መንገዱን ጨርቅ ያርገው ሁሌም ክፉ አይንካሽ ብዬሽ እበቃለሁ ፤
ባሳለፍነው ህይወት የውሸት ድራማ ግን በጣም አዝናለሁ ፤
ባሳለፍነው ህይወት የውሸት ድራማ ግን በጣም አዝናለሁ ፤
በተሰጠኝ ማሰብ መውደድሽ የውሸት መሆኑን ባላጣም፤
ቀኑ ደርሶ እስክትሄጅ አንቺ እየጠላሽኝ ልቤ ካንቺ አልራቀም ፤
ቀኑ ደርሶ እስክትሄጅ አንቺ እየጠላሽኝ ልቤ ካንቺ አልራቀም ፤
አሁን ባለንበት አንቺን የመሰለ የሚታመን ሸጋ መገኘቱ ገርሞኝ ፈጣሪን ብክብም፤
ከመሸ ገብቶኛል በክህደት ሰምጣለች እውነተኛ ጠፍቷት አዝናለች ይቺ አለም።
ከመሸ ገብቶኛል በክህደት ሰምጣለች እውነተኛ ጠፍቷት አዝናለች ይቺ አለም።
ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ጠልተሽ ስትዘጊኝ ለምኜ መለስሁሽ፤
መውደደሽን በግላጭ እንድተርኪልኝ ለወራት ለመንኩሽ ፤
ቸኩያለሁ ብዬም ቀናት እየቀጠርኩ በብዙ ታገስሁሽ ፣
ታዲያ ዛሬ ደርሶ የመጥላትሽን አድማስ ገልፀሽ አስመሰከርሽ፤
መውደደሽን በግላጭ እንድተርኪልኝ ለወራት ለመንኩሽ ፤
ቸኩያለሁ ብዬም ቀናት እየቀጠርኩ በብዙ ታገስሁሽ ፣
ታዲያ ዛሬ ደርሶ የመጥላትሽን አድማስ ገልፀሽ አስመሰከርሽ፤
እንደኔ ለፍላፊ የልብ መጻፍ ጻፊ ለማኝ ባይኖርም ፤
እንዳንቺም ደንዳና ስሜት ማይረዳ ሴት አልተፈጠረም ።
እንዳንቺም ደንዳና ስሜት ማይረዳ ሴት አልተፈጠረም ።
በስሜት ሰምጬ ላንቺ የላክዃቸው መልዕክት ብዛታቸው፤
የአሳባቸው ጥልቀት ስፋት ተማፅኗቸው፤
ፀሀፊና ላኪ እንጅ ተቀብሎ ሚያነብ ያልተገኘላቸው ።
የአሳባቸው ጥልቀት ስፋት ተማፅኗቸው፤
ፀሀፊና ላኪ እንጅ ተቀብሎ ሚያነብ ያልተገኘላቸው ።
ላንቺ መጨነቄን በጥልቀት መውደዴን ብትረጅ ኖሮ፤
በመዓልት በሌሊት የዝርው ለቀሶየን የጭንቀት ሮሮ፤
አድማጭ የሌለውን እያደር ሚበዛ ስላንቺ እንጉርጉሮ ፤
በመዓልት በሌሊት የዝርው ለቀሶየን የጭንቀት ሮሮ፤
አድማጭ የሌለውን እያደር ሚበዛ ስላንቺ እንጉርጉሮ ፤
⁂
እኔን ለመረዳት ለማዳመጥ ፍጹም ፍላጎት የለሽም ፤
ልቤ ስለደማ አንቺን መለመኛ ቃላትን አትሰሚም፣
ልቤ ስለደማ አንቺን መለመኛ ቃላትን አትሰሚም፣
ጥሩ እየተመኘሁ እሷ ለማትወደኝ እኔ እየወደድኳት፤
ዳግም ላንገናኝ እሷ ስለሳሳች በለቅሶ ሸኘኋት፤
ዳግም ላንገናኝ እሷ ስለሳሳች በለቅሶ ሸኘኋት፤
እሱባለው ቸኮል