እንዳሁኑ ሳይሆን ፤
በፍቅርሽ ሰምጬ አንድላይ እንዳለን ፤
በፍቅርሽ ሰምጬ አንድላይ እንዳለን ፤
ለብቻ መሆኔ ሳይከሰት በፊት ፤
ፍቅርን እያመለክሁ በመዉደድሽ ግፊት ፤
ፍቅርን እያመለክሁ በመዉደድሽ ግፊት ፤
እኔ ባይገባኝም፤
በዉሸት ገፅታሽ በክህደት አባዜ ፤
ባንች ለመጠለል እንዳራቅሁ ከወንዜ ፤
በዉሸት ገፅታሽ በክህደት አባዜ ፤
ባንች ለመጠለል እንዳራቅሁ ከወንዜ ፤
ያኔ በፍቅራችን አንች ብልህ ነበርሽ እኔ ደግሞ ሞኙ፤
አንች ሽርሙጥና እኔ ግን ለመኖር በፍቅር ካታኙ።
አንች ሽርሙጥና እኔ ግን ለመኖር በፍቅር ካታኙ።
ዛሬ ግን፤
አይንሽ እንዲጠፋ እግርሽ እንዲቆረጥ ለአምላኬ ባልከስም፤
ወጦልኝ ነቅቼ መከተል አቆምሁኝ አንችን አልመኝም።
ወጦልኝ ነቅቼ መከተል አቆምሁኝ አንችን አልመኝም።
እሱባለው ቸኮል