እሷ ጊዜ ጥሏት አትሰማኝም እንጅ፤
መከርሁኣት ገፀስሁኣት ማንቁርቴ እስኪያፈጅ።
ትስማ እንደሁ ትስማ ያልኩኣትን ቁምነገር፤
ወይ ይገድል ይሰብራል ያለሀቅም ማፍቀር።
ልቧ ተመልሶ ከተረዳች ደግሞ፤
መፋቀር ለዝሙት ወንጀል ነው ፈፅሞ።
ትርጉሙን አታውቀው ወይ ሲባል አልሰማች፤
ሰው ሲያደርግ ለምዳ ተያዘኩ ተያዝኩ አለች።
መክሬ ወቅሬ እስካልተመለሰች፤
እኔም አያታለሁ እሷም ትነዳለች።
እውነት ለመናገር ያልኩኣትን ከናቀች፤
ውድ እንቁ ንብረቷን አልማዟን ታጣለች።
ይቀመጥ አቆይው ስላት ምክሬን ጥሳ፤
ስትመጣ ታዘቧት አልማዟን ጨርሳ።
እሱባለው ቸኮል
ህዳር 2013 ዓ.ም