የጀገንኩበት ቋሚ ስራዬ ዉሉ አፈትልኮኝ ጠፋ ፈረሰ ፤
በሚያልፍ ዱብዳ እቅድ ጠፋብኝ ህልሜ ኮሰሰ፤
በሚያልፍ ዱብዳ እቅድ ጠፋብኝ ህልሜ ኮሰሰ፤
⁂
ከተስፋ ባህር ፀበል ቀምሼ ላድግ ተምሬ፤
ራዕይ ዓላማ ውስጤን ተጋብቶት ኖሬ አቀርቅሬ፤
የዘመን እሾህ አደናቃፊ ቀርቦኝ ደንብሬ ፤
ራዕይ ዓላማ ውስጤን ተጋብቶት ኖሬ አቀርቅሬ፤
የዘመን እሾህ አደናቃፊ ቀርቦኝ ደንብሬ ፤
⁂
ያሰብኩት በአንቃፊዉ እሾህ ተበታተነ ፤
ለፈተና መልስ የያዝኩት እዉቀት ፈጥኖ ተነነ፤
ለፈተና መልስ የያዝኩት እዉቀት ፈጥኖ ተነነ፤
⁂
እንቅፋቱ ሲያልፍ ጊዜ በዓላማህ ተራመድ ሲለኝ፤
የተበተነው እቅድ እዉቀቴ ለእድገቴ ሲያሻኝ ፤
አበርታኝ ፣
ያለፈው ልምዴን ፈልገህ አምጣ ራዕይ ስጠኝ፤
ህልሜ እንዲፈፀም በእዉቀት ዱር ምራኝ ብዬ ለመንኩኝ፤
ጭንቀት ሲከበኝ ለምከተለዉ ለሰማዩ አዳኝ ።
የተበተነው እቅድ እዉቀቴ ለእድገቴ ሲያሻኝ ፤
አበርታኝ ፣
ያለፈው ልምዴን ፈልገህ አምጣ ራዕይ ስጠኝ፤
ህልሜ እንዲፈፀም በእዉቀት ዱር ምራኝ ብዬ ለመንኩኝ፤
ጭንቀት ሲከበኝ ለምከተለዉ ለሰማዩ አዳኝ ።
እሱባለው ቸኮል