
በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን
በቅድስት ማርያም በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት ክቡራን
በሚሆኑ በመላእክትም በሰማዕታትና ለበጎ ነገር በሚጋደሉ
O life of the world, through the petition of our Lady, the
Holy Mary of twofold virginity Your mother, and of John
the Baptist, and through the prayer of all the Holy angels
ለሠናይ እስከ ለዓለመ ዓለም አሜን።
በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን።
And all the martyrs and righteous who have fought for
the good, world without end. Amen.
ካህናትና ሕዝብ በመቀባበል / Priests and people in succession.
ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ፣
ማርያም እምነ ናስተበቍዓኪ።
ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግዳለን። እናታችን ማርያም
ሆይ እንማልድሻለን።
Peace be unto You, while bowing unto You, our mother
Mary, we as for Your prayers.
እምአርዌ ነአዊ ተምኅጸነ ብኪ፣
በእንተ ሐና እምኪ ፤ ወኢያቄም አቡኪ፣
ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።
ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል። ስለ እናትሽ
ሐና ስለ አባትሽም ኢያቄም ድንግል ሆይ አንድነታችንን ዛሬ
ባርኪልን።
Protect us from evil animals. For the sake of thy
mother, Hanna, and Your father, Iyakem, O! Virgin bless
this day.
ናዛዚትነ እምኃዘን ወኃይለ ውርዙትነ እምርስዓን፣
በማኅጸንኪ ተፀውረ ብሉየ መዋዕል ሕፃን።
ከሀዘናችን የምታረጋጊን እና ከእርጅና ይልቅ የወጣትነታችን
ኃይል የሆንሽ ሆይ ፤ ዘመን የማይቆጠርለት ሕፃን በማኅፀንሽ
አደረ።
O You, who is the strength of our youthfulness rather
than our aging and who calms us from our grief, The
Baby who lives forever has been conceived in Your
womb.
ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን፣
በጊዜ ጸሎት ወዕጣን ወበቅዱስ ቊርባን፣
ለናዝዞትነ ንዒ ውስተ ዝ መካን።
ተስፋ ለቆረጡ ተስፋ የሆንሽ ማርያም ሆይ በጸሎት፣ በዕጣንና
ቅዱስ ቁርባንም ጊዜ እኛን ለማረጋጋት ወደዚህ ቦት ነዪ።
O Mary, the hope of those who are in despair, come
here to calm us when we pray, burn incense and
during the Eucharist.
ወላዲተ አምላክ ማርያም እንበለ ሰብሳብ ወሩካቤ፣
በይነ ዘአቅረብኩ ለኪ ንስቲተ ቃለ ይባቤ።
ፈጽሞ ያለጋብቻ አምላክን የወለድሽ ማርያም ሆይ
ስላቀረብኩልሽ ትንሽ የደስታ ቃል
Little happy words I have given You, O Mary, who
gave birth to God without marriage
ፈትቲ እሙ በረከተ አፉኪ መዓዛ ከርቤ፣
ለነዳይ ብእሲ ወለዘረከቦ ምንዳቤ፣
ኅብስተከ ፈትት ኢሳይያስ ይቤ።
የከርቤ መፍሰሻ የሆነው የአፍሽን በረከት ለእኔ ቁረሽልኝ።
ምክንያቱም ነቢዩ ኢሳይያስ ለደሀና ችግር ለደረሰበት ሰው
እንጀራህን ቁረስለት ይላልና።
Because of the prophet Isaiah says, “break your bread
for the poor and afflicted.”, break Your blessing to me
from Your mouth which is the myrrh's flowing.
ይወርድ መንፈስ ቅዱስ በላዕለ ኅብስቱ ወወይኑ፣
ሶበ ይብል ካህን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ፈኑ።
ካህኑ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ላክ ባለ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ
በኅብስቱና በወይኑ ላይ ይወርዳል።
As the priest says let the Holy Spirit descend, on this
revered Holy of Holies.
ማዕከለ ዛቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ፣
ይዌልጦሙ በቅጽበት አባላተ ክርስቶስ ይኩኑ፣
በኃይለ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ ኪኑ።
አስደናቂ በሚሆን የጥበቡ ኃይልና በአስገራሚ ብልሃቱ በቅድስት
ቤተ ክርስቲያኑ መካከል የክርስቶስ አባሎች ይሆኑ ዘንድ
በቅጽበት ይለውጣቸዋል።
The Holy Spirit will descend upon the bread and wine
and towards the Flesh and Blood. His special Spirit will
transform them in an instant with His wisdom.
ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት፣
እለ አዕረፍክሙ በሃይማኖት።
በሃይማኖት ያረፋችሁ ጻድቃንና ሰማእታት ሰላም ለእናንተ
ይሁን።
Peace be unto you, blessed and martyrs, who have died
for the faith.
መዋእያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት፣
ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኵሉ ሰዓት፤
እንበለ ንስሓ ኪያነ ኢይንሥአ ሞት።
በብዙ ትዕግሥት ዓለምን ድል የነሣችሁ እናንተ ፣ ለንስሓ
ሳንበቃ ሞት እንዳይወስደን በየሰዓቱ በፈጣሪ ፊት ቆማችሁ
ለምኑልን።
You who have conquered the world b patience, pray for
us day and night standing in front of our Creator, so
that death will not take us before we have repented.
ሰላም ለክሙ ጻድቃነ ዛቲ ዕለት ኵልክሙ፣
ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ።
ጻድቃን ወንዶችም ሴቶችም ሁላችሁ በየስማችሁ በዚህ ዕለት
ሰላም ለናንተ ይሁን።
Peace be unto you, all those blessed on this day, men
and women according to your name.
ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንተሙ፣
ዝክሩነ በጸሎትክሙ በእንተ ማርያም እሙ፣
ተማኅጸነ በክርስቶስ በሥጋሁ ወበደሙ።
በሰማይና በምድር የከበራችሁ የሥላሴ ወገኖች ስለ እናቱ
ማርያም ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡን ፤ በክርስቶስ ሥጋና ደም
ተማጸንባችሁ።
You that are glorified in heaven and on earth,friends of
the Holy Trinity; remember us in your prayers for the
sake of Mary and for the sake of Christ's flesh and
blood, we beseech you.
እግዚኦ ሰላመከ ሀባ ለሀገር ወጽድቀከኒ ለቤተክርስቲያን።
አቤቱ ጌታ ሆይ ሰላምህን ለሀገር ፤ እውነትህንም ለቤተ
ክርስቲያን ስጥ።
O Lord! Grant Your peace to the country and your truth
to the church.
አግርር ፀራ ታሕተ እገሪሃ ፤ ዕቀብ ሕዝባ ወሃይማኖታ
ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ።
ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጠላቶቿን በእግሮቿ ሥር ጣልላት ፤
ሕዝቧንና ሃይማኖቷን ጠብቅላት።
For our country Ethiopia, O Lord bring her enemies
under her feet and protect her people and religion.
ካህኑን በመከተል እንበል / repeat after priest.
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ (፫ ጊዜ)
አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን
Lord have compassion upon us O! Christ, Lord. (3 times)
ካህኑን በመከተል እንበል / repeat after priest.
በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ (፫ ጊዜ)
ክርስቶስ ሆይ ስለ ማርያም ብለህ ማረን።
For the sake of Mary, have compassion upon us, O!
Christ, Lord (3 times)
ሰአሊ ለነ ማርያም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ።
ማርያም ሆይ! ይቅርታውን ያደርግልን ዘንድ የልጅሽን
ምሕረት ለምኝልን።
O Mary, pray for our mercy, so that He may forgive us.
ጸልዩ በእንቲአነ ወበእንተ ኵሎሙ ክርስቲያን እለ ይቤሉነ ግበሩ
ተዝካሮሙ በሰላም ፤ ወበፍቅረ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብሑ ወዘምሩ።
ስለ እኛና አስቡን ስላሉን ስለ ክርስቲያኖች ሁሉ ጸልዩ። በኢየሱስ
ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር አመስግኑ ፤ ዘምሩም።
Pray You for us and for all Christians who bade us to
make mention of them. Praise you and sing in the peace
and love of Jesus Christ.
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ ዘኢይትነገር ፣ ሀበኒ ከመ እንሣዕ
ለሕይወት ዘንተ ሥጋ ወደመ ዘእንበለ ኵነኔ።
የማይነገር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሦስት የምትሆን ይህንን ሥጋና
ደም ሕይወት ሊሆነኝ ሳይፈረድብኝ እቀበል ዘንድ ስጠኝ።
Holy! Holy! Holy! Trinity ineffable, grant me to receive
this Body and this Blood for life and not for
condemnation.
ሀበኒ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ ከመ አስተርኢ በስብሐቲከ
ወእሕየው ለከ እንዘ እገብር ዘዚአከ ፈቃደ።
በጌትነትህ እንድገለጽ ደስ የሚያሰኝህን ፍሬ እሠራ ዘንድ
ስጠኝ። የአንተንም ፈቃድ እየሠራሁ እኖርልህ ዘንድ ስጠኝ።
Grant me to bring forth fruit that shall be well pleasing
unto You, to the end that I may appear in Your glory
and live unto You doing Your will.
በተአምኖ እጼውዐከ አብ ወእጼውዕ መንግሥተከ ይትቀደስ
እግዚኦ ስምከ በላዕሌነ ፤ እስመ ኃያል አንተ እኵት ወስቡሕ
ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም።
በማመን አባት ብዬ እጠራሃለሁ። አቤቱ ስምህ በእኛ ላይ
ይመስገን። ምስጉን ክቡር የምትሆን ኃያል አንተ ነህና ለአንተ
ክብር ይገባሃል ለዘለዓለሙ።
In faith, I call upon You, Father, and call upon Your
Kingdom; hallowed, Lord, be Your name upon us, for
mighty are You, praised and glorious, and to You be
glory, world without end.
እስመ ኃያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ
ዓለም።
ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘለዓለሙ።
praised and glorious, and to You be Glory, for ever and
ever.
ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢአነ ከመ ለሕይወተ ነፍስ
ይኩነነ ፈውሰ።
ለነፍሳችን አነዋወር መድኃኒት ይሆነን ዘንድ ሥጋውንና
ደሙን ተቀበልን ፤ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።
We thank God for that we have partaken of His Holy
things;
ዘተመጦነ ንስእል ወንትመሐፀን እንዘ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር
አምላክነ።
የተቀበልን እኛ አምላካችንን እግዚአብሔርን እያመሰገንን
እንለምናለን ፤ አደራም እንላለን።
we pray and trust that which we have received may be
healing for the life of the soul while we glorify the Lord
our God.
አሌዕለከ ንጉሥየ ወአምላኪየ ወእባርክ ለስምከ ቅዱስ ለዓለም
ወለዓለመ ዓለም።
ንጉሤና ፈጣሪዬ ሆይ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። ቅዱስ ስምህንም
ለዘለዓለም አመሰግናለሁ።
I will extol You, my King and my God, and I will bless
Your Holy name for ever and ever.
አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
በሰማይ ያለህ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
Our Father You are in heaven, lead us not, Lord, into
temptation.
ተመጦነ እምሥጋሁ ቅዱስ ወእምደሙ ክቡር ለክርስቶስ።
ከክርስቶስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ ተቀበልን።
We have received of the Holy Body and the precious
Blood of Christ.
ኵሎ አሚረ እባርከከ ወእሴብሕ ለስምከ ቅዱስ ለዓለም
ወለዓለመ ዓለም።
ዘወትር አከብርሃለሁ። ቅዱስ ስምህንም ለዘለዓለሙ
አመሰግናለሁ።
Every day will I bless You, and I will praise Your name
for ever and ever..
አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
በሰማይ ያለህ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
Our Father You are in heaven, lead us not, Lord, into
temptation.
ወናእኵቶ ይደልወነ ከመ ንሳተፍ ምስጢረ ክብርተ ወቅድስተ።
ክብርት ቅድስት የምትሆን ምስጢርን እንሳተፍ ዘንድ ስላበቃን
ልናመሰግነው ይገባል።
And let us give thanks unto him that make us meet to
communicate in the precious and Holy mystery.
ስብሐተ እግዚአብሔር ይነግር አፉየ ወኵሉ ዘሥጋ ይባርክ
ለስሙ ቅዱስ ፣ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
አንደበቴ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል። የሥጋ ፍጥረትም
ሁሉ ቅዱስ የሚሆን ስሙን ያመሰግናል ለዘለዓለሙ።
My mouth shall speak the praise of the Lord, and let all
flesh bless His Holy name for ever and ever.
አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
በሰማይ ያለህ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
Our Father You are in heaven, lead us not, Lord, into
temptation.
ኀዳፌ ነፍስ - Pilot of the Soul
አሜሃ መልዐ ፍሥሓ አፉነ ወተኀሥየ ልሳንነ ዘነሣእነ እምዝንቱ
ምሥጢር ዘኢይማስን።
ይን ጊዜ ከማይጠፋ ምሥጢር የተቀበልን የእኛ አፋችን ደስታን
ተመላ ፤ አንደበታችንም ደስ አለው።
Then was our mouth milled with laughter and our tongue
with singing, we who have received this indestructible
mystery.
ኦ እግዚኦ ዘዐይን ኢርአየ ወእዝን ኢሰምዐ ውስተ ልበ ሰብእ
ዘኢተሀለየ ዘአስተዳሎከ አምላክ ለእለ ያፈቅሩ ስመከ ቅዱስ።
አቤቱ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡናም
ያልታሰበውን ቅዱስ ስምህን ለሚውዱ ሰዎች ያዘጋጀህ አምላክ
ምን ትደንቅ።
O Lord, that which eye has not seen, nor ear heard,
neither have it entered into the heart of man, You have
prepared, O God, for them that love Your holy Name;
ወከሠትከ ለነ ለሕፃናት ንኡሳን እለ ውስተ ቤተ ክርስቲያንከ
ቅድስት። ኦ አብ እስመ ዝንቱ ሥምረትከ ዘኮነ በቅድሜከ
እስመ መሐሪ አንተ እግዚአብሔር አምላክነ።
በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ ላለን ለታናናሾች ሕፃናት ለእኛ
ገለጽህ። አብ ሆይ ፈቃድህ በፊትህ የሆነው አምላካችን
እግዚአብሔር አንተ ይቅር ባይ ስለ ሆንህ ነውና።
and have revealed unto us small babies in Your Holy
church : even so, Father, for so it seemed good in
Your sight, because You are compassionate, O Lord our
God!.
ጸልዩ።
ጸልዩ።
Pray.
ወለከ ንፌኑ እስከ አርያም ስብሐት ወክብረ ለአብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
ለአንተም እስከ አርያም ድረስ ምስጋናን ክብርንም ለአብና
ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም እናቀርባለን ፤ ዛሬም ዘወትርም
ለዘለዓለሙ።
To You we send, unto the highest heaven, glory and
honour, Father, Son and the Holy Spirit, both now and
ever and world without end.
አሜን
Amen
ቡራኬ
Benediction
ሕዝብ/People/
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ
ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለ
ዕለትነ ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንሕነኒ
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ
ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እነደሆነ እንዲሁም በምድር ትሁን
የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን፤
Our Father who are in heaven Hallowed be Your name.
Your kingdom come Your will be done on earth as it is
in heaven Give us this day our daily bread, and forgive us
our trespasses
ንኅድግ ለዘ አበሰ ለነ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ
አድኅነነ ወባልሐነ እምኩሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ
መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል ፤ አቤቱ ወደ ፈተና
አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና
ኃይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን።
as we forgive those who trespass against us and lead
us not into temptation but deliver us from evil. For
Yours is the kingdom, and the power, and the glory, for
ever and ever, Amen.
በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም
ለኪ ድንግል በሕሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ እመ እግዚአብሔር
ጸባኦት ሰላም ለኪ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ ገብርኤል
ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም
ድንግል ነሽ ፤ የአሸናፊ እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ
ይገባሻል
By the salutation of the Saint Angel Gabriel, oh my Lady
Mary I salute You, You are virgin in thought, And Virgin
in body, the mother of God Tsabaot (The Lord of Host)
salutation to You.
ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ ተፈሥሒ
ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ ሰአሊ ወጸልዪ
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ
የተባረከ ነዉ። ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል
እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን
Blessed are You among women and blessed is the fruit
of Your womb Jesus Rejoice You who is hailed, O
graceful god is with You. Beseech and pray for our
ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይ ለነ
ኃጣውኢነ።
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን
ኃጢአታችንን ያስተስርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
mercy to Your beloved son Jesus Christ that He may
forgive us our sins. Amen.
ኦ ንጉሠ ሰላም ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላመከ ሀበነ ወአጽንዕ
ለነ ሰላመከ ወሥረይ ለነ ኃውኢነ ወረስየነ ድልዋነ ከመ ንሑር
ወንእቱ ውስተ አብያቲነ በሰላም።
የፍቅር ባለቤት የሰላም ንጉሥ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ሰላምህን ስጠን ሰላምህን አጽናልን ኃጢአታችንንም ይቅር በለን
በሰላም ወደ ቤታችን ሄደን እንገባ ዘንድ የበቃን አድርገን፡፡
O peaceful king of peace, Jesus Christ, grant us Your
peace and confirm unto us Your peace, and forgive us
our sins, and make us worthy to go out and enter into
our homes in peace.
አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በእደ
ገብሩ ካህን ከመ ይባርክሙ።
አገልጋይ በሚሆን በካህኑ እጅ ይባርካችሁ ዘንድ ፤
በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
Bow your heads in front of the Lord our God, that He
may bless you at the hand of His servant the priest.
አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ወይሣለሃነ።
አሜን እግዚአብሔር ይባርከን ይቅርም ይበለን።
Amen. May God bless us and forgive us.
ኦ እግዚኦ አድኅን ሕዝበከ ወባርክ ርስተከ ረዓዮሙ ወአልዕሎሙ
እስከ ለዓለም።
አቤቱ ሕዝብህን አድን ፤ ርስትህንም ባርክ። አቤቱ ሕዝብህን
አድን ፤ ርስትህንም ባርክ። እስከ ዘላለሙ ጠብቃቸው ፤ ከፍ
ከፍም አድርጋቸው።
O Lord, save You people and bless Your inheritance.
Feed them, lift them up for ever,
ወዕቀባ ለቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት እንተ አጥረይካ ወቤዘውካ
በደሙ ክቡር ለዋሕድ ወልድከ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃነ
ኢየሱስ ክርስቶስ።
በአንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጀሃት ፣ ቤዛም የሆንኻት
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንህንም ጠብቃት።
and keep Your church which You did purchase and
ransom with the precious blood of Your only-begotten
Son, our Lord and our God and our Savior Jesus Christ;
ወዘጸዋዕካ ትኩን ማኅደረ ለነገሥት ወለመኳንንት ለዘመድ
ንጹሕ ወለሕዝብ ቅዱስ እለ መጻእክሙ ወእለ ተጋባእክሙ
ወእለ ጸለይክሙ ውስተ ዛቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን።
ለነገሥታትና ለመኳንንት ፣ ለንጹሕ ወገንና ቅዱስ ለሆነ ሕዝብ
ማደሪያ ትሆን ዘንድ የጠራሃት። በዚች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
መጥታችሁ ተሰብስባችሁ የጸለያችሁ ፤
And which You have called to be a dwelling-place for
kings and rulers, for pure kindred and Holy people, You
who have come and gathered and prayed in His Holy
church,
እለ በላዕክሙ ሥጋሁ ቅዱሰ ወእለ ሰተይክሙ ደሞ ክቡረ
ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሥረይ ለክሙ ኃጢአተክሙ
ዘገበርክሙ እመሂ በአእምሮ አው በኢያእምሮ።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን የበላችሁ ፤
ክቡር ደሙንም የጠጣችሁ ፤ በማወቅ ወይም ባለማወቅ
የሠራችሁትን ኃጢአታችሁን ይቅር ይበላችሁ፡፡
and You who have eaten the Holy body and drunk the
precious blood of our Lord Jesus Christ. May He forgive
Your sins which You have committed wittingly or
unwittingly .
በዘኀለፈ ይምሐርክሙ ወበዘይመጽእ ይዕቀብክሙ በእንተ
ሥጋሁ ሥጋ መለኮት ወበእንተ ደሙ ደመ ሕግ ወሥርዓት፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ጸባዖት
ሥጋ መለኮት ስለሚባል ሥጋው የሕግና የሥርዓት ደም
ስለሚሆን ደሙ የአሸናፊ የእግዚአብሔር ልጅ በድንጋሌ ሥጋ
በድንጋሌ ሕሊናም ኅትምት የምትሆን የማርያም ልጅ
May He forgive you your past sins and keep you from
future ones, for the sake of His body, the divine body,
and for the sake of His blood, the blood of the
covenant of Jesus Christ the Son of the Lord of hosts,
ወወልደ ማርያም ንጽሕት በድንግልና ሕሊና ወበድንግልና ሥጋ
ኅትምት ለዓለመ ዓለም አሜን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ባለፈው ይቅር ይበላችሁ ፤ በሚመጣውም
ይጠብቃችሁ። ለዘላለሙ አሜን።
and the Son of pure Mary, who has sealed the Vrginity of
Her conscience and body, world without end. Amen.
ቡራኬ
Benediction
እግዚአብሔር የሀሉ ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
The Lord be with you all.
ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with Your spirit.
አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ለአግብርቲሁ በሰላም ሥርየተ
ይኩነነ። ዘተመጦነ ሥጋከ ወደመከ አብሐነ በመንፈስ ንኪድ
ኵሉ ኃይሎ ለጸላዒ።
አሜን እግዚአብሔር እኛን አገልጋዩቹን በሰላም ይባርክ ፤
የተቀበልነውን ሥጋህና ደምህ ለሥርየት ይሁነን ፤ የጠላትን
ኃይል ሁሉ በመንፈስ እንረግጥ ዘንድ አሰልጥነን።
Amen. May God bless us, His servants, in peace.
Remission be unto us who have received Your body and
Your blood. Enable us by the Spirit to tread upon all the
power of the enemy.
በረከተ እዴከ ቅድስት እንተ ምልዕተ ምሕረት ኪያሃ ንሴፎ
ኵልነ እምኵሉ ምግባረ እኩይ አግኀሠነ ወውስተ ኵሉ ምግባረ
ሠናይ ደምረነ። ቡሩክ ዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ።
ምሕረትን የተሞላች ክብርት የምትሆን የእጅህን በረከት ሁላችን
ተስፋ እናደርጋለን። ከክፉ ሁሉ አርቀን። በበጎውም ሥራ ሁሉ
አንድ አድርገን። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም የሰጠን ብሩክ
ነው።
We all hope for the blessing of Your Holy hand which is
full of mercy. From all evil works keep us apart, and in
all good works unite us. Blessed be He that has given
us His Holy body and His precious blood.
ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ መስቀሉ ለኢየሱስ
ክርስቶስ ፤ ኪያከ እግዚኦ ነአኵት ነሢአነ ጸጋ ዘመንፈስ ቅዱስ።
ጸጋን ተቀበልን ፤ ደኅንነትንም በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ
ኃይል አገኘን። አቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ጸጋን ተቀበልን
፤ አንተን እናመሰግንሃለን።
We have received grace and we have found life by the
power of the cross of Jesus Christ. Unto You, Lord, do
we give thanks, for that we have received grace from
the Holy Spirit.
እትዉ በሰላም።
በሰላም ግቡ።
Go ye in peace.
አሜን
Amen
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።
አሜን።
ምሥጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅድስ ለአንድ አምላክ።
አሜን።
Glory to the Father, to the Son, and to the Holy Spirit, One God.
Amen.
ኑ እንቅረብ መከራ ሳይመጣ
ኑ እንቅረብ መከራ ሳይመጣ፤
ሥጋውን እንብላ ሥጋውን እንብላ ደሙንም እንጠጣ።
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው፤
ተሰውቶልናል እንመገበው።
እድፉን ኃጢያታችን በንስሐ አጥበን፤
እንቀበል አምነን በልጅነታችን።
መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው፤
በስተእርጅና አይደለም በወጣትነት ነው።
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት፤
ከዋክብት ከሰማይ የተነጠፉለት፤
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት።
ቅድስት እናታችን ቤተ ክርስቲያን፤
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን።
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ፤
ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ።
ኑ እንቅረብ መከራ ሳይመጣ፤
ሥጋውን እንብላ ሥጋውን እንብላ ደሙንም እንጠጣ።
ይህ ቁርባን ክቡር ነው
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ፤
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ፤
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ።
ዋ! ምን አፍ ነው የሚቀበለው፤
ዋ! ምን ጥርስ ነው የሚያላምጠው፤
ዋ! ምን ሆድ ነው የሚሸከመው፤
ነበልባል ያለበት የሚያቃጥል ነው፤
በንጽሕና ሆኖ ላልተቀበለው፤
የሚያፍገመግም የሚጎዳ ነው።
አምላካችን ሆይ አንተ ይቅር ባይ፤
እንደ ቸርነትህ በደልን አትይ፤
እንደ ቸርነትህ በደልን አትይ።
አሜን አሜን ብለን ተቀብለናል፤
በድፍረትም ሳይሆን በፍርሃት ቀርበናል፤
በድፍረትም ሳይሆን በፍርሃት ቀርበናል።
ማክበር ይገባናል በንጽሕና ሆነን፤
ደፍረን አናቃለው እንዳያቃጥለን፤
ደፍረን አናቃለው እንዳያቃጥለን።
እንደምታዩትም ይህ ቁርባን ፈራጅ ነው፤
እንደሌላው ሳይሆን የተቀደሰ ነው፤
እንደሌላው ሳይሆን የተቀደሰ ነው።
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ፤
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ፤
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ።
ሱራፌል ኪሩቤል ጸዎርተ መንበር፤
ሊይዙት ያልቻሉት ፈርተውት በክብር፤
ሊይዙት ያልቻሉት ፈርተውት በክብር።
እኛ ተመገብነው አገኘን ድኅነት፤
በነፍስ በሥጋችን ሆነልን ሕይወት።
በነፍስ በሥጋችን ሆነልን ሕይወት።
ምንጭ / Source: mytewahdo.org
← Back to Kidase