እንዲያው እንበልና አንቺ እኔን ብትሆኚ፤
እንደኔው በቀና በጠለቀ ፍቅር ድንገት ብትባክኚ፤
በእውነት ያልሆንሽውን ለኔ ስትይ ሆነሽ በእንበል ወስኚ።
እንደኔው በቀና በጠለቀ ፍቅር ድንገት ብትባክኚ፤
በእውነት ያልሆንሽውን ለኔ ስትይ ሆነሽ በእንበል ወስኚ።
ቢሆን እንበልና፤
ተፈጥሮ በቸረሽ የህይወትሽ ቁና
ተፈጥሮ በቸረሽ የህይወትሽ ቁና
ፍቅር ብትወጥኚ አንዱን ሰው ብትወጂው፤
ልበል ልተው በሚል ከፍርሃት ዋዜማ ወጥተሽ ብታስረጂው፤
ልበል ልተው በሚል ከፍርሃት ዋዜማ ወጥተሽ ብታስረጂው፤
እንበል በመጥፎ እድል ወንዱ ልጅ ጨክኖ እያጉረመረመ ምላሹን ቢነፍግሽ፤
ተስፋሽ ተመዘግዝጎ ቢጠብቅም ልብሽ፤
ተስፋሽ ተመዘግዝጎ ቢጠብቅም ልብሽ፤
ነገር ግን እምቢ ቢል መውደድሽን ቢያከፋው፤
ተስፋሽ ተጨማዶ ልጁን ብትተይው ፤
አንቺ ወይስ እሱ ማነው ጥፋተኛው ?
ተስፋሽ ተጨማዶ ልጁን ብትተይው ፤
አንቺ ወይስ እሱ ማነው ጥፋተኛው ?
በይ አትጨነቂ እንበል ብዬ ነው በፍቅር ያቆምሁሽ ፤
እኔ ብሆንሳ በሚባል ተጠየቅ ሃስብሽን ልገዛሽ።
እኔ ብሆንሳ በሚባል ተጠየቅ ሃስብሽን ልገዛሽ።
እሱባለው ቸኮል