አጥብቄ ልንገርሽ ፤
ወደድሁሽ የምልሽ ሳስመስል ከሆነ አንችም ካላመንሽኝ፤
መሳሪያ የያዘ የዋሸ ሚገድል መርማሪ ላኪብኝ፤
መውደድህ 'እውነት ነው' በሚባል መጠየቅ ልፋጠጥ ቃል አለኝ ፤
አዎ ከኔ በላይ ስል እመልሳለሁ ውሸት መቼ ወጣኝ?
ምርመራው ሲያበቃ ውሸታም ከሆንኩኝ ፤
መሳሪያው ታዝዞ ድቅን ይበልብኝ፤
የፊጥኝ ታስሬ በውሸት መውደድ ክስ ሞት ይፍረድብኝ ።
እውነተኛ ሆኜ ዋሽቷል እንዳልባል፤
ሀቀኛ መርማሪ እውነተኛ ዳኛ ልትልኪ ይገባል ።
እሱባለው ቸኮል