አዎን ፤
ተሳስቼ ነበር ፤
መሆን በሌለበት በማያስት ነገር ፤
……………………………….
ተሳስቼ ነበር ፤
መሆን በሌለበት በማያስት ነገር ፤
……………………………….
በፍቅርህ ተይዤ ሰላም እርቆኛል፤
አንተን ካላየሁኝ በሽታ ይወረኝ ጤና ይርቀኛል፤
ፍቅርህ ግለት አለዉ ከመጠን ያለፈ ይቀጣ ይገርፋል፤
አንተም አትረዳኝ ግለቱ እንዲበርደኝ ማገዝ ተስኖሃል፤
ሌላዉ ይቅርና ማፍቀሩን ረስተህ ማፍቀሬን መረዳት እንዴት ያቅትሃል?
…………………………………….
አንተን ካላየሁኝ በሽታ ይወረኝ ጤና ይርቀኛል፤
ፍቅርህ ግለት አለዉ ከመጠን ያለፈ ይቀጣ ይገርፋል፤
አንተም አትረዳኝ ግለቱ እንዲበርደኝ ማገዝ ተስኖሃል፤
ሌላዉ ይቅርና ማፍቀሩን ረስተህ ማፍቀሬን መረዳት እንዴት ያቅትሃል?
…………………………………….
ብለሽ ስትነገሪኝ መረዳት መዋረድ መሥሎ ስለታየኝ፤
አንችን አሳንሶ እኔን አስኮፍሶ ሰይጣን ስላሳየኝ፤
አንች ስታለቅሽ ስሜትሽ ጨዋታ ቀልድ እየመሰለኝ፤
ፍቅርሽን ረገጥሁ አንችንም አራቅሁኝ፤
…………………………………….
አንችን አሳንሶ እኔን አስኮፍሶ ሰይጣን ስላሳየኝ፤
አንች ስታለቅሽ ስሜትሽ ጨዋታ ቀልድ እየመሰለኝ፤
ፍቅርሽን ረገጥሁ አንችንም አራቅሁኝ፤
…………………………………….
ይሄዉ ዛሬ ደሞ፤
የተኩራራሁበት አንችን ያራቅሁበት
………….. ወኔዬ ተጣሞ፤
ልቤ ከጥላቻ ከአጎል መኮፋፈስ ፈፅሞ አገግሞ፤
የተኩራራሁበት አንችን ያራቅሁበት
………….. ወኔዬ ተጣሞ፤
ልቤ ከጥላቻ ከአጎል መኮፋፈስ ፈፅሞ አገግሞ፤
ልቤ ከገባበት የታወረ ጥላት ተነጥቆ ሲወጣ፤
እንዳዲስ ሲመኝሽ አንች ግን እራቅሽኝ ተረኝነት መጣ፤
እንዳዲስ ሲመኝሽ አንች ግን እራቅሽኝ ተረኝነት መጣ፤
…………………………
ያኔ ስትነግሪኝ እኔ እያናናቅሁሽ ምንም ብንቅሽም፤
አልጠላህም መቼም
ብርሃን ቢተረከም ጀምበር ብትጠልቅም፤
ያልሽኝ የሳግ ትንቢት እስክሞት አይጠፋም ፤
ያኔ ስትነግሪኝ እኔ እያናናቅሁሽ ምንም ብንቅሽም፤
አልጠላህም መቼም
ብርሃን ቢተረከም ጀምበር ብትጠልቅም፤
ያልሽኝ የሳግ ትንቢት እስክሞት አይጠፋም ፤
ቢሆንም፤
እኔ ግፍ ብሰራ ድሮ ብጠላሽም፤
ፀፅቶኝ ስመለስ ልታፈቅሪኝ ቀርቶ ደብዳቤ አትመልሽም፤
ሳፈቅርህ ኗሪ ነኝ ያልሽዉ ቃል አልሰራም ።
እኔ ግፍ ብሰራ ድሮ ብጠላሽም፤
ፀፅቶኝ ስመለስ ልታፈቅሪኝ ቀርቶ ደብዳቤ አትመልሽም፤
ሳፈቅርህ ኗሪ ነኝ ያልሽዉ ቃል አልሰራም ።
እሱባለው ቸኮል ሙሉዬ
ነሐሴ 16/12/12
ነሐሴ 16/12/12