እኔኮ ስለማፈቅርሽ ነዉ የምጠረጥረዉ፤
በቀናት ልዩነት ስሜትሽ ስለኔ ምን ይላል የምለው ፤
አንች ብትሰለችኝ ብትርቂኝ ቆይተሽ፤
አላዉቅህም ብትይ የተሻለ ስበቀሽ፤
አይቻልም እና ለኔ አንችን መለየት ፤
አሁን ብጠረጥር ይሻላል ከማጣት።
አንች እንደሁ፤
የዉስጤን አታዉቂም፤
የፍቅሬ ርዝመቱ ጥበቱ ስፋቱ ሊገባሽ አልቻለም ፤
ፍቅርሽ ካልወጣልኝ ወይ ካልተረዳሽኝ፤
መጠርጠር መብቴ ነው እመነኝ አትበይኝ።
እሱባለው ቸኮል