ህፃናት ፊልም አይተው ሽጉጥ ያዙ ብዬ ስደነቅ ስገረም፤
ይብስ ነገር ታዬ መቼም ጉድ ሳይመጣ መስከረም አይጠባም።
ይብስ ነገር ታዬ መቼም ጉድ ሳይመጣ መስከረም አይጠባም።
የሚማሩት ትምህርት ይህንን ይመስላል፤
በግፍ ሰው መሰየፍ ድል ያጎናፅፋል፤
ከእናት ማህፀን ልጅ ዘክዝኮ ማውጣት ዝናህን ያሰፋል።
በግፍ ሰው መሰየፍ ድል ያጎናፅፋል፤
ከእናት ማህፀን ልጅ ዘክዝኮ ማውጣት ዝናህን ያሰፋል።
አዎ
በተለይ በተለይ ህፃን አይኑ እያየ የተማረው ነገር፤
አንገት በገጀራ ሆድን በሹል ካራ የእመረጡ ዘር።
በተለይ በተለይ ህፃን አይኑ እያየ የተማረው ነገር፤
አንገት በገጀራ ሆድን በሹል ካራ የእመረጡ ዘር።
በግፍ ለሚጨፈጨፉት ንጹህ ኢትዮጵያውያን
እሱባለው ቸኮል
ግንቦት 7/2013
ግንቦት 7/2013